🤜🤛
የክርክር አፀያፊነት እና ክፉ መዘዞቹ ⏲️
ክፍል ሁለት
http://t.me/islamic_Daiwa_Center/IDCبسم الله الرحمن الرحيم
✍በዛሬው ፅሁፋችን በአላህ ፍቃድ ኢማሙ ኣጁሪ ኪታቡ ላይ በጠቀሳቸው መሰረት መልካም ቀደምቶቻችን በዲን ላይ መከራከርና መጨቃጨቅን በተመለከተ የነበራቸው አቋምና የተናገሩት ንግግራቸውን የምናይ ይኾናል።
🤲አላህ ኢሕላስ እንዲወፍቀንና እንዲያግዘን በድጋሚ እንማፀነዋለን‼
📝አቡ ኡማማ የተባለው ሰሐብይ የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ ይላል፦
"ما ضل قوم بعد هدى كانوا عليه إلا أوتوا الجدل"
"ህዝቦች ቀጥተኛው መንገድ ላይ ከነበሩ በኋላ አይጠሙም ክርክርን ቢሰጡ (ተከራካሪ ቢኾኑ) እንጂ"
አስከትለውም ይህንን የቁርኣን አንቀፅ አነበቡ
{ مَا ضَرَبُوهُ لَكَ إِلَّا جَدَلًۢا ۚ بَلْ هُمْ قَوْمٌ خَصِمُونَ }
[ سورة الزخرف : ٥٨]
{ለክርክር እንጂ ለአንተ እሱ ምሳሌ አላደረጉልህም፤ በእውነት እነርሱ ብርቱ ተከራካሪዎች ናቸው}
[አል_ዙህሩፍ: 58]
🔵ታቢዒዮች እና ከእነርሱ በኋላ የመጡትንም የዕውቀት ባለቤት የኾኑ የሙስሊም መሪዎች (አስተማሪዎች) ይህንን የነብዩ ሙሐመድ ሐዲስ ሲሰሙ በእስልምና ላይ አልተጨቃጨቁም‼ አልተከራከሩም‼
ሙስሊሞችን ከጭቅጭቅ እና ከክርክር አስጠነቀቁ። ሱናን ብቻ አጥብቀው እንዲዙ አዘዟቸው። ሰሓቦችን የነበሩበት እንዲዙም መከሯቸው። ይህ ነው አላህ ለገጠመው ሰው የሐቅ ባለቤቶች መንገድ።
ለተናገርነው ነገር የሚያመላክት የኾነ ነገር በአላህ ፍቃድ እንደሚከተለው እንጠቅሳለን……
🔹ሙስሊም ቢን የሳር እንዲህ ይል ነበር፦
✍"ክርክርን ተጠንቀቁ ይቅርባችሁ። ምክንያቱም ዐሊም የነበረው ጃሂል የሚኾንበት ሰዓት ነው፤ ሸይጣንም ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሞ ስህተቱን ይከታተልበታል።"
🔸አቡ ቂላባ እንዲህ ይል ነበር፦
✍"የስሜት ባለቤቶችን አትቀማመጧቸው፤ አትከራከሯቸው፤ እኔ በጥመት ውስጥ እንዳይነክሯችሁ አልተማመንም። ወይንም ከዲናቸው የተለባበሰባቸው ከኾነ ነገር ከፊሉን እንዳያለባብሱባችሁ (እፈራለሁ)።"
🔹ሙዐዊያ ቢን ቁራ እንዲህ ይላል፦
✍"በዲን ላይ መጨቃጨቅ ስራን ውድቅ ታደርጋለች"
🔸ዑመር ቢን ዐብዱልዐዚዝ እንዲህ ይላል፦
✍"ዲኑን ለክርክር ግብ ያደረገ (አላማው መከራከር የኾነ) ሰው መገለባበጥ ያበዛል"
🔹መዒን ቢን ዒሳ (የኢማሙ ማሊክ ተማሪ) እንዲህ ይላል፦
✍"ከዕለታት አንድ ቀን ማሊክ እጄ ላይ ተደግፎኝ ከመስጂድ ወጣ። አቡ ጁወይሪያ የሚባል ሰው ተከተለው። ሰውየው በኢርጃ (የሙርጂአ ዐቂዳ ተከታይ እንደኾነ) ይጠረጠር ነበር። ለማሊክ አቡ "ዐብደላህ ሆይ" ብሎ ጠራውና
"ከእኔ የኾነ ነገር ስማኝና በዝያ ነገር ላናግርህ፣ ልከራከርህ። ራዕዬንም (አመለካከቴንም) ልንገርህ" አለው
ኢማሙ ማሊክ
"ካሸነፍከኝስ?" ሲለው
"ካሸነፍኩህማ ትከተለኛለህ" አለው
"እሺ ሌላ ሰው መጥቶ ቢከራከረንና ቢያሸንፈንስ?" ሲለው
"ካሸነፈንማ እንከተለዋለን" አለው።
በዚህ ጊዜ ኢማሙ ማሊክ
