መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ
አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ።”
ምሳ. 31፡29
ክርስቶስን ያከበሩ፤ መንገዱን የተከተሉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ እውነትን የመሰከሩ፤ ስለ ቃሉ የኖሩ ብዙ ሴቶች አሉ፤ መስዋዕትነትን የከፈሉ በሰማዕትነት ያለፉ ብዙ ሴቶች አሉ፤
ታላላቅ የምድር ነገስታትን፤ ታላላቅ ነቢያትን የወለዱ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ከእነዚህ ሁሉ ግን አንቺ ትበልጫለሽ።
ቅድስት ድንግል ሆይ አንቺ እኮ ሰማይ ዙፋኑ ምድር መረገጫው የሆነ፤ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የሰላም አለቃ፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ ከሆነውም አንዳችም እንኳን ያለርሱ ያልሆነ፤ ዓለምን ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት የመለሰ፤ መንበሩን የሚሸከሙ ኪሩቤልና ሱራፌል የሚንቀጠቀጡለት፤ የሁሉ ፈጣሪ፤ የሁሉ አምላክ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ነሽ።
በፊትም አሁንም ወደፊትም ካንቺ በቀር ፈጣሪዋን ልጄ ብላ የምትጠራ ሴት አልነበረችም፣ የለችም፣ አትኖርምም፤ ክርስቶስም እናቴ ብሎ የሚጠራት ብቸኛዋ ሴት አንቺ ነሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ።
እናት ስትሆኝ ድንግል፤ ድንግል ስትሆኝ እናት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ። ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ብሎ የሚጠራሽ ብቸኛዋ ሴት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ። እግዚአብሔር መርጦና ጠብቆ ያስቀረሽ ዘር በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ። ለዓለም ሁሉ ድኅነት ምልክት የሆንሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ።
እናቴ ሆይ እንግዲህ እኔ ምን ልናገር? ሺህ ቃላትን ብደረድር ያንቺን ክብር ልገልፀውስ እንደምን እችላለሁ? አዎ አሁንም እላለሁ “መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ።”
📖ምሳ. 31፡29
✍ ብፁዕ አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ
ቃለ ሕይወትን ያሰማን
🌹 የእግዚአብሔር ቸርነት 🌹
🌹 የእመቤታችን ጸሎት 🌹
🌹 የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃ🌹
🌹 የቅዱሳን ሁሉ በረከትና ረድኤት 🌹
ከሁላችን ጋራ ይሁን
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን