ስኬትን የፈለገ የሰለፎችን መንገድ ይከተል


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ዐዋቂዎች አይደለንም አህሉል ቢድዓ ግን አይሸውደንም፡፡
[]~ ሰለፍያ~[]
የልባሞች እምነት የጀግኖች ጎዳና
መመሪያሽ ቁርአን የነቢዩ ሡና
በሀቅ የተካብሽው መጠለያ ቤቴ
ከጥመት መሸሻ ብርሀነ-ንጋቴ
ሁሌም የበላይ ነሽ ኢስላሜ ድምቀቴ
መንሀጀ-ሠለፍ ወሠጢያ እምነቴ!!
https://t.me/Menhaj_Asselefiya

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ምዕራፍ 3 የደዕዋ ግልፅ መውጣት

ክፍል 17 ሙርሊሞቹን ማሰቃየት

ሙስሊሞችን መቅጣትና ማሰቃየት በሚዘገንን ሁኔታ ቀጠለበት።

፨ቢላል ቢን ረባህ(ረ አ)የኡመያ ቢን ኸለፍ አልጁመሒ ባሪያ ነበረ። ኡመያ ቢላልን አንገቱ ላይ ገመድ በማድረግ ለልጆች ይሰጧቸዋል ልጆች እየጎተቱ ይጫወቱበቴል። እሱግን "አሐድ አሐድ " ይል ነበር። በእኩለቀን በጠራራ ፀሀይ ይዞት ይወጣና በጣም የሚያቃጥል ድንጋይ ወይም አሸዋ ላይ በጀርባው ያስተኛዋል። ከዚዬም በጣም ትልቅ ድንጋይ አስመጥቶ በደረቱላይ ያስቀምጣል። ከዚያም እንድህ ይለዋል። እስከምትሞት ድረስ ወይም በሙሐመድ ክደህ (ከፍረህ)አል-ላትና አል-ዑዛን እስከምትገዛ ድረስ በዚህ ሁኔታ ትቆያለህ ይለዋል። እሱ ግን "አሐድ አሐድ" (አንዱ አምላክ አንዱ አምላክ )ይል ነበር።

፨ከእለታት አንድ ቀን እንደዚሁ ሲያሰቃዩት አቡበክር (ረ.ዐ) በአጠገቡ አለፉና ገዝተውት ከባርነት አወጡት።

፨ዐሚር ቢን ፉሃይራ ራሱን እስኪስትና የሚናገረውንም ማወቅ እስኪሳነው ድረስ ይሰቃይና ይቀጣ ነበር።

፨አቡፉከይሃም ተሰቃየ።ስሙ አፍለህ ይባላል። ከአዝድ ጎሳ ነው ተብሏል። የበኒ ዐብድዳር ባሪያ ነበር። በሀይለኛ ሙቀት በእኩለቀን ላይ እግሩን በብረት አስረውት ራቁቱን አስወጥተውት በሆዱ በቃጠሎ አሸዋ ላይ ዬስተኙታል። ከዚያም መንቀሳቀስ እንዳይችል ትልቅ ድንጋይ ከጀርባውላይ ያደርጋሉ። ራሱን እስኪስት ድረስ በዚህ ሁኔታ ይቆያል። በሁለተኛው ሂጅራ (ስደት)ወደ ሃበሻ እስከተሰደደበት ጊዜ ድረስ በዚህ መልኩ ሲሰቃይ ቆየ። አንድ ጊዜ ሁለት እግሮቹን በገመድ በማሰር ጎትተውት በአሸዋ ላይ ጣሉት። ከዚያም ሙቷል ብለው እስኪጠረጥሩ ድረስ አነቁት።  አቡበክር በዚህ ሁኔታ ሲያዩት ገዙትና ነፃ አወጡት።

፨ኸባብ ቢን አል አረት በጃሂልያ ዘመን ከተማረኩት ሰዎች አንዱ ነበር። ኡሙ አንማር ቢንት ሲባዕ አል ኹዘዒያ ገዛችው። ቀጥቃጭ ነበር። እሱ ሙስሊም ሲሆን አሳዳሪው እሙ ዐንማር በእሳት አሰቃየችው። በሙሀመድ(ﷺ) እንዲከፍር በእሳት በቀላ ብረት ጀርባውን ትጣብሰው ነበር ።ይህም ቢሆን ኢማንንና ለአላህ እጅ መስጠትን እንጂ ሌላ አልጨመረለትም ።ሌሎች ሙሽሪኮችም አንገቱን እየጠመዘዙ ጸጉርን እየነጩ በተደጋጋሚ በተቀጣጠለ ከሰል ላይ እየወረወሩት ያሰቃዩት ነበር።  ከዛ በጣም ከባድ ድንጋይ በደረቱ ላይ ሲያስቀምጡበት መነሳት ያቅተዋል።

