በአሜሪካን ሀገር በሳን ሆዜ ከተማ አዲስ ግቢ ጉባኤ ተመሠረተ፡፡
በዉጭ ዓለም ላለችው ቤተ ክርስቲያን ተረካቢ ለማፍራት እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ና ክርስትናቸውን ጠብቀው እንዲቆዩ የግቢ ጉባኤዎችን ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ በማኅበረ ቅዱሳን የሳን ሆዜ ንዑስ ማእከል የቤይ ኤሪያ ግቢ ጉባኤ ምሥረታ ተካሂዷል፡፡
ግቢ ጉባኤው ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥልም ውይይት የተካሄደ ሲሆን የግቢ ጉባኤ ተሳትፎ በተማሪዎቹ ዘንድ ከፍተኛ ፍላጎት ያለ መሆኑን በማውሳት ለተግባራዊነቱ የሁሉም ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ድርሻ መሆኑም ተጠቁሟል::
ግቢ ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅሙ ነገ በምድረ አሜሪካ ቁልፍና ታዋቂ ካምፓኒዎች ውስጥ ተቀጥረው ቤተ ክርስቲያንን የሚደግፉ በሥነ ምግባር የታነጹ ኦርቶዶክስ ባለሙያዎችን የሚያፈራ ኦርቶዶክሳዊ ተቋም ነውም ተብሏል በመርሐ ግብሩ፡፡
በተለይም በቤይ ኤርያ እና አካባቢው የሚኖሩ ወላጆች ለከፍተኛ ተቋም ተማሪዎቻቸው ጊዜ ሰጥተው በግቢ ጉባኤ አገልግሎት ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እና በቀጣይነትም ከዚህ በተሻለ ትጋት እንዲሳተፉ መምህራኑ አደራ ብለዋል፡፡