የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች በወቅታዊ የሰላም ጉዳይ ተወያዩ፡፡
በውይይቱ የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር እና የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ እና አስተዳደር ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡
በውይይቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጋርዳቸው ወርቁ(ዶ/ር) አጃንዳው በሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ ውይይት ለማድረግ መሆኑን ገልጸው ሰላም እጅግ ውድ እና ለሁሉም ነገር መሰረት ነው ብለዋል።
ዶ/ር ጋርዳቸው አያይዘውም የዩኒቨርሲቲው ምሁራን በክልላችን እየተስተዋለ ባለው የሰላም እና ጸጥታ ችግሮች ዙሪያ የመፍትሄ እና አሻጋሪ ሀሳቦችን እንዲያመነጩ እና ሀሳባቸውን እንዲሰጡ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልጸው ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች እና ምሁራን የሰላም ዘብ እንዲሆኑ አሳስበዋል፡፡
የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳደሪ እና የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል አቶ ቴዎድሮስ እንዳለው በመክፈቻ ንግግራቸው እንተናገሩት የዩኒቨርሲቲ ምሁራን የተለያዩ አካላት ስብጥር መሆኑን ጠቅሰው ውይይቱ በዋናነነት ከሰላምና ጸጥታ አኳያ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ሚና ፣ከሰላም ዕጦት መውጫ መንገድ መወያየት እና አማራጭ የመፍትሄ ሀሳቦችን ለማሰባሰብ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በውይይቱ የተገኙት ኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት የ302ኛ ኮር ም/አዛዥ ኮሎኔል ሰጤ አራጌ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰላምን ለማስጠበቅ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ሰላም እና መረጋጋት እንዲመጣ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ከፍተኛ ሃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በውይይቱ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳብ እና አስተያየቶች ተነስተው በሚመለከታቸው አካት ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