TGStat
TGStat
Qidiruv uchun matnni kiriting
Ilg‘or kanal qidiruvi
  • flag Uzbek
    Sayt tili
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Saytga kirish
  • Katalog
    Kanal va guruhlar katalogi Kanallar qidiruvi
    Kanal/guruh qo‘shish
  • Reytinglar
    Kanallar reytingi Guruhlar reytingi Postlar reytingi
    Brendlar va shaxslar reytingi
  • Analitika
  • Postlarda qidiruv
  • Telegram'ni kuzatish
ETHIO BOOKS PDF

25 Sep, 09:48

Telegram'da ochish Ulashish Shikoyat qilish

ኀልዮ፦ ለአንተ የድርሰት ቅርጽ እንጀራን ጥሩ አምሳያ ኾኖ አግኝተኸዋል። እንዴት ነበር የተከሠተልህ?

አዳም :- ኹሉም 'ኦርጋኒክ' እና 'ኢንኦርጋኒክ' ነገሮች የተሠሩት ተመሳሳይ 'ሞለኪዉላር' መዋቅር ባ:ላቸዉ ነገሮች ነዉ። እንጀራም ያን ይመስላል። ሆላንድ ዉስጥ በነበርኩበት ጊዜ ፣ ለዐምስት ዓመታት ያኽል እንጀራ ሳልበላ ቆይቼ ነበር። እና ፣ አንድ ቀን ፣ እንጀራ ለመብላት ኼድኩ። ከዚያ ፣ ሳየዉ ፣ ዐዲስ ነገር ኾነብኝ። እና፣ ጥያቄ መጠየቅ ጀመርኩኝ፦ እንጀራ ከጥንት ጀምሮ የነበረዉ ለምንድ'ነው? እስከዛሬ ሰዎች ስለዚያ ባይጽፉም ፣ ያለ ማቋረጥ እስከዛሬ ድረስ ለምንድነ'ው ምግብ ያደረጉት? ምግብነት ብቻ ሳይኾን፣ የኾነ ነገርም አ:ለዉ፣ አልኩ። ከዚህ ጥርጣሬ ተነሣሁ'ና የእንጀራዉን ቅርጽ ማየት ጀመርኩ፤ ከ ጂኦሜትሪ አንጻር ዐየሁት። እንዲህ እያልኩ ስኼድ፣ ስለ የእንጀራ ታሪክም ማንበብ ጀመርኩ። የሚገርም ነበር። ከእግዚአብሔር ጋር ይገናኛል፣ ከጠቢባን ጋር ይገናኛል፣ ከ ጥንታዊ 'ሴክሬድ ጂኦሜትሪ' ጋር ይገናኛል። ስለዚህ ፣ እንጀራን 'ሜታፎር' ማድረግ ፈለግሁ። በእንጀራ ዉስጥ ያ:ለዉ መዋቅር ላይ ወጥ ስታፈስስበት፣ መረቁ በተለያዩ አቅጣጫዎች ነዉ የሚኼደዉ፣ እንጂ በ አንድ በ አንድ አቅጣጫ ከ ሀ ተነሥቶ ወደ ፐ አይደለም። እኔም የምጽፈዉ በዚህ መልኩ ነዉ።

ኀልዩ፦ እዚህ ኢትዮጵያ ዉስጥ አድናቂዎችኽ ብዙ ናቸዉ። እና አኹን ከመጣኽበት፣ እንበልና፣ አንዱ አድናቂህ በድንገት አግኝቶኽ፦ "አዳም ሆይ፣ አንተ እኮ የ ዐማርኛ ሥነ-ጽሑፍ ንጉሠ ነገሥት ኾነኻል!" ቢልኽ፣ ምላሽክ ምን ይኾን ነበር?

አዳም፦ እሸሻለሁዋ!
ኅልዩ፦ እ?
አዳም፦ 'እግሬ አዉጪኝ' እላለሁ!

ምንጭ :- በአጭሩ የተቀጨው መጽሔት 😀

@kooblife
    @kooblife
#Join & share

5.3k 0 3 25
Katalog
Kanal va guruhlar katalogi Kanallar to‘plamlari Kanallar qidiruvi Kanal/guruh qo‘shish
Reytinglar
Telegram-kanallar reytingi Telegram-guruhlar reytingi Postlar reytingi Brendlar va shaxslar reytingi
API
Statistika API'si Postlar qidiruvi API'si API Callback
Kanallarimiz
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
O‘qish
Академия TGStat Telegram tadqiqoti 2019 Telegram tadqiqoti 2021 Telegram tadqiqoti 2023
Kontaktlar
Справочный центр Qo‘llab-quvvatlash Email Vakansiyalar
Har xil narsalar
Foydalanuvchi shartnomasi Maxfiylik siyosati Ommaviy oferta
Botlarimiz
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot