አዳማ ላይ የተዘጋጀው ኮንፈረንስ ታገደ! ከኩሪፍቱም ቃለ ህይወት መረጃ አለን!
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የዳግ ሂዋርድን የአዳማ ኮንፈረንስ እንደማይቀበለው ፣ እውቅናም እንደማይሰጠው ተናግሯል። የምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ማስተባበሪያ የካውንስሉ ፅህፈት ቤት ለኮንፍራንሱ የድጋፍ ደብዳቤ የፃፈው ዋናውን ፅህፈት ቤት ሳያናግር መሆኑን ገልጿል። መግለጫው መንጋውን ከመጠበቅ አንፃር ጥሩ የሚባል ነው። ካውንስሉ ዳግ ሂዋርድን የማይቀበለው 7ቱን ካውንስሉ የተቋቋመባቸውን አዕማዶችን በአስተምህሮቱ የሚጥስ በመሆኑ ነው ሲል ቄስ ደረጀ ጀምበሩ ተናግረዋል። ዳግ ሂዋርድ እነዚህን 7ቱን መሰረታዊ አእማዶችን የሚጥስ እንደሆነ ይታወቃል።
በሌላ ዜና የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ኩሪፍቱ አጥቢያ ዛሬ መግለጫ የሰጠች ሲሆን በኮሪደር ልማት ምክንያት የተጀመረው የአጥር ማስጠጋት እንዲሁም በዚህ ላይ ተንተርሰው የከተማዋ ከንቲባ የ20,000 ካሬ ሜትን የቦታ ንጥቂያ ለህግ የቀረበ ሲሆን ቦታውን ችካል ቸክለው የቆረሱት ግለሰቦች በፍርድ ቤት እገዳ የወጣባቸው ሲሆን ቦታው ላይ ምንም እንቅስቃሴ እያደረጉም አይደለም ሲል ዶ/ር ሰለሞን ሙላቱ ተናግረዋል።
ምንጭ : የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ካውንስል በማርከን ዘጋቢ Gift የተተነተነ
ክርስቲያናዊ መረጃ በፍጥነት
መረጃም ካላችሁ በinbox ማለትም @Gift29 ላኩልን እናሳውቃለን❤️
@Markengeta