፨ ዘኒራ ሮማዊ ባሪያ ነበረች። ሰለመች። ለአላህ ስትል ተሰቃየች ።አይዋንም ታማ ታወረች ።አል ላትና አል ዑዛ ናቸው አይንሽን ያሳወሩሽ ተባለች ።በፍጹም አላህ እንጂ እነሱ አይደሉም ከፈለገ ይከፍትልኛል አለች። በ በማግስቱ ጧት አላህ አይኗን መለሰላት።ይህ ከመሐመድ ድግምቶች አንዱ ነው አሉ።

፨ ኡሙ ዑበይስ  ሰለመች። የበኒ  ዙህራ ባሪያ ነበረች ።ጌታዋ አል አስድ ቢን አብድ የጉስ ያሰቃያት ነበረ።ከአላሆ መልክተኛ (ﷺ)ቀንደኛ ጠላቶችና በሳቸው ከሚሳለቁት  ሰዎች አንዱ ነበር።

፨ ከበኒ አዲይ የአምር ቢን ሙአምሚል ባሪያ (ጃሪየቱ አምር ቢን ሙአምሚል ሰለመች። ኡመር ቢን አልኸጣብ በዚያን ጊዜ ስላልሰለሙ የመሰቃዯት ነበር።እስከሚደክማቸው ድረስ ይደበድቧትና ይተዋታል።ከዛያም ስለ ሰለቸኝ እንጂ አልተውሽም ነበር ይሏታል።እኔን እንደቀጣሃኝ አላህ ይቀጣሃል ትላቸው ነበር። 

፨ሰልመው ከተሰቃዩት ሴት ባሪያዎች ናህዲያና ሴት ልጅዋ ይጠቀሳሉ።የአንዲት የበኒ አብድዳር ሴት ወይዘሮ ነበሩ። አቡበክር(ረ.ዐ)ኣሚር ቢን ፉሃይራንና አቡ ፋከይሃን ገዝተው ከባርነት እንዳወጧቸው ሁሉ እነዚህንም ሴት ባሮች ገዝተው ከባርነት ነፃ አወጧቸው።አባታቸው አቡ ቁሃፋ አቢበክርን ደካሞች ባሮችን ነፃ ታወጣቸዋለህ። ጠንካራ ጠንካራ ወንዶች ባሮቾን ነፃ ብታወጣ ይከላከሉልሃል፣ይረዱሃል፣እያሉ ይወቅሷቸውነበር። መልሳቸውግን እኔ የአላህነረ ውደታ ነው የምፈልገው ነበር።አላህ(ሱ.ወ)አቡበክርን...........ይቀጥላል

https://t.me/Menhaj_Asselefiya


ምዕራፍ 3 የደዕዋ ግልፅ መውጣት

ክፍል 16 የተውሂድ ጉዳይ አብይ የመወያያ ርዕስና የልዩነት መሠረት ነበር


ነቢዩ (ﷺ)ወደ አላህ አንድነት መጣራታቸውና ሙሽሪኮቹ ከአላህ በስተቀር አማልክት አድርገው የያዙአቸውን ሁሉ እሳቸው መተዋቸው ለሙሽሪኮቹ ከከበዳቸው ተቃወሙትም። ከሚባለውነገር ወይም በአፍ ከሚነገረው የተለየና የታሰበ ተንኮል አለው አሉ።እንድህም አለ፦

أَجَعَلَ ٱلْأَلِهَةَ إَلَٰهࣰا وَٰحِدًاۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَیْءٌ عُجَابࣱ۝٥وَٱنطَلَقَ الْمَلَأُ مِنْهُمْ أَنِ ٱمْشُوٱ وَٱصْبِرُ وا عَلَیٓ ءَالِهَتِكُمْۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَیْءࣱ يُرَادُ۝٦ مَاسَمِعّنَا بِهَذَٰا فِی ٱلْمِلَّةِ ٱلْأَخِرَةِ إِنْ هَٰذَآ إِلَّا ٱخْتِلَٰقࣱ۝٧

