KABOD Teenagers


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha
Toifa: Din


📖  “በመካከላችሁ ሳለሁ ኢየሱስ ክርስቶስን ያውም የተሰቀለውን፣ እርሱን ብቻ እንጂ ሌላ እንዳላውቅ ወስኜ ነበርና።”
  — 1ኛ ቆሮንቶስ 2፥2 (አዲሱ መ.ት)
  

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


👋 እንዴት ናችሁ

ነገ ቅዳሜ 9፡00 ሰዕት teenage አለ እባካችሁን አታርፍዱ  እና ጓደኞቻችሁን ጋብዙ
        
                  ተባረኩ እንወዳችሁአለን 🤍


ሰላም ✋
በ አሁኑ አርብ ያነሳነውን ጥያቄ ለማስታወስ ያክል
1,አሁን ባላችሁበት ሕብረት የመንፈስ ቅዱስ አላማ እየተፈፀመ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ ?
                      አይመስለኝም ❗️
ምክንያቱም :- ሰፋ ያለ የፀሎት ሕብረትና ጊዜ   
                       ስለሌለን
                 -በእግዚአብሔር ፊት በጶምና
                     በአንድነት ልብ ስለማንቀርብ
                       
                      አዎ ይመስለኛል
ምክንያቱም:-በ እግዚያብሔር ፊት ሰፋ ያለ የፀሎት
                ሕይወትና ልምምድ ስላለን
                - በአንድ ልብ ሆነን የ እግዚአብሔር መንፈስ ስለምንፈልግ

👆በ እነዚህ ጉዳዮች ላይ ያወራን ሲሆን ሕብረታችን ሙሉና ለተሰበሰብንለት አላማ እንገኝ ዘንድ ትልቁና ወሳኙ ነገር በ ፀሎት የ እግዚያብሄርን ፈቃድና መንፈስ መፈለግ አለብን ብዬ አስባለሁ

በ ሙሉ ልባችን በአንድነት ልብ ወደ እግዚአብሔር ከቀረብን መንፈስ ቅዱስ በ እኛ ላይ ማይሰራበት ምክንያት የለም ብዬ አስባለሁ

📌 ስለዚህ በ አሁኑ አርብ 11:00 ላይ ሰፋ ያለ የፀሎት ግዜ ይኖረናል ስለዚህ በግላችሁም እየፀለያችሁ በጌታ ፊት ቆዩ
                 ተባረኩ እንወዳጅኋለን🧐🤍


👋እንዴት ናችሁ ካቦዶች


‼️የካቲት 22 የ ቅዳሜ ፕሮግራም

ወልድ በብሉይ ኪዳን በሚል ርዕስ ከ አብርሽ ጋር የትምህርት ጊዜ ነበረን

📌 ብሉይ ኪዳንን ለማንበብ ሞክረን ውጤታማ የማንሆነው ቀዳሚው ግባችን ህይወት የሆነውን ወልድን ማየት ሳይሆን ህይወትን( ለህይወት የሚጠቀሙ ነገሮች) ከመፈለግ ስለምንነሳ ነው።



      መነሻ ጥቅስ:  “እርሱም፣ “ስለዚህም የመንግሥተ ሰማይን ምስጢር የተረዳ ማንኛውም የኦሪት ሕግ መምህር፣ ከከበረ ሀብቱ ክምችት አዲሱንም አሮጌውንም የሚያወጣ ባለ ንብረት ይመስላል” አላቸው።”
ማቴዎስ 13:52



📌 ወልድ በብሉይኪዳን በምን ተገለጧል?
- ያህዌ፣ ጌታ

- የእግዚአብሔር መልአክ

- ቅዱሱ

- ልጁ



📌 ወልድ የአዲስ ኪዳን አዲስ ክስተት አይደለም

                     ተባረኩ እንወዳችዋለን 💛

@jtfgcyouth
@jtfgcyouth
#ወልድ_በብሉይኪዳን


👋 እንዴት ናችሁ

ነገ ቅዳሜ 9፡00 ሰዕት teenage አለ እባካችሁን አታርፍዱ  እና ጓደኞቻችሁን ጋብዙ
        
                  ተባረኩ እንወዳችሁአለን 🤍


ሰላም 🖐
በ አሁኑ ሳምንት አርብ ላይ ያነሳናቸውን ጥያቄዎች ለማስታወስ ያክል
1,በሕብረት ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ድርሻና ሚና ምንድነው
       ➡️የመጀመርያው ብለን ያነሳነው መንፈስ                           ቅዱስ ሕብረታችን ውስጥ ሲኖር ትልቁ
አላማው በ ሕብረታችን ውስጥ ክርስቶስን መግለጥ ነው።
       ➡️በሕብረታችን ውስጥ መዋደድን
       ➡️አንዱ ለሌላው ማሰብንና መኖርን

