ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ
***
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል እንዲከላከሉ ብይን ሰጠ።
የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል)፣ አማኑኤል መውጫ፣ ናትናኤል ወንድወሰን፣ ኤልያስ ድሪባ፣ ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ ላይ በነሐሴ 16 ቀኔ 2016 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 3፡30 ሰዓት ላይ ከአበባ ከተማ ወደ መቐለ ከተማ ለመጓዝ አውሮፕላኑ ለበረራ ዝግጁ ቢሆንም የአየር ሁኔታ ለበረራ አዳጋች በመሆኑ በረራው ቢደረግ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ የሚያደርሰውን ከባድ አደጋ ለመከላከል ጉዞው ተሰርዞ መንገደኞች ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ሲነገራቸው በረራው በግድ መደረግ አለበት፤ አውሮፕላኑ ይከስከስ፤ አንወርድም በማለት ቀሪ ተሳፋሪዎችም እንዳይወርዱ በመክልከል አሳድመዋል በሚል በዝርዝር ጠቅሶ ክስ አቅርቦባቸው ነበር።
በተጨማሪም ዐቃቤ ሕግ 1ኛ ተከሳሽን ጆን ዳንኤል በተባለ ተከሳሽ ላይ በ3ኛ ክስ የኮምፒዩተር ወንጀል ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀጽ 13 ንዑስ ቁጥር 3 ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ መተላለፍ ቲክቶክ በተባለ ማሀበራዊ ሚዲያ በተንቀሳቃሽ ምስል ቀርጾ በቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ የሚል ክስ አቅርቦበት ነበር።
በዚህ መልኩ ተከሳሾቹ የክስ ዝርዝሩ ከደረሳቸው በኋላ ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት ከማረሚያ ቤት ቀርበው ጉዳያቸውን ተከታትለዋል።
ተከሳሾቹ "የወንጀል ድርጊቱን አልፈጸምንም" በማለት የዕምነት ክህደት ቃላቸውን በመስጠታቸው ዐቃቤ ሕግ ለወንጀሉ መፈጸም ያስረዱልኛል ያላቸውን ምስክሮች ቃል አሰምቷል።
ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ ዛሬ በዋለው የችሎት ቀጠሮ ሁሉም ተከሳሾች በ1ኛ ክስ ማለትም በወንጀል ህግ አንቀጽ 504 መሰረት እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል።
ሁለተኛውን ክስ በሚመለከት ፍሬ ነገሩ በአንደኛ ክስ ተጠቃሎ የተገለጸ በመሆኑ ተከሳሾቹን በሁለተኛ ክስ ነጻ በማለት በአንደኛው ክስ ብቻ እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል።
በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ጆን ዳንኤል የተባለው 1ኛ ተከሳሽን በተደራቢነት በቀረበበት በ3ኛ ክስ የኮምፒዩተር ወንጀል ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀጽ 13 ንዑስ ቁጥር 3 ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ መተላለፍ በሚለው ክስ እንዲከላከል ብይን ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ የተከሳሾቹን የመከላከያ ማስረጃ ለመጠባበቅ ለመጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጥሯል።
በታሪክ አዱኛ