እልመስጦአግያ+++


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


"እልመስጦአግያ ብሂል ትምህርተ ኃቡአተ"
እልመስጦአግያ ማለት የተሠወረ ትምህርት
—— ማለት ነው
ጌታችን መድኃኒታችን ከትንሳኤው በኁዋላ በመጽሐፈ
…… ኪዳን ያስተማረው ትምህርት ነው ……
ያንብብዋ ምዕመናን እምቅድመ ቅዳሴ ንጹሕ ለዛቲ
ሃይማኖት እልመስጦአግያ
—— 《ሃይማኖተ አበው ምዕ ፪ ፥ ፩》——
#አማርኛ #ትግርኛ #ኦሮምኛ_ቋንቋ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri




ለማገዝ የምትፈልጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር

1000177318934 አበቅየለሽ አደባ


"ዘወትር በዐይንህ ፊት ፈሪሃ እግዚአብሔር ይኑር፤ ሕይወትና ሞት የሚሰጠውን አዘክረው፡፡ ዓለምንና በዓለም ያለውን ሁሉ ጥላው፤ ከሥጋ ብሔር ቃል የገባኸውን አትርሳ፤ ያም በፍርድ ቀን ካንተ ይፈለግብሃል፡፡ ረኀብን በጸጋ ተቀበለው፤ ተጠማ፥ ተራቆት፥ ንቁና በሐዘን የምትኖር ሁን፡፡ በልቡናህ አልቅስና ጩኽ፤ ለእግዚአብሔር የምትመች መሆን አለመሆንህን ፈትን፤ ሥጋህን ቀጥተህ ነፍስህን ታድናት ዘንድ፡፡”

✍ (አባ እንጦንስ


#ተወዳጁ_ልጅሽ_እንዲመግበኝ_ትለምኝልኝ_ዘንድ_እማጸንሻለሁ

እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። የመድኃኒት እናት ሆይ በመዓልትም በሌሊትም አማላጅ ትሆኝኝ ዘንድ እሰግድልሻለሁ። እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከእርሱ የሚገኘውን ኃይልን ይሰጠኝ ዘንድ ከአንቺ ወደ ተወለደው ልጂሽ እንድትለምኝልኝ እማጸናለሁ። በመወለዱ ድኅነት የተገባሽ ሆነሻልና። በሔዋን ውድቀት ሆነ። አብ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት ሰላምን የላከልሽ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። ሰላምታን ሰጠሽ ሰገደልሽም። ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ሰላምታ ይገባሻል። እነሆ ትጸንሻለሽ ልጅም ትወልጃለሽ፣ ስሙንም አማኑኤል ትይዋለሽ። የልዑል ኃይል ይጸልልሻል፤ ከአንቺ የሚወለደውም ቅዱስ ነው፤ እርሱም የልዑል ልጅ ይባላል አለሽ።

በተቀደሰው ስሙ ኅሊናዬን ልቡናዬን እንዲቀድስ ትለምኝው ዘንድ እማጸንሻለሁ። ንጽሕት ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። የሕይወት ቃል ከአንቺ ሰው ይሆን ዘንድ በሥጋ ከአንቺ ይወለድ ዘንድ የተገባሽ የመድኃኒት እናት እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። ከአንቺ በመዋሐዱም እኛ ዳንን። እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። በእናታቸው ማሕፀን ሕፃናትን የሚስላቸው ከአባቱ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም ሁሉን የፈጠረው በማሕፀንሽ የተቀረጸብሽ የብርሃን እናት ሆይ እሰግድልሻለሁ። ረቂቅ ድንቅ ምሥጢርን ዓለምንም ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣውን እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እለምንሻለሁ። በመንፈሳዊ ልደት ይወልደኝ ዘንድ ወደ እርሱ ዓለምና አዳኝ ወደ ሆነች ዕውቀት ከፍ ያደርገኝ ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እለምንሻለሁ፣ አማጸንሻለሁ።