2,በሕብረት ውስጥ እኛ ሰዎች ምን ማድረግ አለብን?
       ➡️ትልቁ ነገር በሙሉ ልብ እግዚያብሄርን መፈለግ ነው
       ➡️ለ እግዚያብሔር መሸነፍ መንፈስ ቅዱስ እስከወደደ ድረስ በሕብረታችን ውስጥ እንዲሰራና የሱ ክብር እንዲገለጥ እኛ ምንም እንዳናዋጣና በራሳችን ምናረገው ነገር እንዳይኖር ሙሉ ለሙሉ የ ሕብረታችን ራስ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ማመን

          📌 የማሰላሰያ ጥያቄ
1,አሁን ባላችሁበት ሕብረት  የመንፈስ ቅዱስ አላማ እየተፈፀመ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?

2,ሕብረታችሁስ ምን ያክል በጌታ ፊት እየበረታ ነው?

3,አንዳችሁስ ለሌላችሁ የብርታት ምክንያት መ
ሆን ትችላላችሁ ?

4,ባላችሁበት ሕብረት ውስጥ ምን ይጎድላል ብላችሁ ታስባላችሁ? 

👆እነዚህን ጥያቄዎችን አስብባቸውና ቀጣይ እናወራቸዋለን ከዛ በተረፈ ደግሞ ያለ እግዚያብሔር ምንም ማድረግ እንደማንችል በማወቅ በቻልነው መጠን ወደጌታ እንቅረብ።

ነገ🙏 የፀሎት ጊዜ ይኖረናል ከ 11:00-12:00 ስዓት
        
              ተባረኩ እንወዳችኋለን 💛       


.
⭐ዘማሪ በረከት ለማ ⭐
እንደ ኢየሱስ
#ወልድ_ብሉይኪዳን


እንዴት ናችሁ ካቦዶች!!😀😀😀
እንግዲህ ቅዳሜ በነበረን የTeenage ፕሮግራም የተከነወኑ ነገሮችን እናጠቃልላለን ።
###. ስለ እየሱስ ማንነት በስፋትና በጥልቀት ያወራንበት ሳምንት ነበር!!!
###. ኢየሱስ ማን ነው??
###. የኢየሱስ ማንነት ላይ ምን ማንሳት እንችላለን??
👉👉👉 የኢየሱስ ማንነት ላይ የሚነሱ ብዙ ጥያቄዎች አሉ።!! እነሱን ከሰዎችና ከተለያዮ እምነቶች አንጻር ተመልክተናል።
👁️👁️ ማቴ 16፤13-16
       ማቴዎስ 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ።
¹⁴ እነርሱም፦ አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት።
¹⁵ እርሱም፦ እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው።
¹⁶ ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።
👀👀 ከዚህ ጥቅስ የምንረዳው ሰዎች በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ሰለ እየሱስ ክርስቶስ ማንነት ያልተመለሰላቸው ጥያቄዎች እንደነበርና እርሱንም ለመመለስ በዛ ያሉ መላምቶችን እንዳስቀመጡ ነወ።!!!
###. ሁለተኛው ነጥብ ደግሞ እየሱስ በተለያዮ እምነቶች/Beliefs እምነቶች የተሠጠው ቦታ ምን ነበር ???
የተለያዮ እመነቶች በተለያዮ ጊዜያት የተለያያ Assumption ይዘው እንደነበር አይተናል።
     🤔🤔🤔 ስለዚህ ለምንድነው አነድ አይነት መደምደሚያ ላይ መድረስ ያልቻሉት??
### እሱን ስንመልስ የኢየሱስ ክርሰቶስ ልጅነት ላይ ጥያቄ ይፈጥርብናል!!!
  በአጠቃላይ ለዚህ ጥያቄ ሁለት ጥቅሶችን ከመጽሐፍ ቅዱሳችን ለማየት ሞክረናል
1. ቆላ 1፤15-18
   ቆላስይስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵-¹⁶ እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው፤ የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤
¹⁷ እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል።
¹⁸ እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥ መጀመሪያ ከሙታንም በኵር ነው።
  2. ራዕይ 1፤8
“ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።”
   👀👀 ከእነዚህ ጥቅሶች ያጠቃለልነው
1. የኢየሱስን የልጅነት ታሪክ በሰውኛ ማወቅ እንደማንችል
2. እርሱ "አልፋና ኦሜጋ" ያለና የሚኖር ወደ ፈትም ደግሞ ሊወስደን የሚመጣ ሁሉንቻይ አምለክ እንደሆነ ተረድተናል።
     ⚠️⚠️⚠️ በዚህ ወር የምንወያያው
     "ወልድ በብሉይ ኪዳን" በሚል ርዕስ ሲሆን በብዛት ሰዎች ኢየሱሰስን ለማወቅ አዲስ ኪዳንን ብቻ ነው መጠቀም ያለብን የሚለውን misconception ለማጥራት የታሰበ ነው።
   ♨️♨️♨️ Task:
ወልድ በብሉይ ኪዳን involved ነው ብለን የምናስብበትን አንብበን ለቀጣይ ሳምንት  እንመጣለን።
            ተባረኩ ❤❤❤
#ወልድ_ብሉይኪዳን