አማልክቶቹን አንድ አምላክ አደረጋቸውን ?ይህ
ስደናቂ ነገር ነው (አሉ)።ከነሱም መኳንንንቶች፦ሂዱ፣በአማልክቶቻችሁም (መገዛት)ላይ ታገሱ ይህ (ከኛ)የሚፈለግ ነገር ነውና(ይህ እኛን ከአማልክቶቻችን ለመለየት ተብሎ የተጠነሰሰ ተንኮልኘው )እየተባባሉ አዘገሙ።ይህንንም በኋለኛይቱ ሃይማኖት አልሰማንም ይህ ውሸትን መፍጠር እንጂ ሌላ አይደለም።(እያሉም)።(ሷድ 38:5-7)

ከዚያም ዳእዋው ሲቀጥልና ሙሽሪኮቹም ከሽርካቸው ለመከላከል፣ዳእዋውን ለመግታት፣ከሙስሊሞቹ ጋር መከራከርና የዳእዋውን ፍሬ ከሙስሊሞቹ ውስጥ ለማጥፋት ሲወስኑ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ማስረጃዎችና መመለስ የማይችሉ ጥያቄዎች መጡባቸው።እንድህ ተባሉ፦በፍጥረታት ውስጥ የሚፈልጉትን ነገር እንድያደርጉ አላህ ለባለሟሎቹ ባሮች ሥልጣን ሰጥቷቸዋል የሚለውን ከየት አወቃችሁ? እናንተ በሚትሉት መሠረት ጉዳዮችን መፈፀምና ጭንቅን የማስወገድ ሥልጣን እንደተሰጣቸው ከየት አወቃችሁ? የሩቁን ምሥጢር (ገይብ)አወቃችሁን?ወይስ ከነቢያትና ከእውቀት ባለቤቶች ከወረሷችሁ መፅሀፍ አገኛችሁት?

አላህ እንድህ አለ፦

أَمْ عِندَهُمُ ٱلْغَيْبُ فَهُمْ يَكْتُبُونَ۝٤١ 

ወይስ እነሱ የሚፅፉት የሆነ ገይብ (የሩቅ ሚስጢር)እነርሱ ዘንድ አለን?(ሊፅፉት የሚችሉ የገይብ እውቀት አላቸውን?)
                   አልጡር 52:41እና አል ቀለም 68:47


ٱءْتُونِی بِكِتَٰبࣲ مِّن قَبْلِ هَٰذآ أَوْ أَثَٰرَةࣲ مِّنْ عِلْمٍ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ۝٤ 

እውነተኞች እንደሆናችሁ ከዚህ (ቁርኣን)በፊት የሆነን መፅሀፍ ወይም ከእውቀት የሆነ ቅርስን አምጡልኝ በላቸው።(አል-አህቃፍ 46:4)

قُلْ هَلْ عِندَكُم مِّنْ عِلْمࣲ فَتَخْرِجُوهُ لَنَآۖ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَإِنْ أَنتُمْ إِلَّا تَخْرُصُونَ۝١٤٨

......(አላህ ማጋራታችሁን መውደዱ) አውጥታችሁ ልታሳዩን የምችችሉ የሆነን እውቀት አላችሁን?ጥርጣሬን እንጂ ሌላን አትከተሉም፣ እናንተ ዋሾዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም። (አል አንኣም 6:148)

ሙሽሪኮች የሩቅን ሚስጥር (ገይብ)አለማወቃቸውን ከነቢያት መፃህፍትም ባንዱም መፅሀፍ ውስጥ እንዳላገኙና ከእውቀት ባለቤቶችም እንዳላገኙ ማመናቸው ተገቢና የማይቀር ነው። ስለዚህም እንድህ አሉ፦

وَأِذَا قِيلَ لَهُمْ ٱتَّبِعُوٱ مَآ أَنزَلَ اللَّهُ قَالُوٱ بَلْ مَا وَجَدْنَا عَلَيْهِ ءَابَآءَنَآ۝٢١

አይደለም በርሱላይ አባቶቻችንን ያገኘንበትን እንከተላለን ይላሉ.....
                        (ሉቅማን 31:21)


إِنَّا وَجَدْنَآ ءَابَآءَنَا عَلَیٰٓ أُمَّةࣲ وَإِنَّا عَلَیٰٓ ءَاثَٰرِهِم مُهْتَدُونَ ۝٢٢
ከቶውንም እኛ አባቶቻችንን በሃይማኖት ላይ አገኘናቸው ። እኛም በፈላጎታቸው ላይ ተመሪዎች ነን አሉ።(አል-ዙኽሩፍ (43:22)

በዚህ ምላሳቸው ምንም ያለመቻላቸውና ያለማወቃቸው ግልፅ ሆነ። ስለዚህም እንደዚህ ተባሉ ፦አላህ ያውቃል እናንተ አታውቁም ።ስለዚህ እርሱ የሚነግራችሁን ስለነዚህ ተጋሪዎቻችሁ እውነታና ማንነት አዳምጡት።አላህ እንድህ ይላል፦

