♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን እንኳን ወደ ባለማዕተቦቹ የተዋሕዶ ልጆች ቻናል በሰላም መጣችሁ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri








✞ የመዝሙር ግጥሞች ✞ dan repost
☦ ​​​​​​በሰሞነ ሕማማት የሚጸለዩት እና የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?



🛐 በሰሞነ ሕማማት የምንጸልያቸው ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?


➦በሰሞነ ሕማማት አጥብቀን የምንጸልያቸው ጸሎቶች ውዳሴ ማርያም:ዳዊት: ሰይፈ ሥላሴ:ሰይፈ መለኮት:ድርሳነ ማሕየዊ ውዳሴ አምላክ ናቸው።

➦እመቤታችን ድንግል ማርያም በዚህ በሰሞነ ሕማም በልጅዋ ምክንያት ብዙ እንግልት ስለደረሰባት የእሷን ምስጋና የሆነውን ውዳሴ ማርያም አናስታጉልም። ውዳሴ ማርያም ማመስገኛ መማጸኛ ስለሆነ እንጸልያለን። ምክንያቱም በዚህ በሰሞነ ሕማማት መከራ ተቀብሎ ሞቶ ሕይወቱን የሰጠንን ጌታ በሥጋ ወልዳለችን በውዳሴዋ እናስባታለን።

➦የቅዱስ ዳዊት ድርሰት የሆነው ታላቁ መዝሙረ ዳዊት በትንቢት ክፍሉ ስለ ጌታችን ሕማም ስቃይ እና ሞት የሚናገርና በዳዊት ምስጋና በምድር የሰው ልጆች በሰማይ ቅዱሳን መላእክት ስለሚያመሰግኑ እንጸልየዋለን።

➦ሰይፈ ሥላሴ ከሦስቱ አካላት እግዚአብሔር ወልድን የሚያመሰግን አምላክነቱን የሚመሰክር እና የሚመሰጥር በመሆኑ እንጸልየዋለን።

➦ሰይፈ መለኮት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ስለ ምስጢረ መለኮት እና ስለ ጌታችን አምላክነት ስለሚናገር እንጸልየዋለን።


➦ድርሳነ ማሕየዊ በቅዱስ ዮሐንስ ወልደ-ነጎድጓድ የዓይን እማኝነት እና የቃል ምስክርነት የተጻፈና የጌታችንን መከራ ስቃይ እንግልት እና ሞት በልዩ ሁኔታ የሚናገር በመሆኑ ልክ እንደ ውዳሴ ማርየም የየእለት/የየቀን ስላለው ብንጸልየው በዓይነ ሕሊና ቀራንዮ ወሰዶ በነፍሳችን የጌታችንን ሰማያዊ ውለታ የሚስልብንና በመጸለያችን ልዩ ጸጋና ክብር የሚያሰጥ የቃል-ኪዳን ጸሎት በመሆኑ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ብንጸልየው እጅጉን እንጠቀምበታለን። ውዳሴ አምላክም የጌታችን ምስጋና በመሆኑ መጸለይ እንችላለን።

🛐 በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?



➦በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩትን ጸሎቶች ጠቅለል አድርገን ስናያቸው ድርሳናት ገድላት እና መልካ መልኮች ናቸው። ይህም የሆነው በሰሞነ ሕማማት ጌታችን ለእኛ ለሰው ልጆች ብሎ የተቀበላቸውን ስቃይ እና መከራ ሞት የምናስብበት እና የምናለቅስበት እንጂ ሌሎቹን በድርሳናቸው በገድላቸው በመልካቸው የምናመሰግንበት ጊዜ ስላልሆነ ነው።

➦በተረፈ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ለራሳችሁ ለሀገራችሁ ብቻ አትጸልዩ ለዓለም ሕዝብ ለአሕዛብ በሙሉ ጸልዩ። ምክንያቱም ለእነሱ የመጣ ሰማያዊ ቁጣ በቀጥታም በተዘዋዋሪም ለእኛም ይተርፋልና። እነሱ ሲለበለቡ እኛ መቃጠላችን እነሱ ሲሰበሩ እኛ ወለም ማለታችን እነሱ ሲሞቱ ሞት ደጃፋችን መቆምን በማሰብ ለእነሱም እንጸልይ። የእነሱ መከራ ሲርቅ ነው የኛም የሚርቀው።

✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞



➮ከወደዱት ያጋሩ

💚 @maedot_ze_orthodox
💛 @maedot_ze_orthodox
❤️ @maedot_ze_orthodox


✟ ጋሜል- ዘ ኦርቶዶክስ ✟ dan repost
🌷​​​​​​ደብረ ዘይት አምስተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹ደብረ ዘይት› ይባላል፡፡


