ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አራት
በፀሎት ከጠፋች ከአንድ ሰዓት በኃላ ነበር አባትዬው ዜናውን የሰሙት፡፡በመጀመሪያ የቤቱ ሰው ሁሉ ያሰበው የተለመደው የልብ በሽተዋ ተነስቷባት ተዝለፍልፋ የሆነ ቦታ ወድቃ ይሆናል ተብሎ ነበር ፡፡ለአንድ ሰዓት ያህል ጋርዶቹ ፤ ዘበኞቹና አስተናጋጆቹ ሳይቀር የቤቱ ጥጋጥግ ከ50 በላይ ክፍሎች አንድ በአንድ እየከፈቱ አንድም ቦታ ሳይቀር ፈልገው ጅባት ካሉ በኃላ ነበር የጋርዶቹ ሀላቃ ፈራ ተባ እያለ የአቶ ኃይለመለኮትን መኝታ ቤት ያንኳኳው….በለሊት ልብሳቸው ሆነው የልጃቸውን የልደት በዓል ምክንያት በድካም የዛለ ሰውነታቸውን አልጋ ላይ አሳርፈው ገና እንቅልፍ እንዳሸለባቸው ነበር በራፋቸው የተንኳኳው…በመጀመሪያ በህልማቸው መስሏቸው ነበር፡፡ በኃላ ግን የምርም ክፍላቸው እየተንኳኳ መኆኑን ገባቸውና እየተነጫነጩ አልጋቸውን ለቀው በንዴት ውስጥ ሆነው በራፉ ሊከፍቱ እየሄዱ ባሉበት ቅፅበት ከመኝታ ቤታቸው ቀጥሎ ካለው ከፍል ውስጥ ያሉት ወ.ሮ ስንዱ ድምፅ ሰምተውና ደንግጠው ክፍላቸውን ከፍተው እየወጡ ነበር፡፡ ሁለቱም በአንድ ጊዜ እያንኳኳ ያለው ጋርድ ላይ አፈጠጡበት፡፡
‹‹ምን ተፈጥሮ ነው?››
‹‹ጋሼ..እንዴት እንደሆነ አናውቅም…..ልጆቹ እየተከታተሏት ነበር….››ለማስረዳት አስቦ መንተባተብ ጀመረ..፡፡
‹‹ምን እያወራህ ነው?››
‹‹በፀሎት..››
‹‹በፀሎት ..ልጄ ምን ሆነች..?አመማት እንዴ…?የልብ ህመሟ ተቀሰቀሰባት?››እናትዬው በመርበትበት በጥያቄ አጣደፉት፡፡
‹‹አይ አላመማትም…ላለፉት አንድ ሰዓት ውስጥ ስንፈልጋት ነበር…የለችም…››
‹‹የለችም ማለት…….?››
‹‹ጓደኞቾ ደብቀው ይዘዋት ሄደው መሰለኝ…. ግቢው ውስጥ የለችም፡፡››
‹‹እንዴ ..ይሄ ምን ማለት ነው..?ያን ሁሉ ጠብደል ጎረምሳ በጠባቂነት የቀጠርኩት እንዲህ አይነት ነገር እንዲከሰት ነው እንዴ…?ሰውዬ የእያንዳንዳችሁን ግንባር በሽጉጥ ሳልነድልላችሁ ልጄን ካለችበት ፈልጉና አስረክቡኝ…፡፡››በመራር ንግግር ቀድሞም የደነገጠውን ሰውዬ ይበልጥ ፍርሀት ለቀቁበት፡፡
‹‹እሺ ጌታዬ… ሁሉም ሰው እየፈለጋት ነው፣ይሄንን ነገር እርሶም በሰዓቱ መስማት አለቦት ብዬ ነው ቀድሜ ያሳወቅኳት…››
‹‹ወይኔ ልጄን..ይሄ የእነሱ ሳይሆን ያንተ ጥፋት ነው…››እናትዬው ቁጣቸውን ወደባላቸው አዞሩት፡፡
‹‹ይሄ ደግሞ ምን ማለት ነው?››ባልና ሚስቶች የተለመደውን ጭቅጭቃቸውን ቀጠሉ፡፡
‹‹ልጄን እንደከብት እረኛ ቀጥረህባት ስታጨናንቃት ነው ለዚህ ያበቃችው፡፡››