إِنَّ ٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللّهِ  عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْۖ ۝١٩٤
እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ብጤዎቻችሁ ተገዠዎች ናቸው (አል-አዕራፍ 7:194)

           ይቀጥላል.............

https://t.me/Menhaj_Asselefiya


ደከምኩኝ አትበል !!
ግጥም

✍🎙አብዱ ሽኩር አቡ ፈዉዛን

t.me/abu_fewzan_abdu_shikur
t.me/abu_fewzan_abdu_shikur


ትዳር እና ኢስላም 🌷🌹🥀 dan repost
📣  🎈ተጀመረ ⭐️🔈
​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•

ርዕስ :- ስለ ኢማሙ አህመድ ታሪክ🎤

📚 ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ሀሰን⭐️
      ተ
⭐️
             ጀ
⭐️
                  መ
⭐️
                          ረ
⭐️
ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም!

ሊንኩን ለሌሎችም ሼር አድርጉት‼

 ➘  ➘ ➘ ➘➘ ➘ ➘ ➘  ➘ ➘ ➘➘ ➘
https://t.me/tdarna_islam?livestream
https://t.me/tdarna_islam?livestream


⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️📡

አዲስ የሙሀደራ ፕሮግራም

በትዳር እና ኢስላም ቻናል

ተጋባዥ ኡስታዞች
⭐️
➡️አብዱ ሸኩር አቡ ፈውዛን
➡️ዶክተር ሰኢድ ሙሳ
➡️አቡ ዑበይዳህ

ርዕስ በሰአቱ ይገለፃል ➷

✅ቀን እና ሰዓት ዛሬ ጁማዐ
ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ➡️

✅የሚተላለፍበት ቻናል✨
⭐️ t.me/tdarna_islam
t.me/tdarna_islam ⭐️


ምዕሬፍ 3 የደዕዋ ግልፅ መውጣት

ክፍል 15 የተውሂድ ጉዳይ አብይ የመወያያ ርዕስና የልዩነት መሠረት ነበር


የእርሻውን ውጤት አትክልቱንም፣እህሉንም፣መጠጡንም ወርቁንም ብሩንም ፣እቃውንም፣ገንዘቡንም ወደ እነዚህ የሷሊሆች ቦታዎች፣መቃብሮችና ምስሎች የሚያቀርቡት በመቃብሮቹና ቦታዎቹ አካባቢ ቸጎራብተው በሚኖሩ ሰዎች አማካኝነት ነው።በአብዛኛው ጊዜ በነሱ አማካኝነትና አገናኝነት (ዋሲጣ)ካልሆነ በስተቀር አይቀርብም።

እንስሳቶችን ግን ለነዚህ ሷሊሆች የሚያቀርቡበት ሌላም ወደ አላቸው። በነዚህ ባለ መቃብሮች ና ምስሎች ሷሊሆች ስም እንስሳዋን ይለቋታል፦ ወደነሱ ለመቃረብና ለመወደድ።ይቺን የተለቀቀችውን እንስሳ ያከብሯታል፣በፍፁም በክፉ አይነኳትም፣የፈለገችውን ትበላለች፣ወደ ፈለገችው ቦታ ትዘዋወራለች። በመጨረሻም በነዚህ ወልዮች መቃብሮችና ለነሱ በተለዩ ቦታዎች ላይ ያርዷታል።ወይም ደግሞ በሌላም ቦታ ሊያርዷት ይችላሉ ነገርግን በሚያርዷት ጊዜ በአላህ (ﷻ)ስም ፋንታ የነዚያን ወልዮቾና ሷሊሆች ስሞች ይጠራሉ።

ከሚያደርጉት ስራዎች አንዱ በነዚህ ወልዮችና ሷሊሆች ምክንያት በገነት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ በአላትን ማዘጋጀት ነበር። ሰዎች ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደነዚህ መቃብሮችና ለነሱ ወደተለዩት ቦታዎችበመሄድና በተለየ ቀናት በመሠብሠብ በአላትን ያከብራሉ። ከላይ በጠቀስነው መሠረት ለበረካ በማለት መቃብሮቹንና ቦታዎቹን ያብሳሉ፣ይዞራሉ፣ስለቶችንና ቁርባኖችን ያቀርባሉ። ልክ እንደ ሀጅ የቅርቡም ሆነ የሩቁ፣ሀብታሙም ሆነ ደሀውም ይገኙበታል። ስለቶቻቸውን አቅርበው የሚፈልጉትን ነገር ለማግኘት ሲሉ ሁሊም ይጎርፉበታል።

