🌹ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም🌹 dan repost
ተፈሲር ሱረቱ ኒሳዕ part 5
ሰዎች በገንዘብ ነክ ጉዳዮች እንዳይጋጩ የእያንዳንዱ ድርሻ ምን መሆን እንዳለበት ዲነል ኢስላም አስቀምጧል ፣ ከላይ የምእራፏ መጀመሪያ ላይ ስለ የቲሞች ይናገር ነበር .. ስለ መህርም ተናግሯል ፣ ውርሻ ላይ ወንድም ሴትም ባለድርሻ እንደሆኑ ተናግሯል ፣ ቀጥሎ ድርሻውን ወደ መመጠን ይገባል ..
يُوصِيكُمُ اللّهُ فِي أَوْلَادِكُمْ لِلذَّكَرِ مِثْلُ حَظِّ الاُنثَيَيْنِ
የአንቀፁን መጀመሪያ በጥልቀት ተመልከቱ «ዩሲኩሙሏሁ ፊአውላዲኩም» ይላል «አሏህ በልጆቻችሁ ጉዳይ አደራ ይላችኋል»። እንግዲህ ከወላጆች የበለጠ አሏህ አዛኝ ስለሆነ ወላጆች አደራ አስፈለጋቸው! “የልጆችን ነገር አደራ” ብሎ አርሀሙራሂሚን ጉዳዩን ወደሱ መለሰው።
አንድ ሰው ማግኜት ያለበት ከሚመለከተው ሸክምና ሀላፊነት አንፃር ነው ። በወጭ በኩል ሴቶች እንዳይጨነቁ ነው ያደረገው ሸርዑ ሙሉለሙሉ! ለዚህም አንዳንድ ኡለሞች “ማሉል መርአቲ ናሚን” ይላሉ (የሴት ገንዘብ በባህሪው መልማት ብቻ ነው) ካላባከነችው በስተቀር ፥ የራሷንም ወጭ ባሏ ነው መሸፈን ያለበት ። ስጦታም ብታገኝ ፣ ውርስም ብታገኝ ፣ በምንም መልኩ ብታገኝ የሷን ገንዘብ እሷ በፍቃዷ ካላወጣች በስተቀር ሙሉ ለሙሉ የወጭን ሀላፊነት ወንድ አንዲሸከም ነው አሏህ ያደረገው ። አባት ከዛ ባል ከሌሉም ወንድም እንዲወጣ ነው ያደረገው ። እሷ መከራ ማየት የለባትም .. አንተ አገልጋይ ነህ ኸድም ነው በአጭሩ ። ወንዱ ሲያገባ ግን ከፍሎ ነው ፡ ተከፍሎት አይደለም ። በትዳር ሲኖር ሁሉን ወጭ የሚሸፍነው እሱ ነው ፣ የሚሸፍንለት የለም ። ኢንፋቅ የሚባል ነገር እሱን ነው የሚመለከተው ። ይሄ ጠቅለል ያለ መንዙመተል ኢስላም ነው ።
አንድ ሰው ወራሽ መሆን የሚችለው ከሶስቱ አንዱ ውስጥ ከሆነ ነው ። አንደኛው መወለድ ነው ( ወላጅ ወይም ልጅ መሆን) ፣ ሌላኛው ጋብቻ ነው ፣ ሌላኛው ደግሞ ወላእ ነው ( ከባርነት ነፃ የወጣ ማለት ነው) ። የጀመረው ከልጅ ነው ፥ ብዙ ጊዜ ወላጆች ቀድመው ነው የሚሄዱትና አልፎ አልፎ ተቃራኒም አለ ግን ኖርማል ከሆነው ነገር ጀመረ ።
የዚህ አያ ሰበበ ኑዙል እንዲህ ነው ፦
ሰእድ ኢብኑ ረቢዕ የተባለ ሶሃቢይ ኡሁድ ላይ ሸሂድ ሆነ ፣ ሚስቱ ወደ ረሱል ﷺ መጥታ እነዚህ የሰዕድ 2 ሴት ልጆች ናቸው ፣ አጎታቸው መጥቶ ያለውን ገንዘብ ጥርግርግ አድርጎ ወሰደባቸው (ተመልከቱ የጃሂሊያን ሁኔታ እነዚህን የቲሞች መርዳት ሲገባው የወንድሜ ገንዘብ ነው ብሎ ለሚስቲቱም ሳያስቀር ወሰደ ) እንዴት ይደረግ ብላ ጠየቀች ። ረሱልም በዚህ ጉዳይ የሚፈርደው አሏህ ነው አሉ ፣ ይህ አያ ወረደ .. ፣ የአሏህ መልክተኛ ወደ ልጆቹ አጎት ለሰዕድ ልጆች 2/3ኛውን ስጥ ብለው ላኩበት ።
እንግዲህ ወራሾች ወንድና ሴት ልጆች ብቻ ከሆኑ 2/3 ኛው ለወንዱ 1/3ኛው ለሴት ስጡ ፣ ሁለትና ከሁለት በላይ ሴት ካለ ደግሞ 2/3 ኛው ለሴቶቹ ይሰጣቸዋል ፣ አንድ ሴት ብቻ ከሆነች ደግሞ ግማሽ ይሰጣታል አለና የልጆችን በዚህ ጨረሰ ።
ወላጆችና የጋብቻውን በቀጣይ እናየዋለን..!
https://t.me/+VUDQfAORZa43NDM0