✨ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ✨

ደብረ ዘይት ማለት ቃሉ “ደብር” ሲል ተራራ ሲሆን “ዘይት” ሲል የወይራ ዛፍን ያመለከታል። ባጠቃላይ ደብረ ዘይት የወይራ ዛፍ (የዘይት ዛፍ) የበዛበት ተራራ ማለት ነው። ቦታው በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ከጎለጎታ (ቀራንዮ) ተራራ በስተምስራቅ በግምት ፪ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ታላቅ ተራራ ነው።

በሁለቱ ተራሮች መካከል ጌቴሴማኒ የሚባለው ለምለም ስፍራ ይኸውም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የመቃብር ስፍራ ይገኛል። የደብረ ዘይት ተራራ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ የሚያድርበት፣ የሚያስተምርበት፣ ውሎ የሚያርፍበት ሥፍራ ነው። ሉቃ ፳፩፥ ፴፯፣ ሉቃ ፳፪፥ ፴፱፣ ዮሐ ፰፥ ፩

➡️ ከዚሁ ተራራ ላይ ነው ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያረገው። ኋላም በዳግም ምጽአት እዚሁ ተራራ ላይ ነው ለፍርድ የሚመጣው። /ሐዋ ፩፥፲፫/። " " በዚህ ቀን ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ወደ ምድር ስለመምጣቱ (ዳግም ምፅአቱ ) ይሰበካል።

ይህን ዓለምንም አሳልፎ ለመረጣቸውና ላከበራቸው ዘላለማዊ መንግሥትን ሊያወርሳቸው እንደሚመጣ ይነገርበታል። ይህ ቀንም እኩለ ፆም በመባል የሚታወቅ ሲሆን በዚህች በተለየች ቀንም ሁሉም እንደ የሥራው ፍርዱን ከአምላክ የሚቀበልበት መሆኑ፤ መልካም ላደረጉ መልካም እንደሚመለስላቸ ክፉም ላደረጉ የክፋታቸውን ዋጋ እንደሚያገኙ ይሰበካል።


➡️ ጌታም የአባቴ ቡሩካን የተዘጋጀላችሁን የክብር ቦታ ውረሱ በማለት ወዳጆቹን እንደሚጠራ ይነገራል። "እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊቱ ይቃጠላል " ማቴ.፳፬፡፩-፴፮ ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ።

እርሱ ግን መልሶ፦ ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው። እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።


➡️ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ብዙዎች። እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ። ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።

ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው። በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።

በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። "መልካም የጾምና የጸሎት ጊዜ ይሁንልን ቅዱስ እግዚአብሔር ጸሎት ልመናችንን ይቀበልልንን።

💚@maedot_ze_orthodox
💛@maedot_ze_orthodox
❤️@maedot_ze_orthodox


✟ ጋሜል- ዘ ኦርቶዶክስ ✟ dan repost
💫 ምኵራብ


🌹እንኳን ለዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።



➡️ ሦስተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹ምኵራብ› ይባላል፡፡ ምኵራብ አምልኮተ እግዚአብሔር ሲፈጸምበት፣ ሕገ ኦሪት ሲነበብበት የነበረ በአይሁድ የሚሠራ መካነ ጸሎት ነው፡፡ ዘወትር ቅዳሜ ብዙ ሕዝብ ይሰበሰብበት ስለ ነበር ጌታችን ለማስተማር ብዙ ጊዜ በምኵራብ ተገኝቶአል፡፡ ስያሜው የተወሰደው በዮሐንስ ፪፥፲፬ ‹‹ወረከበ በምኵራብ እለ ይሠይጡ አልህምተ ወአባግዐ ወአርጋበ …፤ በመቅደስም በሬዎችን፣ ላሞችን፣ በጎችን፣ ርግቦችን፣ የሚሸጡትን አገኘ …›› ተብሎ ከተገለጸው ኃይለ ቃል ላይ ሲኾን፣ ‹ምኵራብ› የሚለው ቃልም በአማርኛ ‹መቅደስ› ተብሎ ተተርጕሟል፡፡


➡️ ምኵራብ የሚባለው ሳምንት ጌታችን ወደ ምኵራብ ገብቶ ማስተማሩ የሚነገርበት፤ ‹‹ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል፤ እናንተ ግን የሌቦች ዋሻ አደረጋችሁት›› ብሎ በምኵራብ ይሸጡ፣ ይለውጡ የነበሩትን የገሠፀበት፤ ቤተ መቅደስን የከብት መንጃ የወርቅና የብር መነገጃ ያደረጉ ሰዎችን ከነሸቀጣቸው ከቤተ መቅደስ ያስወጣበት፤ ቤተ መቅደስ የእግዚአብሔር ማደሪያ፣ የስሙ መጠሪያ፣ የጸሎት ሥፍራ መኾኗን ያስረዳበትና ያወጀበት፤ በቤተ መቅደስ የንግድ ሥራ ማከናወን እንደማይገባ ያረጋገጠበት ዕለት ነው፡፡

ቅዱስ አማኑኤል ጾም ጸሎታችንን ይቀበለን!!!