የሕይወት መገኛ የነገሥታት ንጉሥ የባለሥልጣናቱ ባለሥልጣን የአምላኮችን አምላክ በበረት ያስተኛሽው እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። አዳኝ ስለሆነው ስለስምሽ እንዲረዳኝ ትለምኝልኝ ዘንድም ወደ አንቺ እለምናለሁ፤ እማልዳለሁም። በማየቱ አዳምንና ከእርሱ ጋር ያሉትን ሁሉ ነጻ ያወጣውን በክንድሽ የታቀፍሽው እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ።

በረቂቅ መመልከቱ እንዲመግበኝ ከሰይጣን መሰናክልም እንዲያድነኝ ትለምኝልኝ ዘንድ እለምንሻለሁ፤ እማጸንሽማለሁ። ዓለማትን ሁሉ ለሚመግበው ጡትሽን ያጠባሽው የመድኃኒት እናት እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ፤ የሰማይ ኃይላት የሚመገቡትም ከእርሱ ነው። ነፍሴን በፈቃዱ ከጸጋው ይመግባት ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እማጸንሻለሁ።

እመቤቴ ድግል ማርያም ሆይ ተወዳጁ ልጅሽ እንደ ፍጹም ፈቃዱ እንዲመግበኝ በየጊዜው በየሰዐቱ አማላጅ ሁኚኝ። ይህችም ወደ እርሱ የምትለምኝውን ልመና የተመላች መጽሐፍ ናት ። የለመንሁትን ሁሉ እርሱ ያደርግልሻልና። ኃጢአቴን ይቅር ይለኝ ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እማጸንሻለሁ። ሰላምን ስለሰጠሽ ስለ አብ ከአንቺ ስለተወለደው አንቺንም ስለተዋሐደው ከአንቺም ሰው ስለሆነው ስለወልድ፣ ስለቀደሰሽ፣ ከሦስቱ ቅዱስ ለአንዱ ማደሪያ ለመሆን እስከሚገባሽ ድረስ ስላነጻሽ ስለመንፈስቅዱስም እለምንሻለሁ። አገልጋይሽን ተወዳጁ ልጅሽ እንዲመግበኝ ትለምኝልኝ ዘንድ እማጸንሻለሁ። ለዘለዓለሙ አሜን።

#ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳርያ
(Deacon Birhanu Admass የተረጎመው)


"ባርነቴን ላንቺ በመስጠት ስሜን እንደጻፍሁ እንዲሁም የሰጠሁሽን የባርነቴን ደብዳቤ ጻፊ ልጅሽ በደሙ የዋጀኝ እኔን እንድጎዳ አትጣይኝ ልጅሽንም እንዲህ በይ ይህንን ጎስቋላ ባሪያ በክቡር ደምህ የገዛኸውን ስለ በደሉ ስለ ጉስቁልናው አትናቀው ገንዘቡን በወርቁ የገዛውን ለመጥላት  የሚችል የለምና።"

✍አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ


መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ
አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ።”
       ምሳ. 31፡29



ክርስቶስን ያከበሩ፤ መንገዱን የተከተሉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ እውነትን የመሰከሩ፤ ስለ ቃሉ
ኖሩ ብዙ ሴቶች አሉ፤ መስዋዕትነትን የከፈሉ በሰማዕትነት ያለፉ ብዙ ሴቶች አሉ፤
ታላላቅ የምድር ነገስታትን፤ ታላላቅ ነቢያትን የወለዱ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ከእነዚህ ሁሉ ግን አንቺ ትበልጫለሽ።

ቅድስት ድንግል ሆይ አንቺ እኮ ሰማይ ዙፋኑ ምድር መረገጫው የሆነ፤ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የሰላም አለቃ፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ ከሆነውም አንዳችም እንኳን ያለርሱ ያልሆነ፤ ዓለምን ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት የመለሰ፤ መንበሩን የሚሸከሙ ኪሩቤልና ሱራፌል የሚንቀጠቀጡለት፤ የሁሉ ፈጣሪ፤ የሁሉ አምላክ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ነሽ።