ሙሽሪኮች ለነዚህ አውሊያ እና ሷሊሂን ይህን ሁሉ የሚያደርጉት ወደነሱ በመቅረብና በመወደድ ከአላህ ጋር እንድያቃርቧቸውና በበላህና በነሱ መሀል አገናኞች እንድሆኑላቸው ነው። ወደ አላህ ያቀርባሉ በአላህ ዘንድም ያማልዳሉ ብለው ያምናሉ። በራሳቸውም ሆነ በማማለድ የተነገራቸውን ነግር ሰምተው ለተጠየቁት ነገረ መልስ መስጠት፣ጉዳዮችን መፈፀምና ጭንቅንም ማስወገድ ይችላሉ ብለው ያምኑ ስለነበር ጉዳዮቻቸውን (ሃጃዎቻቸውን) እንድፈፅሙላቸውና ጭንቅ እንድያስወግዱላቸው ይጠሯቸው ነበር።

ይህነበር በአላህ ማጋራቸው፣ከአላህ ሌላ መገዛታቸው፣ከአላህ ሌላ አምላክን መያዛቸውና  ለአላህ ሸሪኮችን ማድረጋቸው።እነዚህ ወልዮች (አውሊያዕ)፣ሷሊሆች (ሳሊሁ ን) እና የ
መሳሰሉትን የሙሽሪኮቹ አምላኮች ነበሩ።
ይቀጥላል.............
https://t.me/Menhaj_Asselefiya


ምዕራፍ 3 የደዕዋ ግልፅ መውጣት

ክፍል 14 የተውሂድ ጉዳይ አብይ የመወያያ ርዕስና የልዩነት መሠረት ነበር


ሙሽሪኮች የአላህን (ሱ.ወ)አንድነት ይቀበሉ ነበር። በዛት (በአካሉ)፣በሲፋቱ (በባህሪያቱ)እና በድርጊቶቹ አንድነቱን ይቀበሉ ነበር።አላሁ ተዓላ ፈጣሪ መሆኑን ሰማያትንና ምድርን፣በመካከላቸውም ያለውን ነገርና ሁሉንም ነገር የፈጠረ መሆኑን ያውቁና ይቀበሉት ነበር።የሁሉም ነገር ባለቤት መሆኑን፣የሰማያትና የምድር እንድሁም በመካከላቸው ያለውን ነገርም ሆነ የሁሉም ነገር ሥልጣን በእጁ መሆኑን፣ሰውን፣እንስሳትንና ሌሎች ሕይወት ያላቸውን ነገሮች በሙሉ የሚረዝቅ ፣ነገሩን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር የሚያዘጋጅ፣የትንሹንም ሆነ የትልቁን ነገር የብናኙንም ሆነ የጉንዳኑን ጉዳይ ሁሉ የሚያስተናብር፣ የሰማያትና የምድር፣ በመሀከላቸውም ያለው ነገር፣ የታላቁ አርሽና የሁሉም ነገር ጌታ መሆኑን፣ፀሀዩን ጨረቃውን ከዋክብቱን፣ዛፉን፣እንስሳቱን፣ጂኑን፣ሰውንና መላእክቱን፣ ሁሉ ያገራና ሁሉም ለሱ የሚተናነሱና የሚዋረዱ መሆኑን፣ የፈለገውን በፈለገው ላይ አሸናፊ የሚያደርግና በሱ ላይ ማንንም ምንንም በፍፁም አሸናፊ ማድረግ የማይቻል መሆኑን፣የሚያኖርና የሚገድል፣የፈለገውን የሚያደርግና የፈለገውን የሚፈርድ፣ለፍርዱም ተቺ የሌለውና ውሳኔው የማይመለስበት መሆኑን ይቀበሉ ነበር።