💚@maedot_ze_orthodox
💛@maedot_ze_orthodox
❤️@maedot_ze_orthodox


🎉የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው

1 ለወጣ 500 ብር ካርድ  💵
2 ለወጣ 250 ብር ካርድ 💵
3 ለወጣ 150 ብር ካርድ 💵

👉 ዝግጁ ከሆናችሁ 💸 START 💸 የሚለውን ይጫኑ 👇


ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ




✞ የመዝሙር ግጥሞች ✞ dan repost
❣️🌷❣️🌷
የመንገዴ መሪ ፈውስ ነህ ለህመሜ
ገብርኤል ስትመጣ በዛልኝ ሰላሜ
ደስታን አብሳሪ ተሸክመህ ዜና
ዛሬም ለሀገራችን ምስራች ይዘህ ና





✝️ ቅዱስ ገብርኤል ከክፉ ነገር ይጠብቀን።


✞ የመዝሙር ግጥሞች ✞ dan repost
​​​​
💗 እንኳን ለታላቁ "የጌታ ጾም ጾመ እግዚእ" በሰላም አደረሳችሁ!!!


➡️ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ምዕመናን
እንዲጾሟቸው የሠራቻቸው 7 አጽዋማት አሏት። "ጾም" ማለት "መከልከል" ነው። የምንከለከለው ደግሞ ከኃጢአትና ከክፋት ሲሆን አንድም ሰውነትን ወደዚያ ከሚወስዱ አዝማደ መባልዕት (የምግብና የመጠጥ ዓይነቶች) መከልከልን ይመለከታል።

➦​ 7ቱ አጽዋማት:-


✨1.ዓቢይ ጾም
✨2.ጾመ ፍልሠታ
✨3.ጾመ ሐዋርያት
✨4.ጾመ ነቢያት
✨5.ጾመ ድኅነት
✨6.ጾመ ነነዌ እና
✨7.ጾመ ገሃድ ይሰኛሉ::


➡️ በእነዚህ አጽዋማት ከዓቢይ ጾም በቀር እስከ 9 ሰዓት ድረስ መጾም ይገባል። ዓቢይ ጾም ግን የተለየ ሥርዓት አለው ስለ ጾም ሲነሳ አስቀድሞ የሚመጣው ጥያቄ አስፈላጊነቱ ነው "ጾም ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ ከመጠየቅ "ሃይማኖት ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ መጠየቁ ይቀላል።

➡️ ምክንያቱም ከሃይማኖታዊ ትዕዛዛት ትልቁ በመሆኑ እርሱን መቃወም ሃይማኖትንና አዛዡን እግዚአብሔርን መቃወም ነውና። እኛ ሃገር ላይ የተለመደች ክፉ ልማድ አለች። የከበደችንን ነገር "አያስፈልግም" በሚል እንከራከራለን።

➡️ ደግሞ ጾምን ለመሻር ጥቅስ የሚጠቅሱ ወገኖች በጣም ይገርሙኛል። ኃጢአትን ለመሥራት ፡ ጾምንም ለመሻር ጥቅስን መጥቀስ አያስፈልግም። እኛ ግን ከፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ (ማቴ. 4:2)

አበው ቅዱሳን ጾመው (ዘዳ. 9:19, ነገ. 19:8, ሐዋ.13:3, ቆሮ. 4:11) አሳይተውናልና እንደ አቅማችን እንጾማለን።


➦​ የጾሙ የመጀመሪያው ሳምንት (ዘወረደ) የሚጾመው እስከ 12 ሰዓት ሲሆን ከቅድስት (ከ2ኛው ሳምንት) እስከ ተጽኢኖ (የኒቆዲሞስ ዓርብ) ድረስ ደግሞ እስከ 11 ሰዓት ይጾማል:: በሰሙነ ሕማማት ግን የምንጾመው "እስከ ይሠርቅ ኮከብ" (እስከ ምሽት 1 ሰዓት) ድረስ ይሆናል::