በፊትም አሁንም ወደፊትም ካንቺ በቀር ፈጣሪዋን ልጄ ብላ የምትጠራ ሴት አልነበረችም፣ የለችም፣ አትኖርምም፤ ክርስቶስም እናቴ ብሎ የሚጠራት ብቸኛዋ ሴት አንቺ ነሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ።

እናት ስትሆኝ ድንግል፤ ድንግል ስትሆኝ እናት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ። ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ብሎ የሚጠራሽ ብቸኛዋ ሴት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ። እግዚአብሔር መርጦና ጠብቆ ያስቀረሽ ዘር በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ። ለዓለም ሁሉ ድኅነት ምልክት የሆንሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ።

እናቴ ሆይ እንግዲህ እኔ ምን ልናገር? ሺህ ቃላትን ብደረድር ያንቺን ክብር ልገልፀውስ እንደምን እችላለሁ? አዎ አሁንም እላለሁ “መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ።”
📖ምሳ. 31፡29


      ✍ ብፁዕ አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ
       ቃለ ሕይወትን ያሰማን

   🌹   የእግዚአብሔር ቸርነት 🌹
   🌹 የእመቤታችን ጸሎት      🌹
   🌹 የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃ🌹
🌹 የቅዱሳን ሁሉ በረከትና ረድኤት 🌹
            ከሁላችን ጋራ ይሁን
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን
     


❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

❤ እንኳን #ለጾመ_ፍልሰታ_ለማርያም እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

                         ✝ ✝ ✝
❤ "#በጾም_ወበጸሎት_ወበምጽዋት ወበተፋቅሮ ይሰረይ ኃጢአት ይእዜኒ ወዘልፈኒ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም"። ትርጉም፦ #በጾምና_በጸሎት_በምጽዋት በመፋቀርም ኃጢአት ይወገዳል ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በጾመ_ድጓው_ላይ።

❤ ጾም ለአገራችን ኢትዮጵያና ለሕዝቧቿ ፍቅር፣ሰላም አንድነትን፤ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ለቅዱስ ሲኖዶስ አንድነት የሚያመጣ ያድርግል። በሰላም ጀምረን በሰላም ለመጨረስ ያብቃን ለሁላችንም የበረከት ጾም መልካም ሱባኤ ይሁንልን።

@Learn_with_John
@JohnDPT27




ፀሐይ ብርሃን ካልሰጠች ፀሐይ አትባልም፤ ብርሃን አለመስጠት ተፈጥሮዋ አይደለምና፡፡ እንስሳት ካልተነፈሱ እንስሳት አይባሉም፤ መተንፈስ ተፈጥሮአቸው ነውና፡፡ ዓሣ ከውኃ ከወጣ ሕይወት ያለው ዓሣ መኾኑ ይቀርና ይሞታል፡፡ አንድ ክርስቲያንም እውነተኛ ክርስቲያን የሚባለው፡-

#ሲጸልይ_ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት በወልድ ውሉድ በክርስቶስ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስም መንፈሳዊ መባል ነውና፡፡ ልጅ ከኾኑ ደግሞ አባትን ማናገር ክርስቲያናዊ ተፈጥሮ ነውና፡፡

#ሲያመሰግን_ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት እግዚአብሔር ፈጣሬ ዓለማት ነው ብሎ ማመን ነውና፡፡ ስለዚህ ለአንድ ክርስቲያን የሰማይና የምድር ውበት እየተመለከተ እግዚአብሔርን ማመስገኑ ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነው፡፡

#ሲመጸውት_ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት ሀብት ኹሉ ከእግዚአብሔር እንደ ኾነ መመስከር ነውና፡፡ ስለዚህ ራስን እንደ መልእክተኛ አድርጎ በመቁጠር ያለውን ለሌላው ማካፈል ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነውና፡፡

#ቅዱሳት_መጻሕፍትን_ሲያነብ_ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት በመንፈስ ቅዱስ ሀብት ደስ የሚሰኝ ነውና፡፡ይህን ለማድረግ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳት መጻሕፍት በኩል ሲናገር መስማት ለአንድ ክርስቲያን ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነውና፡፡