በዚህ መልኩ የአላህን አንድነት -በዛቱ፣በሲፋቱና በድርጊቱ-አንድነቱን በግልፅ ከተቀበሉ በኋላ እንድህ ይሉ ነበር፦አላህ ከባሮቹ እንደ ነቢያት፣ሩሱሎች፣ወልዮችና ሷሊሆች ባለሟሎች ስለ ፍጡሮቹ ጉዳይ የመፈፀም ከፊል ሥልጣን ይሠጣቸዋል። ልጅን መስጠት፣መከራን የመመለስ፣ጉዳዮችን የመፈፀም፣በሽተኛን የማዳንና የመሳሰሉትን ችሎታዎች በአላህ በአላህ ይሠጣሉ ። አላህ ይህን ሥልጣን የሰጣቸው ለሱ ቅርበት ስላላቸውና በሱ ዘንድ ስለተከበሩነው። አላህ ይህንን ስልጣንና ምርጫ ስለሰጣቸው ለሰው በማይታይና በማይታወቅ መንገድ(በገይብ)የባሮችን ጉዳዮች ይፈፅማሉ፣ጭንቅና መከራን ያነሱላችኋል፣የወደዱትን ሰው ወደ አላህ ያቃርባሉ፣ በአላህ ዘንድ ያማልዳሉ።ይሉ ነበር።

ሙዝሪኮች በዚህ አባባላቸው መሠረት እነዚህን ነቢያት፣ወሊዮችና ሷሊሆች ወደ አሏህ መቃረቢያ (ወሲላ) አደረጉዋቸው (ሙሽሪኮችንና አላህን የሚያቃርቡ ማለትነው።)ወደነዚህም የሚቀርቡበትንና ውደታቸውን የሚያገኙበትን ድርጊቶችንና ተግባራትን ፈጠሩ።እነዚህን ድርጊቶች ከፈፀሙ በኋላ ይተናነሱላቸዋል፣ጉዳዮቻቸውንም እንድፈፅሙላቸው ይለምኑዋቸዋል፣በመከራ ጊዜ እርዳታን ይጠይቁዋቸዋል፣በፍራቻ ጊዜም ይጠበቁባቸዋል(ጠብቁን) ይሉዋቸዋል።

ወደነዚህ ለመቃረብ የፈጠሩት ድርጊቶች ለነዚህ ነቢያት (አንቢያ) ወሊዮች፣(አውሊያ)እና ሷሊሆች (ሷሊሁን) የተወሰነ ቦታ ይመርጡላቸውና ቤቶችን ይገነለመቃረብና  ከዚያም በቤቶቹ ውስጥ ምስሎቻቸውን ሰርተው ያስቀምጣሉ። የሚቀርፁት ምስሎች የነቢያቶቹና የወሊዮቹ ትክክለኛ ምስሎች ወይም ሀሳባው ምስሎችናቸው። በነሱ አባባል የአንዳንዶቹን ወልዮችና ሳሊሆች መቃብሮች ሊያገኙ ይችላሉ። ይህ ከሆነ ግን ምስሎቻቸውን ሳይቀርፁላቸው ቤት ብቻ ይገነቡላቸዋል። ከዚያም ወደነዚህ ምስሎችና መቃብሮች በመሄድ በረከት(ረድኤት)ለማግኘት መቃብሮቹንና ምስሎቹን ያብሱዋቸዋል። ይዞሯቸዋል (ጠዋፍ)ያደርጉባቸዋል፣ያልቋቸዋል፣ያከብሯቸዋል፣ያወድሷቸዋል፣ወደነሱ ለመቃረብና ችሮታቸውን ለማግኘት ሲሉ ስለቶችንና ቁርባኖችን ያቀርቡላቸዋል። እነዚህ ሙሽሪኮች ለነዚህ ነገሮች የሚሳሉት አላህ ከሰጣቸው ሲሳዮች(ርዝቆች) ከእርሻው፣ከአትክልቱ፣ከእህሉ፣ከመጠጡ፣ከእንስሳቱ፣ከወርቁ፣ከብሩ፣ከእቃዎችና ከገንዘቦችነው። ይህን ሁሉ የሰጣቸው አላህ ሲሆን ለሌላ ስለት ወይም ነዝር ያደርጋሉ።
         ይቀጥላል

https://t.me/Menhaj_Asselefiya


ሙስሊም ካልሆነ ወንድ ጋር አጉል ቅርርብ ውስጥ የገባችሁ እህቶች በጊዜ ከሰመመናችሁ ውጡ። በፍቅር ምርቃና እንደ ዋዛ ያቆራረጡት አደገኛ መንገድ መመለስ ሲያስቡ ዳገቱ ልብን ሊፈትን ይችላል። ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው። መጨረሻችሁ ኩ- ፍ- ር ከመሆኑ በፊት በጊዜ ንቁ። ርቀቱ ሲጨምር መመለሻው ይከብዳል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️📡