‹‹ሴትዬ እስኪ አሁን ተይኝ….እኔ ለራሴ ግራ ገብቶኛል ይበልጥ ግራ አታጋቢኝ.››አሉን ፊት ለፊት እየሄደ ያለውን ጋርድ ተከትለው ኮሪደሩን አቆርጠው መሄድ ጀመሩ..፡፡ወ.ሮ ስንዱም ማጉረምረማቸውን በለቅሶ አጅበው የለበሱትን ቢጃማ እንኳን ሳይቀይሩ ከኃላ መከተል ጀመሩ…፡፡በፀሎት ግን ለሊቱን ሙሉ ብትፈለግ ..በየወዳጅ ዘመድ ቤት ቢደወል…በከተማ አውራ ጎዳናዎች ከሰላሳ በላይ መኪኖችን ተሰማርቶ ብትፈለግ ድካዋን ለማግኘት አልተቻለም…
በስተመጨረሻ የግቢው ካሜራ ቅጂ ለሁለተኛ ጊዜ በዝግታ ሲታይ ነው እራሷን በአለባበሶ ቀይራ ብቻዋን በሞተር ሳይክል ግቢውን ለቃ እንደወጣች የታወቀው፡፡ይሄ ደግሞ በቤተሰቡ ላይ የነበረውን ድንጋጤና ፍራቻ ይበልጥ አናረው..ምክንቱም አወጣጧ አስባባት መሆኑን ስለተረዱ….፡፡ከዛ አባትዬው አቶ ኃይለመለኮት ያላቸውን ተሰሚነትና ከመንግስት ሰዎች ጋር ያላቸውን ትስስር በመጠቀም ለእያንዳንዱ ፖሊስና ትራፊክ ፖሊስ ፎቶዋና የሞተር አይነትና ታርጋ ቁጥሩ ተበትኖ እንድትፈለግ መመሪያ እንዲተላለፍ ተደረገ ፡፡
በማግስቱም ምንም ፍንጭ ሳይገኝ በመንጋቱ እቤቱ ሁሉ በወዳጅ ዘመድ ተጨናነቀ፡፡..ወላጆቹ በስጋትና ፍራቻ ብቻ ሳይሆን በሰው ትንፋሽም መፈናፈኛ አጣ…አቶ ኃይለመለኮት ሲጨንቃቸው ከአጀቡ ተነጥለው ቀጥታ ወደልጃቸው መኝታ ቤት ገብና ከውስጥ ዘግታው አልጋዋ ጠርዝ ላይ ቁጭ ብለው ግድግዳው ላይ የተለጠፈውን ግዙፍ የልጃቸውን ፎቶ እየተመለከቱ በትካዜ መንሳፈፍ ጀመሩ....እንባቸው መቆጣጠር አልተቻላቸውም…እንደህፃን ልጅ ነው ተንሰቅስቀው ያለቀሱት….በህይወታቸው እንዲህ አይነት ለቅሶ መቼ እንዳለቀሱ ፍጽም ትዝ አይላቸውም….አዎ ልጃቸው የልብ ንቅለተከላ በተደረገላት ጊዜ በህይወታቸው በጣም ያዘኑበትና የተጨናነቁበት ጊዜ ነበር…በቀሪ ህይወታቸውም መቼም ተመሳሳይ ሀዘን ውስጥ እገባለሁ የሚል ግምት አልነበራቸውም….ግን ተሳስተው ነበረ..አሁን ያሉበት ጭንቀትና ስጋት ከዛን ጊዜም ከፍ ያለ ነው…. ፡፡ልጃቸው አንድ ነገር ብትሆን ምን እንደሚሆኑ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም..፡፡ግን በእርግጠኝነት ሌላ ኃይለመለኮት እንደሚሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው..ምን አልባት አብደው ጨርቃቸውን ሊጥሉ ይችሉ ይሆናል...ወይንም ንዴታምና አውሬ አይነት ሰው ሊሆኑ ይችላሉ ….ልባቸው ፍስስ እያለባቸው ነው….አይናቸውን ከወዲህ ወዲያ እያሽከረከሩ የልጃቸውን እቃዎች በስስት ሲቃኙ አይናቸው አንድ ፖስታ ላይ አረፈ..በድንጋጤ ተነሱና ወደእዛው ተራመድ፡፡ አነሱት… ሁለት ነው…፡፡ከላዩ ላይ የተፀፈውን አነበቡት..፣አንደኛው ለአባዬ ይላል…ሁለተኛውን አዩት ለእማዬ ይላል…እሱን ጠረጴዛው ላይ መልሰው አስቀመጡና ለእሷቸው የተጻፈውን ይዘው ወደአልጋ ጠርዝ ተመላሱና ፖስታውን ቀደው ወረቀቱን በማውጣት ማንበብ ጀመሩ፡፡
