Behailu Mulugeta እንደጣፉት
ይህ መርፌ..
ልጄን ለማውጣት ሲባል በሚስቴ ጀርባ የገባ #ይህ_መርፌ!
.
.
ነርቯን ለማግኘት ሲባል የጀርባዋ ማለቂያ ላይ ተሰካ። ግማሸ ሰውነቷ በደነላቸው። ቁልቁል እንዳታይ ከአንገቷ በታች መጋረጃ ተዘርግቷል!
.
ቀዶ ጥገናውን ተጀመረ። "አህ" አለች።
"እንዴ! ትቅሚያለሸንዴ?" አሏት።
ፈርታለች እንጂ የኔ ሚስት
"የታለ? ወይም መቼ?" ነበረ የምትለው😁
.
በአፏ በኩል ደገሟት። እኔ ውጪ ዳዊት ደግማለሁ።
.
relax እንድታደርግ መዝሙር ከፈቱላት። "ቅኔ ከአፌ ፈሰሰ" ይላል። የምትወደው መዝሙር። በሰመመን ሆና መዘመር ገባች!
እጇ ታሰሯል እንጂ አታሸበሽብም ብላችሁ ነው😁
.
ዶክተሮች በሁኔታዋ ፈገግ ማለታቸው አልቀረም።
.
አካሏ ከቀዶ ጥገና ክፍል እየተገፋ ወጣ። አንሶላ ብቻ ጣል ተደርጎባታል። ብቻዬን የማየው ይሔ ገላ ኮሪደር ለኮሪደር እንደ ስጋ ተገፋ። ከአይን እና ጥቂት የአንገት እንቅስቃሴ በስተቀር ሚስቴ የለችም። በአንሶላ ወጥረን አነሳናት። ባል ነኝና አስደበረኝ ይሔም። ባል "በኔ ብቻ የመጣ አይደለም" እያለ ልቡን ይደግፍ።
.
እያሾፍኩ መሆኑ የገባኝ ቆይቶ ነው።
.
ከተቀደደችበት ቦታ ይልቅ አድባ እንድትቀደድ የረዳት ያ መርፌ ለካ አሻራው ቀላል አይደለም። ቁስሉ ደርቆ ተንቀሳቀሽ ሲሏት የስለት ዣንጥላ ይመስል ታጥፋ ተነሳች። ሚስቴም እንደ ልጄ አንገቷን በራሷ መደገፍ የተሳናት ሆነች።
.
የማስታገሻ አይነት ዋጠች ማስታገሻው ያደረሰውን ጉዳት ልታስታግስ። ራስምታቱ ደሞ ሌላ ነው። በዛ ላይ ደሙ እንዲወርድ እያሉ ሆዷን እንደምለዋ ያሹታል። ቆጣ ያለ ዶክተር መጥቶ "ተነስተሽ ወክ አድርጊ" ይላል።
.
ጌታሆይ!🥺
እኔስ ግዜ ምን እያደረግኩ ነው?...
ከየአቅጣጫው #እንኳን_ደስ_አለህ እየወረደብኝ። "ታድለህ ሴትናትንዴ" ታድለህ እየተባልኩ።
.
አሁን እኔም ወላጅ ነኝ አ? ወንድ አስወላጅ እንጂ ወላጅ ሊባል አይገባውም አልኩ ግራ ቀኙን ሳልገላመጥ። ለደስታዬ በረጨሁት እሷ ዘጠኝ ወር ቋቅ አላት። ወልዳም አታርፍ።
.
አዳም የሔዋን ባል በለስ ስላበላችው "አሳች" ብሏት ነበረ። ልጅ ስትወልድስ? #ሒወቴ_ነሽ አላት። #የህያዋን_ሁሉ_እናት_ነሽ ሲል ሔዋን አለ።
.
እንደ አዳም ሰራኝ። ለሰርጋችን እህቶቿ ፊት ፎቶ አንሺው ሳም ሲለኝ ያፈርኩ ሰውዬ እናቷ ፊት አይዞሽ እያልኩ ሳምኳት።
.
ለዘጠኝ ወር በጀርባና በሆዷ መተኛት ሲያምራት እየተገላበጥኩ ተኝቻለሁ ጎኗ። "ኧረ በቀኝ ጥሩ አይደለም" ሲሏት ጎድኗ እስኪያብጥ በአንድ በኩል ተሰየፈች። ከወለደች በሗላ ደሞ በግራና ቀኝ አይቻልም በጀርባሽ ያለትራስ ብለዋታል🥺
.
ሴት በመውለድ ትድናለች እንዲል ይህ መድሀኒት ይሁንልሸ!
.
የወለዳችሁ ሴቶች ለናንተ ትልቅ ክብር አለኝ🙏