⭐️የመተዋወሻ እና ለህፃን አቲካ
⭐️የትብብር  ፕሮግራም

በትዳር እና ኢስላም ቻናል

ኑ! በልብ ህመም እየተሰቃየች የምትገኘው ህፃን አቲካን ሰበብ እንሁናት

በእለቱም ተጋባዥ ኡስታዞች እና ወንድሞች:
⭐️
➡️ኡስታዝ አቡ ሂበተላህ🎤
➡️ኡስታዝ ዓብዱረዛቅ ባጂ 🎤
➡️ኡስታዝ ኢብራሂም ኸይረዲን 🎤
➡️ኡስታዝ አቡ ዑበይዳህ🎤
➡️አቡ ሁዘይፋህ (ሰዒድ)🎤
➡️አቡ ማሂ (ሙሐመድ ኢድሪስ)🎤

የህፃን አቲካ ህመም ምንድነው?👇
t.me/tdarna_islam/4859?single
t.me/tdarna_islam/4863
⬆️
✅ቀን እና ሰዓት ነገ እሁድ 22/03/2017
ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ➡️

✅የሚተላለፍበት ቻናል✨
⭐️ t.me/tdarna_islam href='https://t.me/tdarna_islam' rel='nofollow'>
      t.me/tdarna_islam ⭐️


ምዕራፍ 3 የደዕዋ ግልፅ መውጣት

ክፍል 13 ደዕዋን ለመዋጋት ቁረይሾች የተጠቀሙት የተለያዩ ዘደዎች


ይህም ማለት ወህይ፣ቁርኣን ፣ነቢይነት (ኑብዋ)እና መልእክተኛነት (ሪሳላ)የአላህ ችሮታዎች ስለሆኑ ችሮታውን እንዴት እንደሚያከፋፍል፣ የት እንደሚያስቀምጣቸው ፣ለማን እንደሚሰጣቸውና ማንን እንደሚከለክላቸው የሚያውቀው እርሱ አላህ ብቻነው። አላህ እንድህ ይላል፦

اللَّهُ أَعْلَمُ حَيْثُ يَجْعَلُ رِسَالَتَهُۗ۝١٢٤፡
አላህ መልእክቱን የሚያደርግበትን ስፍራ ይበልጥ አዋቂነው።( አል-አንኣም 6:124)

ከዚህ በኋላ ደግሞ ወደ ሌላ ማስመሰያ(ሹብሃ) ተዘዋወሩ። መልእክተኛ(ረሱል) መሆን ያለበት ከምድራዊ ነገስታት አንዱ ነው።በንግስናው ምክንያት ክብርንና ግርማን የተጎናፀፈ፣አገልጋዮች፣አጃቢዎች፣አትክልቶች ገንዘብና የመሳሰሉት ነገሮች ያሉት፣ግብርና ዝና ባላቸው ጠባቂዎችና አጃቢዎች ታጅቦ የሚሄድ መሆን አለበት አሉ።ሙሐመድ ደግሞ የእለት ጉርሻውን ለማግኘት በገበያ ውስጥ ከሰው ጋር እየተጋፋ የሚሄድ የአላህ መልእክተኛ ነኝ ይባላልን?አሉ።


لَوْ لَآ أُنزِلَ إِلَيْهِ مَلَكࣱ فَيَكُونَ مَعَهُ نَذِيرًا۝٧أَوْ يُلْقَیٓ إِلَيْهِ كَنزٌ أَوْ تَكُونُ لَهُ جَنَتٌّ يَأْكُلُ مِنْهَاۚ وَقَالَ ٱلظَّٰلِمُونَ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا رَجُلࣰا مَسْحُورًا۝٨

ከርሱ ጋር አስፈራሪ ይሆን ዘንድ ወርሱ መልአክ (በገሃድ)አይወርድም ኖሯልን?አሉ፦ወይም ወደርሱ ድልብ አይጣልለትንም?ወይም ከርሷ የሚበላላት አትክልት ለርሱ አትኖረውምን?(አሉ)በዳዮችም (ላመኑት)የተደገመበትን ሰው እንጂ ሌላን አትከተሉም አሉ። (አል ፉርቃን25:7-8)