👋 እንዴት ናችሁ

ነገ ቅዳሜ 9፡00 ሰዕት teenage አለ እባካችሁን አታርፍዱ  እና ጓደኞቻችሁን ጋብዙ
        
                  ተባረኩ እንወዳችሁአለን 🤍


👋 እንዴት ናችሁ
   
     የማሰላሲያ ጥያቄዎች

1. እምነት ማለት ምን ማለት ነው

2. መጸሃፍ ቅዱስ የህጻን ልጅ እምነት በሎ የሚጠራው ምን አይነት እምነት ነው

3. አዲስ ኪዳን ላይ ጻዲቅ ግን በእምነት ይኖራል ተብሎ  3 ጊዜ ተፅፉዋል ምን እያለን ነው

       ኮሜንት ላይ ሀሳባችሁን ንገሩን    

             ተባረኩ እንወዳችኋለን 🤍


ነገን ሳይ የሚታየኝ
ነገን ሳይ ምናፍቀው
በማግኘት በማጣት አልፌ
ራሴን ሳይ እግርህ ስር ሆኜ

እስከሞት ታምኜ
እስከሞት አምኜህ
ተራራ አምኜህ
ሸለቆም አምኜህ


አጥቻለሁ ብዬ እንዳልተውህ
ብኩርናዬ ሽጬ እንዳልክድህ
እንዳይበርድ ያንተ ፍቅር
እንዳይያያዝ ከምድር

አግኝቻለሁ ብዬ እንዳልተውህ
እንዳልታበይ እንዳልንቅህ
እንዳይበርድ ያንተ ፍቅር
እንዳይያያዝ ከምድር

ላይ እሻለው ፍትህን እያየሁ ስኖር
ላይ እሻለው በመቅደስህ ሳጥን ስኖር
ላይ እሻለሁ እርጅናዬ ባንተ ውስጥ ሆኜ
ላይ እሻለው ሽምግልናዬን በዘይት ለምልሞ

ላይ እሻለሁ Bereket Lemma

ተባረኩ በመዠሙሩ እንወዳችኃለን 🤍


👋 እንዴት ናችሁ
   
         ቅዳሜ የካቲት 8

      ይህን ወር ወደ ፊቱ መቅረብ ነበር

   # ስለ ወደ ፊቱ መቅረብ 2 ሰዎችን አይተን ነበር

1. ዳዊት ሲሆን እንደ ልቤ የተባለለት ነበር እናም ዳዊት ሀጥያት እየሰራም እግዚሀብሄር ፊት ይቀርብ ነበር

2. ጴጥሮስ ደሞ መንፈስ ቅዱስ ካገኘ በኃላ  3000 ሰዎች ጌታን ተቀብሎ ነበር እናም መንፈስ ቅዱስ ነው ድፍረት ምናገኘዉ ወደ ፊቱ ለመቅረብ

      ወደ ፊቱ ምንቀርብበት ፀጋውን ያብዛልን

      

