✞ ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው ✞
ጨነቃት ጠበባት የዳዊት ከተማ
የጌታ መወለድ ተአምሩ ሲሰማ
ወረደ መልአኩ ምስራች ሊያወራ
የህፃኑ ክብር በምድር አበራ
ሰብዐ ሰገል መጡ ከሩቅ ምስራቅ አገር
ወርቅ ዕጣን ከርቤውን ለርሱ ለመገበር
በእናቱም እቅፍ አገኙት ህፃኑን
ለዓለም ተናገሩ ንጉሥ መወለዱን
የይሁዳ ምድር ምስጋና ተመላ
ንጉሥ መጥቷልና ከናዝሬት ገሊላ
ተአምሩን ትናገር ቤተልሔም ታውራ
ዝማሬ ሲውጣት ተረስቶ ቆጠራ
የማይታይ ታየ ተዳሰሰ አንደ ሰው
በጠባቡ ደረት ዓለምን ወሰነው
ገረማት ጥበቡ ታናሿን ሙሽራ
ተዋህዷልና ቃል ከሥጋ ጋራ
ሊቀ መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው
በመጠቅለያም ጠቀቀለለችው
የለምና ስፍራ ለንግዶች ማረፊያ
ግርግም አስተኛችው በከብቶች ማደሪያ
ጨነቃት ጠበባት የዳዊት ከተማ
የጌታ መወለድ ተአምሩ ሲሰማ
ወረደ መልአኩ ምስራች ሊያወራ
የህፃኑ ክብር በምድር አበራ
ይህ ምስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር(፪)
አዝ
ሰብዐ ሰገል መጡ ከሩቅ ምስራቅ አገር
ወርቅ ዕጣን ከርቤውን ለርሱ ለመገበር
በእናቱም እቅፍ አገኙት ህፃኑን
ለዓለም ተናገሩ ንጉሥ መወለዱን
ይህ ምስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር(፪)
አዝ
የይሁዳ ምድር ምስጋና ተመላ
ንጉሥ መጥቷልና ከናዝሬት ገሊላ
ተአምሩን ትናገር ቤተልሔም ታውራ
ዝማሬ ሲውጣት ተረስቶ ቆጠራ
ይህ ምስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር(፪)
አዝ
የማይታይ ታየ ተዳሰሰ አንደ ሰው
በጠባቡ ደረት ዓለምን ወሰነው
ገረማት ጥበቡ ታናሿን ሙሽራ
ተዋህዷልና ቃል ከሥጋ ጋራ
ይህ ምስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር
ሊቀ መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
@ailafat_1