(ገብረ እግዚአብሔር ኪደ)

       ቃለ ሕይወትን ያሰማን

   🌹   የእግዚአብሔር ቸርነት 🌹
   🌹 የእመቤታችን ጸሎት      🌹
   🌹 የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃ🌹
🌹 የቅዱሳን ሁሉ በረከትና ረድኤት 🌹
            ከሁላችን ጋራ ይሁን
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን

    


የእለቱ መልእክት 📜
"+ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል:: ከሚስቱም ጋር ይተባበራል:: ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ:: ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው:: እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርትስቲያን እላለሁ:: ሆኖም ከእናንተ ደግሞ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደ ራሱ አድርጐ ይውደዳት:: ሚስቱም ባሏን ትፍራ:: +"+ (ኤፌ. 5:31)


💛

🕊     ቅ ዱ ስ   አ ማ ኑ ኤ ል     🕊

❝ ሰላም ለአስተርእዮቱ በሥጋ
ዘአስተርአየ ገሃድ ከመ የሀበነ ጸጋ ❞

[  በግልጽ ጸጋን ያድለን ዘንድ በሥጋ የተገለጠ ለኾነ ለእርሱ አገላለጥ ሰላምታ ይገባል ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

❝ ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል ፤ እነሆ ፥ ድንግል ትፀንሳለች ፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች ፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ❞

[ ኢሳ.፯፥፲፬ ]

" Therefore the Lord himself shall give you a sign; Behold, a virgin shall conceive, and bear a son, and shall call his name Immanuel."

[ Isaiah 7:14 ]


መልካም እለተ ሰንበት✨


"እግዚአብሔርን "ለምን ትረሳኛለህ?" አትበለው "ጌታ ሆይ የረሳሁህን እኔን ይቅርበለኝ፤ ፍቅርህን  ዘንግቻለሁና በመከራዬ ጊዜም አስበኝ" በለው እንጂ።"


#አቡነ_ሽኖዳ_ሳልሳዊ
       ቃለ ሕይወትን ያሰማን

   🌹   የእግዚአብሔር ቸርነት 🌹
   🌹 የእመቤታችን ጸሎት      🌹
   🌹 የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃ🌹
🌹 የቅዱሳን ሁሉ በረከትና ረድኤት 🌹
            ከሁላችን ጋራ ይሁን
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን

    


የእለቱ መልዕክት
"እኔ ሕያው ነኝና ኃጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኃጢአተኛው ይሞት ዘንድ አልፈቅድም" ይላል ጌታ እግዚአብሔር:: "የእሥራኤል ቤት ሆይ! ተመለሱ:: ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ:: ስለ ምንስ ትሞታላችሁ?" በላቸው:: (ሕዝ. 33:11)


❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

                           ✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለሴት_ተክለ_አቤል_ርእሰ_አበው። ተዘከረኒ እግዚኦ በምረትከ በእንተ ሴት ገብርከ ዘዓቀበ ትእዛዘከ ሕገከ ወሥርዓተከ፣ መሐረኒ በእንቲኣሁ ወአድኅነኒ እምሲኦል መሪር ለገብርከ አሜን"። ትርጉም፦ #የአባቶች_ራስ_ለኾነ_ለአቤል_ምትክ #ለሴት_ሰላምታ_ይገባል፤ አቤቱ ትእዛዝኽን ሕግኽንና ሥርዐትኽን የጠበቀ ስለኾነ ስለ አገልጋይኽ ስለ ሴት በምሕረትኽ ዐስበኝ፤ ስለ ርሱ ብለኽ ማረኝ፤ ከመሪር ሲኦል እኔን አገልጋይኽን አድነኝ፤ አሜን። #ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በተአምኆ_ቅዱሳን_ላይ።

@JohnDPT27


ጭንቀት ~ምን ያህል ከአምላክ መንፈስ እንደራቅን የሚጠቁም ስሜት ነው::