"አንተ የአላህ ባሪያ ሆይ, አላህ ሙሐመድን በአንድ ዲን ላይ ነው የላካቸው። አንተ ሳይህ ግን ከአንድ ዲን ወደ ሌላ ዲን የምትገለባበጥ ትመስለኛለህ።" አለውና የዑመር ቢን ዐብዱልዐዚዝ ቀጣዩን ንግግር አስታወሰው
"ዲኑን ለክርክር አላማ ያደረገ ሰው መገለባበጥ ያበዛል""
🔸ሂሻም ቢን ሓሳን እንዲህ ይላል፦
✍"አንድ ሰው ወደ ሐሰን መጣና "አቡ ሰዒድ ሆይ ና በዲን ልከራከርህ" አለው። ሐሰንም
"እኔ እንደኾነ ዲኔን አግኝቼዋለሁ (ይዤዋለሁ) አንተ ግን ዲንህን የጠፋብህ እንደኾነ ሂድና ፈልገው" አለው።
🔹ሓማድ ቢን ሙስዒዳ እንዲህ ይላል፦
✍"ዒምራን አልቀሲር እንዲህ ይል ነበር
"ጭቅጭቅ እና ንትርክን አስጠነቅቃቹሃለሁ። አደራችሁ እነዝያ "እንዲህ ቢኾን፣ እንዲህ ቢኾን" የሚሉ ተከራካሪዎችን ተጠንቀቋቸው።"
🔸ሰላም ቢን አቢ ሙጢዕ እንዲህ ይላል፦
✍"ከስሜት ባለቤቶች የኾነ አንድ ሰው ለአዩብ ሰህቲያኒ
"አቡ በክር ሆይ ስለ አንዲት ቃል ልጠይቅህ እንዴ?" አለው። አዩብም ፊቱን አዞረበትና በጣቱ ምልክት እያሳየው
"ግማሽ ንግግር እንኳ ብትኾን፣ ግማሽ ንግግር እንኳ ብትኾን እንዳትጠይቀኝ" አለው።"
🔹አስማዕ ቢን ሀሪጃ እንዲህ ይላል፦
✍"ሙሐመድ ኢብኑ ሲሪን ዘንድ ሁለት ከስሜት ባለቤት የኾኑ ሰዎች ገብተው "አቡ በክር ሆይ ሐዲስ እንንገርህ" ሲሉት
"አልፈልግም" አላቸው።
"እሺ ከአላህ ኪታብ ከቁርኣን አንድ አንቀፅ እናንብብልህ" አሉት
"አይኾንም ወይ እናንተ ውጡልኝ ካልኾነ ተነስቼ ልወጣ ነው" አላቸው።
🔸ዐብዱል ከሪም ጀዘሪ እንዲህ ይላል፦
✍"ዲኑ ላይ ጥንቁቅ የኾነ ሰው በጭራሽ አይከራከርም።"
🔹ዐምር ቢን ቀይስ እንዲህ ይላል፦
✍"ለሐኪም ሰዎች ወደ ስሜት ያስገባቸው ነገር ምንድን ነው? ብዬ ስጠይቀው
"ክርክር ነው" አለኝ።"
🔸መሐመድ ቢን ዋሲዕ እንዲህ ይላል፦
✍"ሰፍዋን ቢን ሚህረዝ ከመስጅዱ ጫፍ ላይ ኾነው የሚከራከሩ ሰዎችን አየና ልብሱን ሰብስቦ ተነሳ። ከዝያም ለተከራካሪዎቹ
"እናንተ በሽታ ናችሁ፣ እናንተ በሽታ ናችሁ ሲላቸው አየሁት።"
🔵ውድ አንባቢያን እነኚህ ከላይ የተዘረዘሩት እነዝያ ዕውቀታቸው ከባህር የሰፋ፣ አላህን በመፍራት ላይ ምሳሌ የሚደረጉ፣ ጠላት የሚምበረከክላቸው፣ ቢድዐን ተሸክሞ በሚመጣ ሰው ላይ እንደ አዳኝ አንበሳ ጀግናና አይበገሬ የነበሩ ብርቅዬ የሱና ፈርጦችና የዲን ምሁሮች ንግግር ነው።
እነርሱ ከነበራቸው ጥልቅ ዕውቀትና ድካ ከደረሰ አላህን መፍራት ጋ በዲናቸው ላይ መከራከርና መጨቃጨቅ ይህንን ያህል ከተፀየፉ፣ ከተጠነቀቁ እና ካስጠነቀቁ፤
እኛ ከዕውቀት ምንም የሌለን፣ ኢኽላሳችን የደከመ፣ ያለንበት ዘመን በወንጀልና በሹብሀ የተጥለቀለቀ በኾነበት ሁኔታ የያዝነውን ዲን ለክርክርና ለንትርክ የምናውለው ከኾነ መጥፋታችንና ፊትና ላይ መውደቃችን ሳይታለም የተፈታ ይኾናል።
በመኾኑም "ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ ..." ነውና አላህ መርጦ የሰጠን ተውሂድና ሱና ይዘን ከበሽተኞች የሚመጣውን የጭቅጭቅና የክርክር በር ዘግተን አላህን በመገዛትና ዲናችን በመማር ላይ መወጠር አለብን።
🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸
✍ሐምዱ ቋንጤ
♻️👉
http://t.me/islamic_Daiwa_Center/IDC