Mame Posts


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha
Toifa: Bloglar


"In our channel:
We share beneficial Islamic reminders, daily moral guidance, and valuable posts for a better life. & Beneficial posts for everyone!

Buy ads: Telega.io/c/mame_posts
For paid promotion👇

contact us: @Ads_poster1bot

Bog‘liq kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Toifa
Bloglar
Statistika
Postlar filtri


የጌታችንን ንግግር ችላ ብለን እንለወጣለን ማለት ያለ ዉዱ መስገድ ያለፆም ማፍጠር የለ እውቀት ማወቅ የሆነ ግራ የሚያጋባ ኑሮ ነው So ወደ ቁርዓን እንመለስ....

https://t.me/mame_posts


ለፈገግታ😁

▢ ​አንድ ወጣት ካገባ በኋላ እናቱ ወደ እሱ መጥታ፦ 'ልጄ ሆይ! ሚስትህ ቀኑን ሙሉ ተኝታ እኔ ደግሞ ማብሰልና መጥረግ ደከመኝ፤ የቤት ስራ እንድታግዘኝ ንገራት'😭 አለችው።

​እሱም፦ 'እማዬ እሷን ቀጥታ ለመናገር አፍራለሁ፤ ግን አሪፍ ዘዴ አለኝ!' አላት።

▢ ​'ጧት ሲነጋ መጥረጊያውን ይዘሽ መጥረግ ጀምሪ፤ እኔ ደግሞ መጥቼ "እማዬ እኔ እያለሁ #አንቺ_አትጠርጊም" ብዬ መጥረጊያውን እቀማሻለሁ። አንቺ ደግሞ "አይ ልጄ አንተ ወንድ ነህ፣ እኔ እያለሁ አትጠርግም" ትይኛለሽ ሚስቴ ይህንን ስትሰማ አፍራ ወዲያው ተነስታ በራሷ መጥረግ ትጀምራለች' አላት።☕️

​ጠዋት ላይ እቅዳቸውን ለመተግበር ተነሱ። እናትና ልጅ መጥረጊያውን እየተቀባበሉ 'እኔ ልጥረግ... እኔ ልጥረግ' መባባል ጀመሩ። ሚስት በጩኸቱ ተቀስቅሳ ተነሳችና፦ 'ምን ሆናችሁ ነው በጠዋት እንደዚህ የምትጫረሱት?' አለች።

​ባልየው፦ 'እናቴ ስትጠርግ አይኔ እያየ ዝም አልልም!' አለ። እናትየውም፦ 'አይ ልጄ እኔው እራሴ ነኝ የምጠርገው!' አለች።

​ሚስትየው ነገሩን በትዝብት ተመለከተችና፦
'እሺ በቃ... ችግር የለውም! አንድ ቀን አንተ ጥረግ፣ አንድ ቀን ደግሞ እናትህ ትጥረግ!' ብላ እርፍ😭

1.6k 0 33 22 162

Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
.
​ሮማንቲክ ምንም #ያልገባትን ስታገባ የሚፈጠረው😭

1.8k 0 32 20 105

.
ሱብሐን አላህ! ሰዎች እጃቸውን በሰበሰቡ ጊዜ ሰጪ የሆነው፣ ምክንያቶችና መፍትሔዎች በመጡ ጊዜም ከልካዩ #አላህ_የጠራ_ነው። ትዕዛዙ የማይለወጥ፣ ሕጉም የማይሻር፣ እርዳታውና እዝነቱ ፈጽሞ የማይቋረጥ አላህ የጠራ ነው። 🤍


ከልብ የመነጨ ዱዓ❤️‍🩹

አላህ ሆይ! እነዚህን ባሮችህን አስደስታቸው፣ ጭንቃቸውን ግፈፍላቸው፣ ተስፋቸውንና ምኞታቸውን ሁሉ #አሳካላቸው፣ ጀነትንም መኖሪያቸውና ማረፊያቸው አድርግላቸው፣ ከማንኛውም ህመምና  በሽታ አርቃቸው ያረብ፤ በ ጀነትም ውስጥ ከእነሱ ጋር አሰባስበኝ።🤍


@mame_posts


.
ከዚህ ነው #ትእግስትን የተማርነው😭

2k 0 5 37 86

ጁምዓን ዬት ሰገዳችሁ #ኹጥባውስ ስለ ምን ነበር?