ሰላም ~ ምን ያህል ወደ አምላክ መንፈስ እንደቀረብን የሚናገር ስሜት ነው::

ከፈጠረን አምላክ አስበልጠን ሌላ ነገር ስንፈልግ በውስጣችን ጭንቀት ይፈጠራል::በልባችን ፍርሃት እና ውጥረት ያድራል::

ከሁሉም ነገር አብልጠን የአምላክን መንፈስ ስንፈልግ ሰላም በውስጣችን ይወለዳል::ልባችን በፍቅር እና በደስታ ይሞላል::

ዓለም እና ነገሮቿን ሁሌም ከእኛ ጋር ማድረግ አንችልም::ሰው ..ገንዘብ …ስልጣን ….ዝና እና ወ.ዘ.ተ ምንም ጊዚያዊ ደስታን ቢሰጡም ቶሎቶሎ የመቀያየር ጠባይ አላቸው::ያዝናቸው ስንል ይሄዳሉ::

የማይሄደው እና ምንጊዜም በልባችን የሚኖረው እኛንም እስከመጨረሻ የሚወደን ቅዱሱ የእግዚአብሄር መንፈስ ብቻ ነው::

ገንዘብ ብናገኝ ብናጣ ~ሰው ቢፈልገን ባይፈልገን ~
ጤና ቢኖረን ባይኖረን በቅፅበት በሚለዋወጠው አለም ሁሌም የማይቀያየር አምላካችን ብቻ ነው::

ይህንን አምላክ ከዓለም ያስቀደሙ አለምን ያሸንፋሉ::ለከንቱ ምኞት ውድ ነፍሳቸውን አይሰጡም::በጊዜያዊ ደስታ ዘለዓለማዊውን አምላክ አይለውጡም::
በሚለዋወጠው ዓለም የማይለዋወጥ ግንኙነት ከአምላክ ጋር አድርገዋል::ከጊዚያዊው አብልጠው ዘለዓለማዊውን መርጠዋል::

እርሱ የእውነት መታመን የሚቻልበት ወዳጃቸው ነው::ጥበብ ~ፍቅር ~ሀይል ~ስልጣን ~በረከት ~ሀብት እና ሁሉም ነገር አለው::

ወደዚህ መልካም አምላክ ስንቀርብ እርሱም ወደ እኛ ይቀርባል::ሰላሙንም በልባችን ያኖራል::ጭንቀት እና ፍርሃታችን ይወገዳል::

       ቃለ ሕይወትን ያሰማን

   🌹   የእግዚአብሔር ቸርነት 🌹
   🌹 የእመቤታችን ጸሎት      🌹
   🌹 የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃ🌹
🌹 የቅዱሳን ሁሉ በረከትና ረድኤት 🌹
            ከሁላችን ጋራ ይሁን
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን
ደህና እደሩ ተወዳጆች


እለታዊ መልዕክት
"+ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያናሩታል:: በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል:: መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ:: +"+ (ማቴ. 5:13-16)


                          †                          

   [   🕊  ቅ ዱ ስ    ዮ ሴ ፍ   🕊   ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

🕊  †  ፃድቁ_አረጋዊ_ዮሴፍ  †   🕊

እንኳን አደረሰን !

በዓለ ዕረፍቱ ለፃድቁ አረጋዊ ዮሴፍ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት በዚህች ዕለት መልካም ሽምግልና የነበረው የእመቤታችን የድንግል ማርያም ጠባቂ ድካሟን ለመሳተፍ ፣ ክብር ይግባውና ለጌታችንም አሳዳጊው ለመሆኑ የተገባው ፃድቁ አባታችን ቅዱስ ዮሴፍ አረፈ።

በአረፈበትም ጊዜ ጌታችን ወደ እርሱ መጥቶ እጆቹን በላዩ ላይ ጫነ ለሥጋውም መፍረስና መበስበስ እንዳያገኘው ኃይልን ሰጠው በአባቱ በያዕቆብም መቃብር አኖሩትየዘረ አዳምን አደራ ለመቀበል የተመረጠ ልዩ አባት ቅዱስ ዮሴፍ በረከቱ ይድረሰን።

