#ተወዳጁ_ልጅሽ_እንዲመግበኝ_ትለምኝልኝ_ዘንድ_እማጸንሻለሁ
እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። የመድኃኒት እናት ሆይ በመዓልትም በሌሊትም አማላጅ ትሆኝኝ ዘንድ እሰግድልሻለሁ። እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከእርሱ የሚገኘውን ኃይልን ይሰጠኝ ዘንድ ከአንቺ ወደ ተወለደው ልጂሽ እንድትለምኝልኝ እማጸናለሁ። በመወለዱ ድኅነት የተገባሽ ሆነሻልና። በሔዋን ውድቀት ሆነ። አብ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት ሰላምን የላከልሽ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። ሰላምታን ሰጠሽ ሰገደልሽም። ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ሰላምታ ይገባሻል። እነሆ ትጸንሻለሽ ልጅም ትወልጃለሽ፣ ስሙንም አማኑኤል ትይዋለሽ። የልዑል ኃይል ይጸልልሻል፤ ከአንቺ የሚወለደውም ቅዱስ ነው፤ እርሱም የልዑል ልጅ ይባላል አለሽ።
በተቀደሰው ስሙ ኅሊናዬን ልቡናዬን እንዲቀድስ ትለምኝው ዘንድ እማጸንሻለሁ። ንጽሕት ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። የሕይወት ቃል ከአንቺ ሰው ይሆን ዘንድ በሥጋ ከአንቺ ይወለድ ዘንድ የተገባሽ የመድኃኒት እናት እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። ከአንቺ በመዋሐዱም እኛ ዳንን። እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። በእናታቸው ማሕፀን ሕፃናትን የሚስላቸው ከአባቱ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም ሁሉን የፈጠረው በማሕፀንሽ የተቀረጸብሽ የብርሃን እናት ሆይ እሰግድልሻለሁ። ረቂቅ ድንቅ ምሥጢርን ዓለምንም ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣውን እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እለምንሻለሁ። በመንፈሳዊ ልደት ይወልደኝ ዘንድ ወደ እርሱ ዓለምና አዳኝ ወደ ሆነች ዕውቀት ከፍ ያደርገኝ ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እለምንሻለሁ፣ አማጸንሻለሁ።
የሕይወት መገኛ የነገሥታት ንጉሥ የባለሥልጣናቱ ባለሥልጣን የአምላኮችን አምላክ በበረት ያስተኛሽው እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። አዳኝ ስለሆነው ስለስምሽ እንዲረዳኝ ትለምኝልኝ ዘንድም ወደ አንቺ እለምናለሁ፤ እማልዳለሁም። በማየቱ አዳምንና ከእርሱ ጋር ያሉትን ሁሉ ነጻ ያወጣውን በክንድሽ የታቀፍሽው እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ።
በረቂቅ መመልከቱ እንዲመግበኝ ከሰይጣን መሰናክልም እንዲያድነኝ ትለምኝልኝ ዘንድ እለምንሻለሁ፤ እማጸንሽማለሁ። ዓለማትን ሁሉ ለሚመግበው ጡትሽን ያጠባሽው የመድኃኒት እናት እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ፤ የሰማይ ኃይላት የሚመገቡትም ከእርሱ ነው። ነፍሴን በፈቃዱ ከጸጋው ይመግባት ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እማጸንሻለሁ።
እመቤቴ ድግል ማርያም ሆይ ተወዳጁ ልጅሽ እንደ ፍጹም ፈቃዱ እንዲመግበኝ በየጊዜው በየሰዐቱ አማላጅ ሁኚኝ። ይህችም ወደ እርሱ የምትለምኝውን ልመና የተመላች መጽሐፍ ናት ። የለመንሁትን ሁሉ እርሱ ያደርግልሻልና። ኃጢአቴን ይቅር ይለኝ ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እማጸንሻለሁ። ሰላምን ስለሰጠሽ ስለ አብ ከአንቺ ስለተወለደው አንቺንም ስለተዋሐደው ከአንቺም ሰው ስለሆነው ስለወልድ፣ ስለቀደሰሽ፣ ከሦስቱ ቅዱስ ለአንዱ ማደሪያ ለመሆን እስከሚገባሽ ድረስ ስላነጻሽ ስለመንፈስቅዱስም እለምንሻለሁ። አገልጋይሽን ተወዳጁ ልጅሽ እንዲመግበኝ ትለምኝልኝ ዘንድ እማጸንሻለሁ። ለዘለዓለሙ አሜን።
#ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳርያ
(Deacon Birhanu Admass የተረጎመው)