እስኪ እንተዋወስ💙

2k 0 0 15 34

.
የልባችሁ ደርሶ፣ ❝አላህኮ ያንን ነገር አሳካልኝ!❞ የምትሉበትን የደስታ ጊዜ አላህ ያቅርብላችሁ፤ ምኞታችሁንም ሁሉ ይሙላላችሁ።🤲

🤲


አላህን በደንብ እንድወደው እና ወደሱ እንድቃረብ የምሰራቸው ዒባዳዎችም (አምልኮዎችም) እንዲጣፍጡኝ ምን ላድርግ?

ምን ትመክሩኛላችሁ?
😢


.
አንድ ባል ' #በቃሽ_ዝም_በይ!' ሲላት ያለ ምንም ጭቅጭቅና ክርክር ወዲያውኑ ጸጥ ብላ የምትቀበል ሚስት ላይ የአላህ ሰላም ይውረድ😌

2.6k 0 15 30 154

#አጠር_ያለች_ታሪክ❤️‍🩹

​ አንዱ ሰው ወተት ይሸጥ ነበር፤ ወተቱም ያልተበረዘ (ንጹህ) ጥራት ያለው ነበር። ​ብዙ ያሚያምኑትና የሚተማመኑበት ደንበኞችም ነበሩት። ከዕለታት አንድ ቀን ግን ሻጩ የእለት ተእለት ትርፉን ለመጨመር ወሰነ፤ እናም ወተቱን ከውሃ ጋር በመቀላቀል ሸጠው።

▢ ደንበኞቹ በእሱ ላይ ሙሉ እምነት ስለነበራቸው አልተጠራጠሩም፤ ሻጩም የተለመደውን ዕለታዊ ትርፍ እጥፍ አተረፈ።
​ወደ ቤቱ በመመለስ ላይ ሳለም ሰውየው ደከመው፤ እናም በወንዙ አጠገብ ያለችው ዛፍ ስር አረፍ ብሎ ሊቀመጥ ወሰነ፤ ገንዘቡን የያዘውን ከረጢቱንም መሬት ላይ አስቀመጠው። ድንገትም አንድ ዝንጀሮ መጥቶ ከረጢቱን ወሰደው።

▢ ሻጩም ከረጢቱን እንዲመልስለት መማጸን ጀመረ፤ ዝንጀሮውም የገንዘብ ከረጢቱን ከፈተና፤ አንድ ሳንቲም ለሻጩ እየወረወረ፣ ሌላዋን ሳንቲም ደግሞ ወደ ወንዙ መወርወር ጀመረ፤ ከረጢቱም እስኪያልቅ ድረስ ይህንኑ ማድረጉን ቀጠለ።

▢ ​ሰውየው ገንዘቡን ሲቆጥረው ተገረመ፤ ገንዘቡም ሳይበረዝ (ንጹህ) በነበረው ወተት ያገኘው የትርፍ መጠን ልክ ብቻ ሆኖ አገኘው። ሰውየውም ፈገግ ብሎ እንዲህ አለ፦


«የወተቱ ገንዘብ ለወተት ሄደ፣ የውሃው ገንዘብ ደግሞ ለውሃው ሄደ!»❤️‍🩹

✅ @mame_posts

2.7k 0 25 7 106

.
በቻልነው አቅም #እንፈራሃለን ጌታዬ።
አንተን ለማይፈሩት አሳልፈህ አትስጠን።


.
በህፃንነቴ፣ ከኔ በዕድሜ የምትበለጥ ልጅ ነበረች፣ #ሁልጊዜ_ትደበድበኝ ነበር... አላህ ይቅር ይበላት!😭

​ዛሬ በአጋጣሚ መንገድ ላይ ከባለቤቷ ጋር ስትሄድ አየኋት። ሁለቱም ወደ እኔ ዞረው ትኩር ብለው ተመለከቱኝና ፈገግ ብለው ሳቁብኝ...💔

