🤜🤛የክርክር አፀያፊነት እና ክፉ መዘዞቹ ⏲️
ክፍል ሶስት
[የመጨረሻው ክፍል]
http://t.me/islamic_Daiwa_Center/IDC
👉ይህንን ከማር የሚጣፍጥ የኢማሙ ኣጁሪ ንግግር እንመልከት…
✍"ዕውቀትና ንፁህ አዕምሮ ያለው የኾነ ሰው ከኪታቤ መጀመሪያ ጀምሮ እስከዚህ ድረስ የጠቀስኩለትን የመለየትና በእሱም የመስራት ግዴታ እንዳለበት ያውቃል። አላህ መልካም የፈለገለት ከኾነ የነብዩ ሱና፣ የሶሓቦች፣ የተከታዮቻቸውንና በሁሉም ዘመን የነበሩ መልካም የነበሩ የሙስሊም መሪዎችን ፈለግ ይከተላል።
ዕውቀት ሲማርም ከራሱ ላይ አላዋቂነትን ለማስወገድ ብሎ ይማራል፤ ሲማረው ለአላህ ብሎ ነው የሚማረው።
ሊጨቃጨቅበት፣ ሊከራከርበት፣ ዱንያን ሊሰበስብበት ብሎ አይማረውም። አላማውና ፍላጎቱ እንዲህ የኾነ ሰው በአላህ ፍቃድ ከቢድዐ ከጥመት የተጠበቀ ይኾናል።
የእነዝያ እነርሱ በሚወሱ ጊዜ ጭርታን የሚያስወግዱ የኾኑ የመልካም ቀደምቶቹን ፈለግ ይከተላል። አላህም ለዚህ ነገር እንዲገጥመው እማፀንለታለሁ።
አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ቢጠይቅ……
❓"አንድ ሰው አላህ ዕውቀትን አሳውቆታል። አንድ ሰውዬ ሀይማኖታዊ ከኾኑ ነጥቦች ሊጠይቀው፣ ሊጨቃጨቀውና ሊከራከረው ቢመጣ ይህ ሰውዬ በሰውየው ላይ ማስረጃ እስኪያረጋግጥበት ድረስ እንዲከራከረው ታይለታለህን?" ካለ እንዲህ ተብሎ ይመለስለታል…
✍የተከለከልነው እኮ ከእንደዚህ አይነቱን ነው። ቀደምት የኾኑ የሙስሊም መሪዎች (አስተማሪዎች) ያስጠነቀቁት ከእንደዚህ አይነቱን ነው።
❓"እና ምን ማድረግ አለበት?" ካለን … እንዲህ እንለዋለን
✍ይህ የሚጠይቅህ ሰውዬ ወደ ትክክለኛው መንገድ መመራት ፈልጎ የሚጠይቅ፣ ሐቅን የሚፈልግና ክርክርን የማይፈልግ ከኾነ ለስለስ ባለና ዕውቀታዊ በኾነ አነጋገር ከቁርኣን እና ከሐዲስ እየጠቀስክ አመላክተው። የሰሓቦችና የመልካም ቀደምቶች ንግግርም ጥቀስለት።
🔵ነገር ግን አንተን መጨቃጨቅ፣ መነታረክና መከራከር የሚፈልግ ከኾነ ዑለማዎች ላንተ የጠሉልህ ነገር ይህ ራሱ ነው። አትከራከረው። በዲንህም ላይ ተጠንቀቀው። ልክ መልካም የነበሩ መሪዎቻችን እንዳሉት በትክክል እነርሱን የምትከተል ከኾንክ።
❓"እና እንዲው በባጢላቸው ላይ እንደ ፈለጉ ይናገሩ፣ እኛ ዝምን ብለን እንተዋቸው እንዴ?" ካለን እንዲህ እንለዋለን
✍ለእነርሱ ፀጥ ብለህ ንቀህ መተውህ፣ የተናገሩትንም ነገር ጠልተህ መተውህ በእነርሱ ላይ እነርሱን ከመከራከርህ የበለጠ ብርቱ ነው።
መልካም የኾኑ ቀደምቶችና የሙስሊም መሪዎችም እንዲሁ ነበር ያሉት።
ንግግራቸውን ተመልከት
🔹አዩብ እንዲህ ይላል፦
📝"በእነርሱ ላይ ከዝምታዬ የበለጠ ብርቱ ምላሽ የለኝም"
🔸ኢብኑ ዐባስ እንዲህ ይላል፦
📝 "የስሜት ባለቤቶችን አትቀማመጡ፤ እነርሱን መቀማመጥ ልብን ያሳምማል"
🔹መህዲ ቢን መይሙን እንዲህ ይላል፦
📝"ሙሐመድ ኢብኑ ሲሪን እንዲህ ሲል ሰማሁት; አንድ ሰው ተከራከረውና እንዲህ አለው "እኔ ምን እንደ ምትፈልግ አቃለሁ, እኔም ደሞ ከአንተ የበለጠ ክርክር የምችል ሰው ነኝ, ነገር ግን አልከራከርህም""
🍅ጣፋጭ የኾነው የኣጁሪ ንግግር በድጋሚ እንመልከት🕶️
✍አንድ ጠያቂ እንዲህ ብሎ ቢጠይቀን …
❓"እንደው የኾነ አጋጣሚ ተከስቶ በጊዜው እንድከራከርና በሰዎቹ ላይ ማስረጃን እንዳረጋግጥ ብገደድ ልከራከራቸውን??"
