✟ ጋሜል- ዘ ኦርቶዶክስ ✟ dan repost
💗✞ የፍቅር ሐዋርያ ✞💗
==================
➦ በተለይ ደግሞ ከፈጣሪው ክርስቶስ ጋር የነበረው ፍቅር ፍጹም የተለየ ነበር። በዚህ ምክንያትም ጌታ ባረገ ጊዜ እንዲህ ብሎታል:- "ለፍጡር ከሚገለጥ ምሥጢር ከአንተ የምሠውረው የለኝም" ብሎታል።
➦ ቀጥሎም በንጹሕ አፉ ስሞታል። ሊቁ:-
"ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ:
ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ" እንዳለው። (መልክዐ ኢየሱስ)
➦ ቅዱስ ዮሐንስ ከእመቤታችንም ጋር ልዩ ፍቅር ነበረው። እርሷ እንደ ልጇ ስትወደው: እርሱ ደግሞ እንደ እናቱ ልቡ እስኪነድ ድረስ ይወዳት ነበር:: እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ ተከትሎ ያገኛት እመቤቱ ናትና።
➦ ከዚያ ሁሉ ጸጋና ማዕረግ የመድረሱ ምሥጢርም ድንግል ናት። ለ15 ዓመታት በጽላሎተ ረድኤቷ (በረዳትነቷ ጥላ) ተደግፎ አብሯት ሲኖር ብዙ ተምሯል ከመላእክትም በላይ ከብሯል። ከንጽሕናዋ በረከትም ተካፍሏል።
➦ ድንግል ባረፈችበት ቀንም ልክ እንደ ልጇ ክርስቶስ እርሷም ስማው: ታቅፋው ዐርፋለች። ሊቃውንቱ ለዚህ አይደል በንጹሕ ከንፈሮቿ መሳምን (መባረክን) ሲሹ "በከመ ሰዓምኪ ርዕሰ ዮሐንስ ቀዳሚ: ስዒሞትየ ማርያም ድግሚ" ያሉት።
➦ ታላቁ ቅዱስ ሐዋርያ ዕድሜው 90 ዓመት በሆነው ጊዜ በዚህች ዕለት ተሰውሯል። ከዚያ አስቀድሞም የዓለምን ፍጻሜ ተመልክቷል። ዛሬ ያለበትን የየሚያውቅ ቸር ፈጣሪው ነው።
መልካም የገና በዓል
💚@maedot_ze_orthodox
💛@maedot_ze_orthodox
❤️@maedot_ze_orthodox
==================
⛪️ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን 'የፍቅር ሐዋርያ' ትለዋለች። ለ70 ዘመናት በቆየ ስብከቱ ስለ ፍቅር ብዙ አስተምሯል። ፍቅርንም በተግባር አስተምሯል። በየደቂቃውም "ደቂቅየ ተፋቀሩ በበይናቲክሙ ልጆቼ ሆይ! እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ" እያለ ይሰብክ ነበር።
➦ በተለይ ደግሞ ከፈጣሪው ክርስቶስ ጋር የነበረው ፍቅር ፍጹም የተለየ ነበር። በዚህ ምክንያትም ጌታ ባረገ ጊዜ እንዲህ ብሎታል:- "ለፍጡር ከሚገለጥ ምሥጢር ከአንተ የምሠውረው የለኝም" ብሎታል።
➦ ቀጥሎም በንጹሕ አፉ ስሞታል። ሊቁ:-
"ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ:
ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ" እንዳለው። (መልክዐ ኢየሱስ)
➦ ቅዱስ ዮሐንስ ከእመቤታችንም ጋር ልዩ ፍቅር ነበረው። እርሷ እንደ ልጇ ስትወደው: እርሱ ደግሞ እንደ እናቱ ልቡ እስኪነድ ድረስ ይወዳት ነበር:: እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ ተከትሎ ያገኛት እመቤቱ ናትና።
➦ ከዚያ ሁሉ ጸጋና ማዕረግ የመድረሱ ምሥጢርም ድንግል ናት። ለ15 ዓመታት በጽላሎተ ረድኤቷ (በረዳትነቷ ጥላ) ተደግፎ አብሯት ሲኖር ብዙ ተምሯል ከመላእክትም በላይ ከብሯል። ከንጽሕናዋ በረከትም ተካፍሏል።
✝️ ስለ ድንግል ማርያምም "ነገረ ማርያም" የሚል ድርሰት ሲኖረው "የሰኔ ጐልጐታንም" የጻፈው እርሱ ነው።
➦ ድንግል ባረፈችበት ቀንም ልክ እንደ ልጇ ክርስቶስ እርሷም ስማው: ታቅፋው ዐርፋለች። ሊቃውንቱ ለዚህ አይደል በንጹሕ ከንፈሮቿ መሳምን (መባረክን) ሲሹ "በከመ ሰዓምኪ ርዕሰ ዮሐንስ ቀዳሚ: ስዒሞትየ ማርያም ድግሚ" ያሉት።
➦ ታላቁ ቅዱስ ሐዋርያ ዕድሜው 90 ዓመት በሆነው ጊዜ በዚህች ዕለት ተሰውሯል። ከዚያ አስቀድሞም የዓለምን ፍጻሜ ተመልክቷል። ዛሬ ያለበትን የየሚያውቅ ቸር ፈጣሪው ነው።
💠 እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው።
✨ወንጌላዊ
✨ሐዋርያ
✨ሰማዕት ዘእንበለ ደም
✨አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ)
✨ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት)
✨ወልደ ነጐድጉዋድ
✨ደቀ መለኮት ወምሥጢር
✨ፍቁረ እግዚእ
✨ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ)
✨ቁጹረ ገጽ
✨ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ)
✨ንስር ሠራሪ ልዑለ ስብከት
✨ምድራዊው መልዐክ
✨ዓምደ ብርሐን
✨ሐዋርያ ትንቢት
✨ቀርነ ቤተ ክርስቲያን
✨ኮከበ ከዋክብት
💠 በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር።
መልካም የገና በዓል
💚@maedot_ze_orthodox
💛@maedot_ze_orthodox
❤️@maedot_ze_orthodox