የሰ/መ/ቁ/ 15531
የካቲት 6/1999
ዳኞች፡- አቶ መንበረጸሃይ ታደሰ
አቶ አሰግድ ጋሻው
አቶ መስፍን ዕቁበዩናስ
ወ/ት ሒሩት መለሰ
አቶ ተሻገር ገ/ሥላሴ
አመልካች፡- የኢት/ኤሌትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን
መ/ሰጭ፡- አቶ አዱኛ ገመዳ
የስራ ክርክር - የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ስልጣን - የወል የስራ ክርክር - የግል የስራ ክርክር - የሰ/መ/ቁ/ 18180፡፡
ተጠሪው ከደረጃዩ ዝቅ ተደርጌያለሁ ብለው በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ያቀረቡትን ክስ ቦርዱ የማየት ስልጣን አለው ሲሉ የምዕ/ ኦሮሚያ የአሰራና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡትን ውሳኔ በመቃወም የቀረበ አቤቱታ ነው፡፡
ውሳኔ፡- የምዕ/ ኦሮሚያ የአሰራና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡትን ውሳኔ ተሸሯል፡፡
1. የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የማየት ስልጣን የተሰጠው የወል የስራ ክርክር ጉዳዮችን ነው፡፡
2. አንድ የስራ ክርክር የወል የስራ ክርክር ነው የሚባለው ጉዳዩ የጋራ በሆነ የሰራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አሉታዊም ሆነ አወንታዊ ውጤት የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡
3. አንድ የስራ ክርክር የግል የስራ ክርክር ጉዳይ ነው የሚባለው የክርክሩ ውጤት በተከራካሪው ሰራተኛ (ሰራተኞች) ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀርብ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡
4. ከደረጃዩ ዝቅ ተደርጌያለሁ ተብሎ የሚቀርብ ክስ የጋራ በሆነ የሰራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አሉታዊም ሆነ አወንታዊ ውጤት የሚያስከትል አይደለም፡፡