መልአከ እግዚአብሔር እያነጋገረው እርሱ ግን በዝምታ የኖረ ታላቅ ቅዱስ ነው እመቤታችንን ለመጠበቅ ሦስት ተአምራት የተመለከተለት ብቸኛ አባት የድኅነታችን የምስጢር ሙዳይ ድንግል ማርያምን ለመቀበል የተመረጠ ክቡር ቅዱስ የሆነ በእርግና ዘመኑ ስለ ክርስቶስ መከራን የተቀበለ የሃይማኖት አርበኛ

ከእመቤታችን ቀጥሎ ጌታችንን ተንከባክቦ በማሳደጉ አባቱ ተብሎ እስከመጠራት የደረሰ ልዩ ነው። የእርሱን ያኽል ጌታውን በእጁ የዳሰሰ በትከሻው የተሸከመ አይገኝም።

🕊

የአረጋዊው የቅዱስ ዮሴፍ ምልጃና ጸሎቱ ከዘለዓለም እሳት ያድነን:: ጸጋ በረከቱ ይክፈለን::

🍒

†                       †                       †
💖                    🕊                    💖


#በስድብ_ፈንታ_አመስግኑ

ብዙ ጊዜ ስንሳደብ እና መጥፎ ቋንቋ ስንጠቀም “እኔ ይህን አለማድረግ አልችልም ልማዴ ነው" እንላለን፡፡ እናም ሲጎዱን አንድ ነገር መናገር ካለብንም፣ በስድብ ፈንታ ምስጋና መናገርን እራሳችንን እናስተምር።

ነገር ግን፣ ሰው እያሰቃየኝ ዝም ማለት አልችልም ትላለህ፡፡ ከመናገርምጨ ጨጠ  ዠዠ አልከለክልህም፡፡ ሆኖም ከመሳደብ ይልቅ ምስጋናን ተናገር፡፡ ከመበሳጨት ይልቅ ምስጋናህን ግለጽ፡፡

ለጌታህ መናዘዝ ትችላለህ፡፡ በጸሎትህ ውስጥ ጩኽ፤ እንዲሁ መከራህን ያቀልልሃል፣ ፈታኙም ሰይጣን በምስጋናህ ውስጥ ይሸሻል፣ የእግዚአብሔርም እርዳታ ወዳንተ ይቀርባል።

ከተሳደብክ፣ የእግዚአብሔርን ስጦታ ትከለክላለህ፤ እናም ፈታኙ በአንተ ላይ እንዲበረታ ታደርጋለህ፤ በዚያም እራስህን የበለጠ በህመም ውስጥ ታስገባለህ፡፡ ብታመስግን ግን የክፉ መንፈስን ጥቃት ትቃወማለህ፡፡

ነገር ግን ምላስ ብዙውን ጊዜ በልማድ ኃይል አንዳንድ መጥፎ ቃላትን ከመናገር ወደኋላ ማለት አይችልም:: ከዚያም በምትወድቅበት ጊዜ ኹሉ ቃሉ ከመናገርህ በፊት ጥርሶችህን ጠብቀው ይዘጉ፡፡ ምላስህ የደም ጠብታ ብታፈስስ ይሻላታል ፤ ከስድብም በኋላ የማያቋርጥ ቅጣት ከምትቀበል በጊዜው ሥቃይን ብትታገሥ ይሻልሃልና፡፡

(
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #የነፍስ_ምግብ #በፍሉይ_ዓለም_የተተረጎመ)
       ቃለ ሕይወትን ያሰማን

   🌹   የእግዚአብሔር ቸርነት 🌹
   🌹 የእመቤታችን ጸሎት      🌹
            ከሁላችን ጋራ ይሁን
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን
ደህና እደሩ ተወዳጆች
    


እለታዊ መልዕክት📜
=>+"+ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ: ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን:: +"+ (ዕብ. 6:10-13

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

567

obunachilar
Kanal statistikasi