​ አስቡት... የድሮውን የምትደበድበኝን ታሪክ በሙሉ ለባለቤቷ ዘርዝራ ነግራው ይሆን እንዴ?😭

2.6k 0 7 16 162

📌 ክብር የጋራ ነው!
ስንፈልጋችሁ 'ዝም' ያላችሁ ሰዎች  ስትፈልጉን ባታገኙን አትዘኑ። ጓደኝነት እና ክብር የጋራ (Two-way street) እንጂ ሲመቻችሁ ብቻ የምትመጡበት ማረፊያ አይደለም! ላከበረን ክብር አለን ላራቀን ደግሞ ቆንጆ ዝምታ አለን! 🤫
📌 ዋጋህን እወቅ!
ለሰጠኸው ክብር እና ጊዜ ተገቢውን ምላሽ (Reply) ለማይሰጥህ ሰው  አንተም ራስህን አታስጨንቅ። ስትፈልጋቸው ለሌሉ ሰዎች ሲፈልጉህ መገኘት ግዴታህ አይደለም። ሁሌም ለራሳችሁ ክብር ስጡ መከበር ያለበትን ሰው ብቻ አክብሩ!
📌 አንዳንድ ሰዎች የሚፈልጉህን ያህል እንጂ የምትፈልጋቸውን ያህል አጠገብህ የሉም። ለእንደዚህ አይነት ሰዎች የሚመጥነው ምርጡ መልስ "ዝምታ"ብቻ ነው! 💯


✍🏽بنت أبي
@mame_posts


ታሞ ነበረ ዳነ፤ አጥቶ ነበረ አገኘ፤ አዝኖ ነበረ ሳቀ! ለመባል አላህ ያብቃችሁ፤ ያብቃን።

2.9k 0 18 25 172

A girl commented on my post, a guy replied her, she replied again, they were about to fall in love, so I deleted my post 😂


.
ጌታዬ ! እሷ ለእሷ #የሚበጃትን አታውቅምና እባክህ ለእኔ ዳራት!😁

3.7k 0 39 24 194

📌 ለተግባር እንጂ ለቃላት ክርክር ቦታ የለንም!

አንዳንዴ በቃላት ስያሜና ትርጉም ላይ በመከራከር ጊዜያችንን ስናጠፋ፣ ዋናውን የፈጣሪን ትዕዛዝና አላማ እንዘነጋለን።

የሴት ልጅን እስላማዊ አለባበስ "ሂጃብ"፣ "ጅልባብ" ወይም "ኹሙር" አልነው፤ ዋናው ቁምነገር አላህ (ሱ.ወ) ያዘዘንን የጨዋነት፣ የክብር እና የመሸፈን ስርዓት በተግባር ላይ ማዋላችን ነው። የቃላቱ ትርጉም ምንም ይሁን ምን፣ የተግባሩ ግብ አላህን መታዘዝ ነው!

ዲን ማለት ትዕዛዝን በተግባር መፈጸም እንጂ፣ በቃላት ስያሜ ላይ ስህተት እየፈለጉ መከራከር እና ሰውን መወነጃጀል አይደለም። ታላላቅ ዑለማኦች ያስተማሩንን የቃላት አጠቃቀም እንደ "አዲስ ዲን" (ቢድዓ) ማየት መሃይምነት ነው።

እውቀታችንን ለስራ እና ለትግበራ እንጂ፣ አጉል ክርክር አንክፈትበት።

✨ ዋናው ቁምነገር ስሙ ማን ይባላል ሳይሆን አላህ ያዘዘውን በተግባር እየፈጸምን ነው ወይ? የሚለው ነው!


✍🏽بنت أبي
@mame_posts


አንድ ጓደኛዬ የሆነ ምክር መከረኝ💔

'መንገድ ላይ አንዲት ሴት ብቻዋን ስትሄድ ብታይ እንዳትፈራህ
#ከጀርባዋ_አትከተላት፤ ይልቁንም ፈጠን ብለህ  ከፊቷ ቀድመህ እንዳትፈራ አረጋጋት!' አለኝ።

​ ዛሬ ወደ  ሱቅ ተልኬ ስሄድ መንገድ ላይ አንዲት ሴት ብቻዋን ስትሄድ  አየሁ፤ መንገዱም ጭር ያለ  ነበር። የጓደኛዬን ምክር ተግባራዊ ለማድረግ እንዳትፈራኝ ብዬ ልቀድማት ሞከርኩ...

​እኔ ራመድ ራመድ ብዬ ልቀድማት ስሞክር  እሷም አፈጠነች!

እኔ ፍጥነቴን ጨምሬ ስሮጥ እሷም እየሮጠች ጩኸቷን ቀወጠችው!  'ድረሱልኝ!  ድረሱልኝ ሊያፍነኝ ነው!' እያለች በጩኸት አከባቢውን አወከችው! ወደ ቤት እየሮጥኩ ተመለስኩ😭


@mame_posts

3.4k 0 50 16 194

ኢላሂ የኔ ጌታ......>>
ደካማ ባሪያህ አይደለዉ
ተስፋ መቁረጥ ከጀመር
እቅድህ ከእቅዴ ከህልሜ
የተሻለ እንደሆነ አስታዉሰኝ‼️🤲

@mame_posts

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.