አባዬ….እንዴት እንደምወድህ ታውቃለህ አይደል? በጣም ነው የምወድህ..ግን ሁሌ ትናፍቀኛለህ…፡፡ሁሌ እሩቅ ውጭ ሀገር ያለህ ነው የሚመስለኝ….እቤት እያለህ እራሱ የሌለህ መስሎ ነው የሚሰማኝ…እርግጥ አንተ ሁሉ ነገር ተሟልቶልኝ በቅምጥል የምኖር ደስተኛ
ልጅ ነው የምመስልህ…እየቀያየርኩ ምነዳችወ ከሶስት በላይ ዘማናዊ መኪናዎች አሉኝ፣በወር ከመቶ ሺ ብር በላይ በእጄ ይሰጠኛል….በየሄድኩበት እየሄዱ የሚጠብቁኝ ቁጥራቸውን የማላውቃቸው ጋርዶች አሉኝ……በአመት ሁለትና ሶስት ጊዜ የፈለኩትን ውጭ ሀገር ሄጂ እዝናናለሁ…በአጠቃላይ ኑሮዬ ለአብዛኛው ኢትዬጵያዊ በተረት አለም እንኳን ሰምቶት የማያውቀው የህልም አለም አይነት ነው…ግን እኔ በእድሜዬ እናትና አባቴ ሲሳሳሙ አይቼ የማላውቅ ልጅ እንደሆኑክ ማንም አያውቅም..አረ መሳሳሙ ይቅር አንድ መኝታ ቤት ውስጥ አብረው ሲያድሩ አይቼ አላውቅም… አይገርምም…..፡፡
አባዬ ልጅ ሆኜ እርግቤ እያልክ ነበር የምትጠራኝ..እርግቤ ስትልኝ እንዴት እንደምደሰት አታውቅም ፡፡የእውነትም ያንተ ነጭ እርግብ ሆኜ አድማሱን ሰንጥቄ በሰማይ መብረር የምችልና ጨረቃ ጋር ደርሼ ከዋክብቶችን ጨብጬ ምጫወትባቸው ይመስለኝ ነበር…ባቃ ትንሽ መልአክ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ነበር የምታደርገው..ግን አባዬ አንተ ያልተረዳኸውነ ነገር እኔ ከ19 ዓመቴ በኃላ ማለቴ የሌላ ሴት ከሰውነቴ ካወሀድኩ ጀምሮ እኔ እኔን አይደለሁም…..ትዝ ይልሀል እርግቤ አትበለኝ በስሜ ጥራኝ ብዬ ያስተውኩህ እራሴው ነኝ..ለምን ብለህ ጠይቀኸኝ ግን አታውቅም..ምን አልባት ዝም ብዬ እርግቤ የሚለው ሰም ደስ ስለማይለኝ መስሎህ ሊሆን ይችላል እንደዛ ግን አይደለም….ከልብ ነቅለ-ተከላ ከተደረገልኝ በኃላ ክንፏ የተሰበረባት መብረር የማትችል እና በየጓሮ የምትንፏቀቅ እርግብ እንደሆንኩ እየተሰማኝ ስለመጣ ነው ያስቆምኩህ..ለአንድ ልጅ እኮ በሰማይ እንዳሻት እንድትበር የሚያደርጋት የአባቷ ፍቅር ቀኝ ክንፍ እና የእናቷ ፍቅር ግራ ክንፍ ሲሆናት ነው….የወላጆቾ ፍቅር ነው እንድትበር የሚያደርጋት….ያ እንደሌለኝ ስረዳ ነው ስሙ ያስጠላኝ፡፡ለምን እንደሆነ አላውቅም ከድሮዬ በተለየ ፍቅር