🌿.......... ሐያእ.........🌿
ከሐያእ ማጣትመገለጫዎች መካከል በጥቂቱ፡-
☞ ዋልጌ ስድቦችና መጥፎ ቃላቶች መጠቀም
☞ የገቡትን ቃል ማፍረስ፤ የተናገሩትን ነገር መካድ
☞ አላህን ሳይፈሩ ሰውም ይታዘበኛል ሳይሉ በሀሰት መማል
☞ የሰውን ሐቅ መካድ፣ አለመመለስን አስቦ መበደር
☞ ከጣሪያ በላይ መሳቅ፣ መጮህ፣ እግር አንስቶ ጭምር
መንከትከት
☞ መንገድ ላይ መሽናት፣ በሚል ብልትን ይዞ
መዞር
☞ ጠቃሚና አስፈላጊ ያልሆነ ወሬ ማውራት፣ ሀሜት፣
ወሬዎችን ማመላለስ
☞ ሴት እህቶችን መላከፍ፣ ጥብቅ ሴቶችን በዝሙት ማነወር፣
መተንኮስና መሳደብ
☞ በተለይ ሴት ልጅን ለማታለል ሲባል በውስጥ የሌለን ነገር
መናገር፣ ላይፈጽሙ ቃል መግባት
☞በትዳር ላይ ክህደት፣ አግብተው አላገባሁም ማለት
☞ ሰውን በሰውነቱ ሳይሆን በሀብቱ ልክ ማክበር። ድሃን
አላውቀውም ሀብታምን ግን ዘመዴ ነው ማለት::
☞ ታላላቆችን አለማክበር፣ ኡስታዞችንና መሻኦኾችን ማነወር
☞ አለኝ ብሎ ሰውን መናቅ፣ መመፃደቅ፣ ራስን አለቅጥ
መካብ
☞ በየሄዱበት መቅለብለብ ከፊት ልታይ ልታይ ማለት
☞ ሰውን ማንጓጠጥ፣ እብሪተኝነት፣ ለመማታት መጋበዝ
☞ በደህና ጊዜ ያከበሩትን ሰው ሲደሀይ አሊያም ሲቸገር
ማዋረድ (መናቅ)
☞ የሰውን ንግግር አለማዳመጥ፣ ከሰው ጋር እያወሩ ሌላ ነገር
መስራት
☞ ከአጅነብይ ዐይንን አለመስበር፣ ሲያወሩም ፈታኝ የሆኑ
ቃላቶችን መጠቀም
☞ የሌሎችን ስራ ለማናናቅ ብሎ በጎንዮሽ የራስን ስራ
ማውራትና ማጋነን
☞ በአደባባይና በህዝብ መገልገያ ቦታዎች ላይ መትፋት፣
መናፈጥ
☞ በትዳር ካልተሳሰሯት ሴት ወይም ወንድ ጋር አላስፈላጊ ግንኙነት
መመስረት
☞ በትራንስፖርት ውስጥም ሆነ በሌሎች ቦታዎች ላይ
ሞባይል በሚያነጋግሩበት ጊዜ ለሰው ቁብ አለመስጠትና
ለሚያወሩት ነገር አለመጠንቀቅ
🍃አላህ ሐያእ ያልብሰን🍃
:¨·.·¨: ❀
·. ┈┈••◉❖◉●••┈,,
🔍
https://t.me/joinchat/AAAAAENeGQLfaU994fwAmw 📩📩........🍂🍂.......🌹🌹