አላህ ወክበር ☪☪☪(አሀድ ሐበሽዬ)
ብሌ ቢላል ሳይጨርስ ካንደበቱ
በረካው ጎረፈ ቢያምር ድምፀቱ
ነጮች በሞሉበት ጥቁር በሚንቁት
ከፊታቸው ቆሞ ባሜት በሚደቁት
ተህሚዱን ቢያቀርብ ለጌታው ምስጋና
አለም አጨበጨበ እንዲሆን ገናና
አይ ቢላልዋ( *2)
የኔ መረዋ
የኔማ የኔ ነህ ለዛውም ሀበሻ
በአዛንህ አስከበርከኝ እንዳልነበርኩ ውሻ
የኔማ የኔ ነህ የልቤ ላይ ጀግና
ከነጮቹ ቀድመህ ያረከኝ ሳተና
የኔማ የኔ ነህ የእኔው ማንንት
ህመም የሚያስታግስ የድምፅህ ውበት።
አይ ቢላልዋ
የኔ መረዋ
አሀድ(*2)
ድምፅህ አለ በፍጥረታት ኡዙን
አስመልጠኸን አንዴ ፍጥረታት ላይዙን
ምነኛ ጠንካራ ብትሆን ልበ ሙሉ
በፍቅር ያሸነፍክ መምጫህ ቢጠሉ
ስጋህን ቢታሉ
ድንቅ ነህ ልዩ ከሳባዎች መኃል
ከጥበብህ ደርሶ ማንስ ያክልሀል
አይ ቢላልዋ የኔ መረዋ
አንተ ተላክላት ሀገሬ በተራዋ
በልማ ውጣና ከመድረኩ ደፍ
ነብዩ መሀመድ በዜማ ይክነፍ
የኔም ትታደስ ፍራሽ ነብስያዬ
ዝንት አለም ዘላለም ልባል ሐበሽዬ።
መልካም ፆም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች🙏🙏
✍️αвєℓ тαує
ብሌ ቢላል ሳይጨርስ ካንደበቱ
በረካው ጎረፈ ቢያምር ድምፀቱ
ነጮች በሞሉበት ጥቁር በሚንቁት
ከፊታቸው ቆሞ ባሜት በሚደቁት
ተህሚዱን ቢያቀርብ ለጌታው ምስጋና
አለም አጨበጨበ እንዲሆን ገናና
አይ ቢላልዋ( *2)
የኔ መረዋ
የኔማ የኔ ነህ ለዛውም ሀበሻ
በአዛንህ አስከበርከኝ እንዳልነበርኩ ውሻ
የኔማ የኔ ነህ የልቤ ላይ ጀግና
ከነጮቹ ቀድመህ ያረከኝ ሳተና
የኔማ የኔ ነህ የእኔው ማንንት
ህመም የሚያስታግስ የድምፅህ ውበት።
አይ ቢላልዋ
የኔ መረዋ
አሀድ(*2)
ድምፅህ አለ በፍጥረታት ኡዙን
አስመልጠኸን አንዴ ፍጥረታት ላይዙን
ምነኛ ጠንካራ ብትሆን ልበ ሙሉ
በፍቅር ያሸነፍክ መምጫህ ቢጠሉ
ስጋህን ቢታሉ
ድንቅ ነህ ልዩ ከሳባዎች መኃል
ከጥበብህ ደርሶ ማንስ ያክልሀል
አይ ቢላልዋ የኔ መረዋ
አንተ ተላክላት ሀገሬ በተራዋ
በልማ ውጣና ከመድረኩ ደፍ
ነብዩ መሀመድ በዜማ ይክነፍ
የኔም ትታደስ ፍራሽ ነብስያዬ
ዝንት አለም ዘላለም ልባል ሐበሽዬ።
መልካም ፆም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች🙏🙏
✍️αвєℓ тαує