የበመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌስቲቫል ውድድር ሶስተኛ ቀን መርሃ ግብር እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በቡብ ጨዋታ ሁለቱም ውድድሮች አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ዩ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ በሚገኘው የስፖርት ፌስቲቫል ዛሬ በተደረገው ቡብ ጨዋታ /ወንዶች/እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ድሬደዋ ዩኒቨርሲቲን 3 ለ 0 እንዲሁም ቡብ/ሴቶች/ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲን በተመሳሳይ 3 ለ 0 አሸንፏል።
በቡብ ጨዋታ ቀጣይ መርሀ ግብር ነገ ቀጥሎ ሲካሄድ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በወንዶች ከወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ሲገናኝ በሴቶች ከጎንደር ዩኒቨርስቲ ነገ 4 ሰዓት ይጫወታል።
በሌላ በኩል ዛሬ በተደረገ የወርልድ ቴኳንዶ ከ54 ኪሎ ግራም በታች ወንዶች ጨዋታ በመጀሪያው ዙር እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲን 2 ለ ባዶ ሲያሸንፍ በሁለተኛው ዙር በጅማ ዩኒቨርሲቲ 2 ለ1 ተሸንፏል።
በአትሌቲክስ ስፖርት እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ100 ሜትር 3 ስፖርተኞችን ያሳተፈ ሲሆን በመጀመሪያው ማጣሪያ ሁለቱ አትሌቶች ከየምድባቸው አማኑኤል ዋሴ 1ኛ እና ዮርዳኖስ ማሙሸት ሁለተኛ ሆነው ግማሽ ፍፃሜውን ቢቀላቀሉም በግማሽ ፍጻሜው አማኑኤል ዋሴ ሶስተኛ ዮርዳኖስ ማሙሸት 5ኛ በመውጣታቸው ለፍፃሜው ሳያልፉ ቀርተዋል።በሌላኛው ምድብ ማጣሪያ የተሳተፈው ታምራት አላምነህ የመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ ሶስተኛ በመውጣቱ ግማሽ ፍፃሜውን ሳይቀላቀል ቀርቷል።
ጥር 20/2017 ዓ.ም
ያለህን ዕምቅ አቅም ለይተህ ተጠቀም!