             ተባረኩ እንወዳችኋለን 🤍


👋 እንዴት ናችሁ

ነገ ቅዳሜ 9፡00 ሰዕት teenage አለ እባካችሁን አታርፍዱ  እና ጓደኞቻችሁን ጋብዙ
        
                  ተባረኩ እንወዳችሁአለን 🤍


👋እንዴት ናችሁ

ነገ🙏 የፀሎት ጊዜ ይኖረናል ከ 11:00-12:00 ስዓት
        
              ተባረኩ እንወዳችኋለን 💛


ሚገባህን ሁሉ በፊትህ ላፍስሰው
ምንም ነገር የለም ላንተ የማልሰዋው
ያየሁት ምህረት ከ ቃላቴ በልጥዋል
መላው አካላቴ ክብር ይሰጥሀል
🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼🎼
ተባረኩ እንወዳችዋለን💛

@jtfgcyouth
@jtfgcyouth
#በፊቱ_መቅረብ


👋 እንዴት ናችሁ ካቦዶች

           ‼️የካቲት 1 የ ቅዳሜ ኘሮግራም
ወደ እግዚአብሔር መቅረብ በሚል ርዕሰ በ ወንድም ሳምሶን የ እ/ር ቃል ተካፋለን ነበር
   - ወደ ፊቱ ከምንቀርብበት መንገዶች አንዱ ፀሎት ነው
❓ፀሎት ምን ማለት ነው
ፀሎት ማለት: 1. የ አባት ና የ ልጅ ግንኙነት ነው
                     2. ከ እግዚአብሔር ጋር የምናደርገው ህብረት ነው
                     3. የ ህይወታችን ጉዳይ ነው
                     4. ለ እግዚአብሔር ምንገኝበት ነው
                     5. የ እምነታችን ውጤት ነው

አጋዝ ጥቅሶች( ዩሐ 1:13፣ ሮሜ 8:15፣ 1ተሰ 5:17 እና መዝ 89:20)


❓ለማን ነው ምንፀልየው
ለ እግዚአብሔር

ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ።”
  — ኢዮብ 42፥2

 
❓ለምን እንፀልያለን
- በ እራሣችን ምንም ማድረግ ስለማንችል

“እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።”
  — ዮሐንስ 15፥5


-በ እኛ ላይ ያለውን አላስፈላጊ ልምምድ እና ሀጥያት ስለሚያሶግድ

“ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል።”
  — ዮሐንስ 15፥2


ተባረኩ እንወዳችዋለን💛
@jtfgcyouth
@jtfgcyouth
#በፊቱ_መቅረብ


👋እንዴት ናቹህ ካቦዶች
  📌የዚህ ሳምንት የ ማሰላሰያ ሃሳብ( This week meditation 💡idea)

በ መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ በ እግዚአብሔር ፊት የ ቀረቡ ሰዎች እናገኛለን ከነዚህ መካከል በዚህ ሣምንት የምናነሳው ዳዊትን ነው። ይን ሰም በምንሰማበት ጊዜ የተለያዩ የ ዳዊት ታሪኮች ወደ አእምሮአችን ይመጣል አንዱም እግዚአብሔር ዳዊትን እንደ ልቤ የሆነው ሰው በማለት የተናገረው ነው
“እርሱንም ከሻረው በኋላ ዳዊትን በእነርሱ ላይ እንዲነግሥ አስነሣው፥ ሲመሰክርለትም፦ እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ አለ።”
  — ሐዋርያት 13፥22

"እንደ ልቤ" ሲባል የእግዚአብሔርን ሀሳብ በመረዳት በምንም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን ሁሌ በመታዘዝ መፈፀም ነው፤ ይህም የ ሚጀምረው በ እርሱ ፊት በመቅረብ ነው።  ዳዊት ገና ልጅ ሆኖ እረኛ በነበረበት ጊዜ እስከ ንግስናው ድረስ በተሰበረ ልብ እራሱን በእግዚአብሔር ፊት ያቀርብ ነበር። ይህ ሲባል" ዳዊት ፃድቅ፣ ሀጢያት የማያቀዉ እና ጥፋት ያላጠፋ ነው " ማለት ሳይሆን ለ ንሰሀም በፊቱ ይቀርብ ነበር።


➱ እኛም ከ እግዚአብሔር ጋር በማውራት(ፀሎት)፣ የእግዚአብሔርን ቃል በማጥናት አና ህብረት በማድረግ በፊቱ እንቅረብ🙏🙏
                    ተባረኩ እንወዳችዋለን💛



