"እንደ ሀገር ያጋጠመንን የትምህርት ጥራት ለማስተካከል የአካዳሚክ ፕሮግራሞችንና ተቋማዊ ጥራትን ኦዲት ማድረግ አስፈላጊ ነው'' ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት
----------------
በትምህርት ጥራት፣ ውጤት ተኮር ትምህርት፣ የአካዳሚክ ፕሮግራሞችንና ተቋማዊ ጥራትን ኦዲት ማድረግና እውቅና ለመስጠት የሚያስችል (Education Quality, Outcome Based Education, Quality Audit, and Academic Program Accreditation) ስልጠና ለዩኒቨርሲተው አካዳሚክ ካውንስል አባላት ተሰጥቷል፡፡
በስልጠናው ወቅት እንደሀገር በትምህርት ጥራት ላይ ያጋጠመውን ችግር ለማስተካከል የአካዳሚክ ፕሮግራሞችንና ተቋማዊ ጥራትን ኦዲት ማድረግ እንደሚገባ ዶ/ር ጋርዳቸው ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጡ የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን አሟልተው እንዲሰጡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው የፕሮግራሞችን ጥራት እና አግባብነት ከፍ እንዲሉና ለሁሉም ፕሮግራሞች እውቅና(Accreditation) ለማግኘት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ ይህን ለማሳካትም የሚያግዘው በትምህርት ጥራት፣ ውጤት ተኮር ትምህርት፣ የአካዳሚክ ፕሮግራሞችንና ተቋማዊ ጥራትን ኦዲት ለማድረግ እና እውቅና ስርዓት አሰጣጥ ላይ ግንዛቤ የመፍጠር ስልጠና አንዱ ተግባር መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በዚህ ዓመትም የተመረጡ ፕሮግራሞች ኦዲት ተደርገው እውቅና(Accreditation)እንዲኖራቸው ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid0n2aMs1b7eoPfdviyTtHxdN22Sm7YGPcnshSTz62Jrthawe46qucNTgPAQt2E4eml/?app=fbl