የሰበር መ/ቁ 14057
ጥቅምት 30 ቀን 1998 ዓ.ም
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ ፍሰሀ ወርቅነህ
ወ/ሮ ስንዱ አለሙ
ወ/ሮ ሆሳዕና ነጋሽ
አቶ አሰግድ ጋሻው
አመልካች፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
ተጠሪ፡- አቶ ጌታሁን ኃይሉ
ስራ ክርክር - የዓመት እረፍት ክፍያ - የአዋጅ ቁጥር 42/85 አንቀጽ 79/2/ እና /5/፣ 77/5/፣ 77/3/
የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ መስርተው የ128 ቀናት የዓመት እረፍት በገንዘብ ተለውጦ እንዲሰጣቸው የጠየቁበመጀመሪያ ያየው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የተላለፈ የዓመት እረፍት ፈቃድ ከሁለት አመት በላይ መራዘም ስለሌለበት 128 የእረፍት ቀናት ተቀንሶ አዋጁ በሥራ ላይ ከዋለበት ጀምሮ ተጠሪ እስከተሰናበቱበት ድረስ የአንድ አመት ከአሥራ ሦስት ቀናት የዓመት እረፍት ክፍያ ብቻ ይከፈል በማለት ሊወሰን ጉዳዩን በይግባኝ ያየው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ደግሞ የተጠሪ ገንዘብ (የጠየቀው የአመት እረፍት) ሳይቀነስ ሊከፈል ይገባል በማለት በመወሰኑ የቀረበ አቤቱታ፡፡
ውሣኔ፡ - የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውና የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያሻሻለው ውሣኔ ተሻሽሏል፡፡
1. ከሁለት አመት በላይ የተራዘሙ ፈቃዶች በገንዘብ የሚተኩ አይደሉም፡፡
2. አንድ ሠራተኛ የሥራ ውሉ ሲቋረጥ ያልተጠቀመበት የዓመት ፈቃድ ክፍያ ሁሉ የጊዜ ገደብ ሳይኖረው በገንዘብ ተቀይሮ ሊከፈለው አይችልም፡፡