"ስነ ምግባር፣ ሙስናና መከላከያ መንገዶቹ" በሚል ርዕስ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሠጠ፡፡
----
የካቲት 10/2017ዓ.ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የስነ ምግባር መከታተያ ስራ አስፈጻሚ ከዩኒቨርሲቲው ጠቅላላ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ ጋር በመተባበር ለግቢ ውበትና አትክልት ልማት ሰራተኞች በስነ ምግባር ግንባታ እና በሙስና መከላከል ስትራቴጂዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና ሠጥቷል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የስነ ምግባር መከታተያ ስራ አስፈጻሚ ደሳላው ጌታሁን ስልጠናው ስነ ምግባር፣ ሙስናና መከላከያ መንገዶቹ ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸው የስነ ምግባር ችግር ለመልካም አስተዳደር እጦትና ለሙስና መንስኤ በመሆኑ እንደ ሀገር አሁን ላይ እየታዩ ላሉ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ከባቢያዊ ችግሮች ሁሉ ዋነኛ መንስኤያቸው የትውልድ የስነ ምግባር ጉደለት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ አቶ ደሳለው አክለውም ሰላምና መረጋጋት የሰፈነባት እና ለዜጎቿ ምቹ የሆነች ሀገር እንድትኖረን ከተፈለገ ሁሉም ዜጋ ለትውልድ ስነ ምግባር ግንባታ እና ለሙስና መከላከል ተግባራት ትኩረት መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡
በስልጠናው የዩኒቨርሲቲው ግቢ ውበትና አትክልት ልማት ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