የሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አክሲዮን ለማህበሩ ባዕድ ለሆነ ሰው ስለሚተላለፍበት ሁኔታ:-
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 154564 (ቅጽ 24፣ ገፅ 244) ስር የሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አክሲዮን ለማህበሩ ባዕድ ለሆነ ሰው ስለሚተላለፍበት ሁኔታ በሰጠው ፍርድ ላይ የአክሲዮን መተላለፍ ገዥ እና ሻጭን ለማስገደድ በጽሁፍ መደረግ ያለበት ሲሆን ማህበሩን ለማስገደድና የተላለፈለት ሰው በባለአክሲዮንነት ሙሉ መብት ለመጠቀም ስለአክሲዮን መተላለፋ ማህበርተኞች የተስማሙበት ውሳኔ በአክሲዮኖች መዝገብ ሊመዘገብ ይገባል:: እንዲሁም በሦስተኛ ወገኖች ላይ እንደመቃወሚያ ሊቀርብ የሚችለው የአክሲዮኖቹ መተላለፍ በንግድ ሚኒስቴር የንግድ መዝገብ ላይ ሲመዘገብ ነው:: ይህን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም አሁን ክርክር ባስነሱ አክሲዮኖች መተላለፍ ላይ የሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 103472 (ቅጽ 24፣ ገፅ 238) ስር በሰጠው ፍርድ ላይ ግልጽ አስገዳጅ የሆነ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል:: በማለት አስገዳጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል::
ይህንንም የሕግ ትርጉም ለመሥጠት መሠረት የተደረጉት በቀድሞው/በተሻረው የንግድ ሕግ/ኮድ አንቀጽ 522ና 523(3) ስር የተመለከቱት ድንጋጌዎች ሲሆን ይህ የህግ ትርጉም ከአዲሱ የንግድ ሕግ/ኮድ አንጻር ያለው አግባብነትና የተፈጻሚነት ወሰን መታየትና መፈተሸ ይኖርበታል::
By Zeray Weldesenbet the lawyer