✞ እርሱ ፍጹም ሊልቅ ✞
እርሱ ፍጹም ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባል
ከኔ ይልቅ ጌታ እጅግ ይበረታል
እኔ ለንስሐ በውሃ አጠመቅኳችሁ
በእሳት ያጠምቃል ይመጣል ያልኳችሁ(፪)
ጫማውን ልሸከም ከቶ የማይገባኝ
እኔን አስቀድሞ ለአገልግሎት ጠራኝ
ከኋላዬ የመጣው ነበረ ከፊቴ
በስሙ ታምኑ ዘንድ እርሱ ነው ስብከቴ
በምድረ በዳ ላይ የጮህኩለት ንጉሥ
የኃያላን ኃያል ተገልጿል ኢየሱስ
ለኃጢያት ስርየት ይሰዋል ይኄ በግ
ለዓለም ሁሉ መዳን በቀራንዮ ሠርግ
ለንስሐ የሚሆን ፍሬ ዛሬ አድርጉ
በሠርጉ ሊጠራን መጥቷልና በጉ
ከሚመጣው ቁጣ በእርሱ እንድታመልጡ
የእፉኝት ልጆች ከባቢሎን ውጡ
የአብርሃም ልጆች ነን በማለት ላትድኑ
የመዳኑን ሰዓት ቀኑን አታባክኑ
ለአብርሃም ልጆች ከድንጋይ ያስነሳል
መንሹንም በእጁ ነው አውድማው ይጠራል
ጠማማው ልብ ይቅና ጥርጊያው ይደላደል
ፍሬ የሌለው ዛፍ በእቶን ሳይቃጠል
ምሳር በዛፎች ስር ዛሬም ተቀምጧል
ንስሐ ግቡ ነው የመጨረሻው ቃል
መዝሙር
ሊቀ መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
"እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል"
ዮሐ ፫ ፥ ፴
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yebuhe_mezmuroch
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
እርሱ ፍጹም ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባል
ከኔ ይልቅ ጌታ እጅግ ይበረታል
እኔ ለንስሐ በውሃ አጠመቅኳችሁ
በእሳት ያጠምቃል ይመጣል ያልኳችሁ(፪)
ጫማውን ልሸከም ከቶ የማይገባኝ
እኔን አስቀድሞ ለአገልግሎት ጠራኝ
ከኋላዬ የመጣው ነበረ ከፊቴ
በስሙ ታምኑ ዘንድ እርሱ ነው ስብከቴ
በምድረ በዳ ላይ የጮህኩለት ንጉሥ
የኃያላን ኃያል ተገልጿል ኢየሱስ
ለኃጢያት ስርየት ይሰዋል ይኄ በግ
ለዓለም ሁሉ መዳን በቀራንዮ ሠርግ
ለንስሐ የሚሆን ፍሬ ዛሬ አድርጉ
በሠርጉ ሊጠራን መጥቷልና በጉ
ከሚመጣው ቁጣ በእርሱ እንድታመልጡ
የእፉኝት ልጆች ከባቢሎን ውጡ
የአብርሃም ልጆች ነን በማለት ላትድኑ
የመዳኑን ሰዓት ቀኑን አታባክኑ
ለአብርሃም ልጆች ከድንጋይ ያስነሳል
መንሹንም በእጁ ነው አውድማው ይጠራል
ጠማማው ልብ ይቅና ጥርጊያው ይደላደል
ፍሬ የሌለው ዛፍ በእቶን ሳይቃጠል
ምሳር በዛፎች ስር ዛሬም ተቀምጧል
ንስሐ ግቡ ነው የመጨረሻው ቃል
መዝሙር
ሊቀ መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
"እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል"
ዮሐ ፫ ፥ ፴
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yebuhe_mezmuroch
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