@jtfgcyouth
@jtfgcyouth
#በፊቱ_መቅረብ




ልቅረብ ወደ ፊትህ ትቼ ሁሉን ነገር
ቀኖቼም ይለፋ ሳወራ ካንተ ጋር
ማዶ አሻግሬ የሚባክነኝን
ከ እግሮችህ ስር ልዋል
እያደመጥኩ አንተን
አምላኬ..
🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
ተባረኩ እንወዳችዋለን💛
@jtfgcyouth
@jtfgcyouth

#በፊቱ_መቅረብ


👋እንዴት ናችሁ ካቦዶች

‼️ጥር 24 የ ቅዳሜ ፕሮግራም

በግብፅ ሀገር የተወለደ አንድ ሙሴ የተባለ ሰው ነበር።እርሱም ከጌታ ጋር እጅግ የጠበቀ ግንኙነት ነበራቸው ልክ ወዳጅ እንደሚያናግር ነበር ያወራው የነበረው።
ታዲያ ሙሴም በአንድ ወቅት ከሰፈር ትንሽ ራቅ ብሎ ትንሽዬ ቤት ተከለ ስሙንም “የመገናኛው ድንኩዋን”ብሎ ጠራው እዛም ማንም ጌታን ማናገር (መጠየቅ) የፈለገ ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኩዋን ይሄድ ነበር።እርሱም በገባ ጊዜ ከሰማይ ደመና ይወርድና ይከልለው ነበር።እንዲሁም ሙሴ በእያንዳንዱ እርምጃው ላይ እ/ርን እየጠየቀ ነበር ይሄድ የነበረው እናም እስራኤላውያንን ከግብፅ በሚያወጣ ጊዜ ቅድምያ እ/ርን ያማክር ነበር።በአንድ ወቅት ሙሴ ህዝቡን ባህር ከፍሎ ሲያሻግራቸው በቅድሚያ እ/ር አውረቶት ነበር።
         
ከላይ ያለውን 👆👆አጠር ያለ ታሪክ መሰረት በማድረግ

በነዚህ ጥያቄዎች 👇 👇

°እንዴት ወደ እ/ር እንቅረብ ወይም ወደ እርሱ ለመቅረብ ምን ማረግ አለብን?
◦ Devotion time (የጥሞና ሰአት) አሏችሁ ምን ምን ሰአት ነው?
◦ ጠይቃቹ (ነግራቹት) ከተደረገላቹ ነገሮች መካከል ቢያንስ 2 ጥቀሱ


📝summary's point( የ ማጠቃለያ ነጥቦች)
በ እግዚአብሔር ፊት ስንቀርብ:-
◆ እንደ እግዚአብሔር ቃል ማለትም በ ፅድቅ፣ በቅድስና ፣ እግዚአብሔርን በመፋራት፣ በተሰበረ ልብ እና በንስሐ መንፈስ
◆ በ ሙሉ እምነትና በ ማወቅ
◆ በ ሁኔታዎች መለዋወጥ ሣንሰናከል በ ትጋት ( ቢመችም ባይመችም) ለምሣሌ:- ዳንኤል / ፊቱ የመቅረብ ፍላጎቱ ከከበበው ሁኔታ በልጦ ነበር

➱ ሙሴ ራሱን ሰጥቶ እንደቀረበ እኛም እራሣችን ሰጥተን መቅረብ ይኖርብናል

ተባረኩ እንወዳችዋለን💛
#በፊቱ_መቅረብ
@jtfgcyouth
@jtfgcyouth


👋እንዴት ናችሁ ካቦዶች

በ አሁኑ ቅዳሜ ኘሮግራማችን ላይ እንዳወራነው ከመቼውም ጊዜ በላይ እራሳቸውን ቅዱስ እና ህያው መስዕዋት አድርጋችሁ የምታቀርቡበት፤ በ እግሮቹ ስር በመሆን እርሱን የምታቁበት፤ ሀሳቡ ፍቃዱን አላማውን የምትረዱበት፤ ምንም ሣንሰስት ያለን ብቻ ሳይሆን እራሣችውን(እናንተነታችሁን) የ ምታቀርቡበት እና በ መንፈሳዊ ህይወታቹ የምትጠነክሩበት ሰናይ ሳምንት ይሁንላችሁ!!
                                ተባረኩ እንወዳችዋለን💛
@jtfgcyouth
@jtfgcyouth
@jtfgcyouth

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.