ልባችሁ አይታወክ ብንኖር ለወንድማችን ጥቅም ብንሞት ለኛ ጥቅም!
አንድ ሰሞን ክርስትናዬን የፈተነ አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር አንዲት መልካም ለእግዚአብሔር ጥሩ ቦታ ያላት ብዙ የተስፋ ቃላትን በየቸርቹ ሚነገራት መታ ምትነግረን አንዲት እህት ከቸርች ፕሮግራም ስትወጣ በመኪና አደጋ አረፈች በጣም ያዘንኩበት እና የአምላክ ቃል ይታጠፋል እንዴ? ብዬ ለሳምንታት የዛልኩበት ጥያቄዬ ነበር ቆይቶ የገባኝ ግን እግዚአብሔር ልክ እንደሆነ ነው።የሚወደውን የመረጠውን ሰው እግዚአብሔር በፈለገው መንገድ ወደ ራሱ ይጠራል ብዛት አብረውት ያገለገሉት ሀዋርያት ወደ ጌታ የሄዱበት መንገድ በጣም ዘግናኝ ነው።ይህ ስጋችን ሰማይ ላለው ህያው ለሆነው አካል ምንም ድርሻ የለውም(ይህን ስል ደግሞ በዚህ አካላችን በሀጢያት እንዛል እያልኩኝ ሳይሆን አፈር የሆነውን ይህን ስጋ እዚሁ እንጥላለን ማለቴ ነው) ብቻ የነፍሳችንን ብስለት እና እድገትን እንጠብቅ እንጂ እግዚአብሔር በወደደው መንገድ ወደራሱ ይጠራናል።ወዳጄ ጳውሎስ እንዳለው እዚህ የመኖራችን ትልቁ በረከትነቱ አጠገባችን ላለው ወንድማችን ጥቅም ነው እንጂ የሰማዩ ለኛ ተስማሚ ነው።እግዚአብሔር በፈቀደው ቀን ሰአት ወደራሱ ይሳበን እንጂ ለምን በመጋዝ አይሰነጥቁንም ከፈለጉ ዘቅዝቀው አይሰቅሉንም ሽልማታችን ይህ ስጋ አይደለም ብዙ አክሊል አለን። ሳጠቃልለው ወደጌታ የሄድንበት መንገድ ሀጢያተኛነታችንን ወይም ፅድቃችንን አያሳይም በጣም ብዙ አገልጋዩችም ሆኑ በእግዚአብሔር ቤት የተባረኩ አባቶች እናቶች ብዙ ቦታ ምንጠብቃቸው ወጣት አገልጋዩች በመኪና አደጋ እንዲሁም በተለያዩ ከባባድ አደጋዎች ወደ ጌታ ሄደዋል። በምድር ስንኖር በሚገባ ለእግዚአብሔር እንኑር።
በእንደዚህ አይነት ሀዘን ያላችሁ እስቲ ታሪካችሁን ኮሜንት ላይ አጋሩን እንዴትስ ተፅናናችሁ?
BROTHER GIFT
@Markengeta