❀━┅┉┈ወላሂ ገራሚ ቂሷ ናት┈┉┅━❀
አንድ ንጉስ ሁሌ በዙፋኑ ቁጭ ብሎ ብቸኛ ሴት ልጁን ለማን መዳር እንዳለበት ያስባል።
ከእለታ አንድ ቀን በማታ ሰዓት እላፊ ንጉሱ ይነሳና አማካሪውን እና ወታደሮችን አስከትሎ ወደ መስጅድ ያቀናል።
በዛ ሰዐት እንቅልፉን አሸንፎ ለይል የሚሰግድ
ወጣት ካለ ልጁን ሊድረው....
በጣም የሚገርመው ደሞ በዛ ሰዐት አንድ ጉደኛ ሌባ መስጅድ ሚዘረፍ ነገር ካለ ብሎ ግቢ ሲገባ በሩን ዝግ ያገኘውና ከላይ መስኮቷን መታ አድርጎ ይገባል።
ልክ ገብቶ በጭለማ ይዞ ሚወጣውን ሲያስስ
ድንገት የመስጅዱ በር ተበረገደ።
ጀለስ በቃ እሚሆነውን ሲያጣ እዛው ባለበት ቆሞ ሰላት አረመ /ውዱእ የለ፣ኒያ የለ....
በቃ ከነዚ ሰዎች ቢቻ ለመትረፍ ሰላቱን ጀመረው።
ንጉሱም፦"ሱብሀን አላህ ለሰላት ካለው ጉጉት የተነሳ በሩ ሲዘጋበት ከላይ ገብቷል!!! አጂብ" አለ። kkk...
ከዚያም ለወታደሮቹ ሰላቱን እስኪያጠናቅቅ እዛው ጠብቀው ቤተ መንግስት ድረስ እንዲያመጡት ትዕዛዝ ሰጥቶ ንጉሱ ተመለሰ።
ጀለስ ግን በቃ የፍራቻ ብዛት ልክ እንዳሰላመተ ወዲያው ሌላ ረክዓ ያርማል።
ይህን ሁኔታውን ያዩ ወታደሮች በግርምት ይመለከቱታል።
ከሰላቱ መርዘም የተነሳ መጠበቅ የሰለቻቸው ወታደሮችም ልጁ የጀመረውን ረክዓ እንዳጠናቀቀ ሊያስቆሙት ይወስኑና ልክ እንዳጠናቀቀ እጁን ይይዙታል።
ከዚያም ይዘውት ወደ ቤተ መንግስት ወሰዱት።
ወታደሮችም ለንጉሱ፦"የዒባዳው ጥንካሬ በጣም ይገርማል የሰላቱ ርዝመት አይወራም"
ብለው ሲነግሩት...
ንጉሱም ወደ ሌባው ዞሮ፦"አንተ በዚህ ኢማንህ ለዘመናት እፈልግህ የነበርክ ሰው ነህ ስለዚህ እንዲት ብቸኛ ልጄን እድርሀለሁ ስልጣንም እሰጥሀለሁ"አለው።
ሌባውም የሚሰማባቸውን ጆሮዎችን ማመን አቃተው ግራ በመጋባት አቀረቀረ።
አንገቱን በሀፍረት ደፋ'ና እንዲህ አለ፦"ያ አለህ!!! ከሰዎቹ ለማምለጥ ዝም ብዬ አስመስዬ በሰገድኩት ሰላት እንዲህ አይነት ከሆነ ስጦታህ.
አንተን በመፍራት ከልቤ ብስግድ ምን ይሆን ስጦህ!!!?"
by SA
For any comment⇣⇣
@OfficialAmharicbot
Join us⇣⇣
https://t.me/joinchat/AAAAAEJslpKJcGetAUsYfA ✔