➡️ ነገር ግን ሁሉም እንደ መጠኑ ነውና ከመምሕረ ንስሃ ጋር ሊጨዋወቱት ይገባል። በዓቢይ ጾም ለቻለ ቂጣ በጨው እየበላ፡ ውሃ እየተጐነጨ ሊጾም ይገባል። በእነዚህ 55 ቀናትም ከዕለተ ሆሳዕና በቀር ከበሮ አይጐሰምም። ጸናጽል አይጸነጸልም። ተድላ ደስታም አይደረግም።

➡️ አብዝቶ መብላት ፡ ሳቅ ማብዛትና ጌጥን ማብዛትም እንዲሁ አይገባም። ለቻለ ደግሞ በሌሊት ሰዓታቱን፡ በግህ ኪዳንና ስብሐተ ነግሁን ፡ በመዓልት ቅዳሴውን ፡ በሰርክ (ምሽት) ደግሞ ምሕላውን ሊሳተፍ ይገባል።

➡ በእነዚህ 55 ቀናት ፈቃደ ሥጋ ሊደክም : ፈቃደ ነፍስ ልትሰለጥን ግድ ነውና። ከሌላው ጊዜ በተሻለ ወቅቱ ምጽዋትና ጸሎት የሚደረግበት ነው። በዚያውም ላይ ነገሮችን እያመቻቹ በእነዚህ ዕለታት ቅዱስ ቃሉን መስማት (ማንበብ) ይገባል። በትዳር ውስጥ ላሉም መኝታን መለየት ግድ ነው።

➦​ ከ7ቱ አጽዋማት አንዱ የሆነው ይህ ጾም=


✨1.ዐቢይ (ታላቁ) ጾም
✨2.የጌታ ጾም
✨3.ጾመ ሑዳድ
✨4.የድል ጾም
✨5.የካሳ ጾም
✨6.አርባ ጾም
✨7.የፍቅር ጾም . . .በሚሉ መጠሪያዎችም ይታወቃል።

➦​ የጾሙ መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት ደግሞ=


✨1.ጾመ ሕርቃል
✨2.ጾመ በረከት ዘሐዋርያት
✨3.ሰሙነ ዘወረደም ይባላል።

✝️ ጾሙን የሰላም ፡ የፍቅር ፡ የምሕረት: የፀጋ :የበረከት ያድርግልን። ጾሞ ለማበርከትም ያብቃን፡፡



"አሁንስ ይላል እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁ በጾምም በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ። ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ። አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ: ቁጣው የዘገየ: ምሕረቱም የበዛ: ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ። "ትን. ኢዩኤል 2:12

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞








✞ የመዝሙር ግጥሞች ✞ dan repost
💗 እንኳን ለነነዌ ጾም አደረሳችሁ




🌺💚🌺💚🌺


✞ የመዝሙር ግጥሞች ✞ dan repost
                                              



🌺💚🌺💚🌺



†††
ወርኀ ጥርን በቸር ያስፈጸመ አምላከ ቅዱሳን ወርኀ የካቲት እንዲባርክልን እንለምነው።



♱ ♱ ♱
💚 💛 ❤️   
                                        


🛏 አልጋ መግዛት ለምትፈልጉ ኑ አልጋ ላሳያችሁ!!ይህ አልጋ የተራ ሰው ወይም የወታደር አልጋ አይደለም፡፡ የንጉሥ አልጋ ነው፡፡ ንጉሥም ቢባል ተራ ንጉሥ ሳይሆን በዓለም ሁሉ የሚዘመርለት ታላቅ ንጉሥ አልጋ ነው፡፡ የንጉሥ ዳዊትን አልጋ ላሳያችሁ፡፡ ይህ አልጋ ከወርቅ ወይም ከአልማዝ ወይም ከከበሩ ድንጋዮች የተሠራ አይደለም፡፡ ይህ አልጋ.... See mor


✞ የመዝሙር ግጥሞች ✞ dan repost
በጨነቃችሁ ጊዜ ሁሉ ቸሩ መድኃኔዓለም አለው ይበላችሁ።


🥰🙏🥰



♡ ㅤ   ❍ㅤ    ⎙ㅤ   ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ




✟ ጋሜል- ዘ ኦርቶዶክስ ✟ dan repost
"ጌታ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ። እነሆም ሰማያት ተከፈቱ። የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ፡ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ። እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ:- 'በእርሱ ደስ የሚለኝ፡ የምወደው ልጄ ይህ ነው' አለ።"
(ማቴ. ፫፥፲፮)





🕊 🕊
🕊
🕊
🕊 መልካም የጥምቀት በዓል ይሁንልን! 🕊

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.