እንዲህ ተብሎ ይመለስለታል……
✍መገደድ የሚከሰተውማ አንድ መሪ (መንግስት) ይኖርና ለዚህ መንግስት መጥፎ የኾነ እምነት (አመለካከት) ይኖረዋል፤ በዚህ መጥፎ እምነቱ ሰዎችን ይፈትንበታል፤ ወደ እምነቱም ይጠራቸዋል ነው። ልክ በኢማሙ አሕመድ ጊዜ እንደ ተከሰተው።
ሶስት መሪዎች እየተተካኩ ሰዎችን ፈተኑ፤ ወደ ብልሹ እምነታቸውም ጠሯቸው። በዚህ ጊዜ ዑለማዎች ለዲን ዘብ ከመቆም ቅሮት አላገኙም። ለህብረተሰቡ ሐቅን ከባጢል ለይተው ማሳወቅ ፈለጉ።
🔵በፍላጎታቸው ሳይኾን ግዴታ ኾኖባቸው ነው የተከራከሩት!!
አላህ ሐቅን ከኢማሙ አሕመድና አብረውት ከነበሩት ጋ እንደኾነ አረጋገጠ፤ ሙዕተዚላዎችን አላህ አዋረዳቸው አጋለጣቸው።
ማህበረሰቡንም ሐቅ ኢማሙ አሕመድ ባለበት መንገድ ላይ እንደኾነ ተገለፀለት።
አላህ አሕለል ሱና ወልጀማዎችን ሁሌም ከፊትና እንዲጠብቃቸው እማፀነዋለሁ‼‼
🔵ስለ ክርክር አፀያፊነት ይህንን ካየን በመጨረሻም የአላህ መልዕክተኛ ሱናን በመሀፈዝና በመስራት፣ የሰሓቦች፣ የታቢዒዮችና የመልካም ቀደምቶቻችን፣ የእነ ማሊክ፣ የእነ አውዛዒ፣ የእነ ሱፍያነ ሰውሪ፣ የእነ ኢብኑ ሙባረክ፣ የእነ ሻፊዒይ፣ የእነ ኢማሙ አሕመድ፣ እና የእነርሱን መንገድ ላይ በመፅናት አደራ እንላለን።
ከእነርሱ በተቃራ ያሉትን ችላ ብላችሁ ተዋቸው። አትከራከሯቸው፤ አትጨቃጨቋቸው።
🔴የቢድዐ ባለቤት መንገድ ላይ ካገኘኸው ሌላን መንገድ ይዘህ ሂድ‼
🔴የቢድዐ ባለቤት ባለበት መቀማመጫ ላይ ተጥደህ ከኾነም ተነስና ቦታ ቀይር‼
ቀደምቶቻችን በዚህ መልኩ ነው ስራዓት ያስያዙን።
🌱የሕያ ቢን አቢ ከሲር እንዲህ ይላል፦
📝"መንገድ ላይ የቢድዐ ባለቤት ከተገናኘህ መንገድህ ቀይር"
🌱አቡ ቂላባ እንዲህ ይላል፦
📝" የስሜት ባለቤቶች ጠማማዎች ናቸው፤ ጉዟቸውም ወደ እሳት እንደኾነ እንጂ አይታየኝም"
በሌላም ቦታ እንዲህ ይላል፦
📝"አንድንም ሰው ቢድዐን አይፈጥርም ሰይፍ (መገዳደልን) ሀላል ቢያደርግ እንጂ"
/የኣጁሪ ንግግር አበቃ/
🌴ውድ አንባቢዮቻችን
ዕውቀታቸው ከባህር የጠለቀ፣ አላህ የበላይነትን ያጎናፀፋቸው፣ ሲናገሩ ከአፋቸው ማር ጠብ የሚል የኾኑ የብርቅዬ ቀደምቶቻችን ንግግር በከፊሉ ለማየት ሞክረናል‼
🛣️መንገዳቸውን ለመከተል የወፈቀን አላህ ምስጋና ይድረሰው‼
🤲ፅናቱንም ይስጠን‼‼
የእነርሱን ንግግር አይተን የእኛን ሀሳብ እንጨምር ማለት የተገነባውን ማፍረስ ነውና ምንም ነገር መጨመር አንፈልግም።።
🤲አላህ
የሚጠቅመንን ያሳውቀን
ባወቅነው ያስጠቅመን አ ሚ ን‼
🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸
✍ሐምዱ ቋንጤ
♻️ 👉http://t.me/islamic_Daiwa_Center/IDC