ነቢዩ (ﷺ)ለሁሉም የሰው ልጅ አይነት፦ለትንሹም ለትልቁም፣ለደካማውም ለጠንካራውም፣ለተራውም ለክብሩም፣ለባሪያውም ለነፃውም (ለጨዋውም)የተላኩ መሆናቸው የሚታወቅነው ከላይ እንደተባለው ግርማ ያላቸውና የሚፈሩ፣በአገልጋዮች፣በአጃቢዎችና በታላላቆች የታጀቡ ቢሆን ኖሮ የኅብረተሰቡን አብዛኛውን ክፍል የሚወክሉት ደካሞችና ትንንሾች ሊጠቀሙባቸው ስለማይችሉ የሐልእክቱ(የሪሳላው)ዋና አላማ ሳይፈፅም ይቀር ነበር።እስካሁን የሚወሳና ሊጠቀስ የሚችል ጠቅም ባላስገኝም ነበር።ስለዚህም ሙሽሪኮች ለዚህ ጥያቄያቸው ሙሐመድ(ﷺ)መልእክተኛ ነው የሚል መልስ ነው የተሰጡት። በርግጥ መልእክተኛ መሆናቸው ሁሉንም የሙሽሪኮች ማምታቻ ጥያቄዎች ፉርሽ ለማድረግ በቂ ነው ።መልእክተኛ እንድኖሩት የጠየቃችሁት መፈራት፣ግርማ፣አጃቢና ገንዘብ ለብዙሃኑ ሕዝብ መልእክት የማድረሱን ኣላማና ተግባር የሚፃረር ጥያቄ ነው።መልእክት እንድደርስ የሚፈለገው ለሁሉምነውና።

በዚህ ሹበሀቸው ላይ መልስ ሲሰጥበት ሌላ እርምጃ ተራመዱ።ለእምቢተኝነትና ነቢዩን ለማታከት ተአምራትን እንድያሳዩአቸው ጠየቁዋቸው። በዚህ ጉዳይ በነቢዩና (ﷺ)በነሱ መካከል ክርክርና ውይይት ተካሄደ።ወደፊት የተወሰኑትን ለማምጣት እንሞክራለን ኢንሻ አላሁ ተዓላ።

       ይቀጥላል

https://t.me/Menhaj_Asselefiya


እውነት / ሀሰት 
((1)) ሸሪአዊ እውቀት መፈለግ መማር ግዲታ ነው ??

ጥያቄ ትክክለኛው መልስ ሰታገኙ የሚያመጣላችሁን add አድርጉለት 👇


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته የዚህ ቻናል ቤተሰቦች እንደት ከርማችሁነው ይቅርታ ተቋርጦ የነበረው ፅሁፌ በአላህ ፈቃድ ከዛሬ ጀምሮ ይቀጥላል እናንተም ሳትሰለቹ አንብቡ


ምዕራፍ 3 የደዕዋ ግልፅ መውጣት

ክፍል 12 ደዕዋን ለመዋጋት ቁረይሾች የተጠቀሙት የተለያዩ ዘደዎች

وَقَالُوٱ مَالِ هَاذَا ٱلرَّسُولَ يأْكُلُ ٱلطَّعَامَ وَيَمْشِی فِی ٱلأَسْوَاقِۙ۝٧

"ለዚህም መልዕክተኛው ምግብን የሚበላ በገበያዎችም የሚሄድ ሲሆን ምን (መልዕክተኛነት)አለው ?--አሉ" (አልፉርቃን25:7)

አላህ እንድህ አለ፦

بَلْ عَجِبُوٓٱ أَن جَآءَهُمْ مُنذِرࣱ مِنْهُمْ فَقَالَ ٱلْكَٰفِرُونَ هَذَا شَیْءٌ عَجِيبٌ۝٢

"ይልቁንም ከነሱ ጎሳ የሆነ አስፈራሪ ስለመጣላቸው ተደነቁ  ከሐድዎችም ፦ይህ አስደናቂ ነገር ነው አሉ።(ቃፍ50:2)

إِذْ قَالُوٱ مَآ أَنزَلَ اللهُ بَشَرࣲ مِّن شَیْءࣲ۝٩١

አላህ በሰው ላይ ምንም አላወረደም አሉ።(አለ አንኣም (6:91)
ለዚህም አላህ የሚከተለውን መልስ በመስጠት እምነታቸውን ፉርሽ አደረገባቸው ፦

قُلْ مَنْ أَنزَلَ ٱلْكِتَٰبَ ٱلَّذِی جَآءَ بِهِ مُوسَیٰ نُورࣰا وَهُدࣰی لِّلنَّاسِۖ۝٩١

ያንን ብርሃንና ለሰዎች መሪ ሆኖ ሙሣ ያመጣውን መጽሐፍ ማን አወረደው በላቸው (አል-አንዓም 6:91)

አላህ (ሱ.ወ)የነቢያትንና የመልክተኞችን ታሪኮችና በነሱና በሕዝቦቻቸው መካከል ተደርጎ የነበረው ክርክር ተረከላቸው።ሕዝቦቻቸው እነሱን በመቃወም " እናንተ ብጤያችን ሰው እንጂ (ሌላ)አይደላችሁም "ማለታቸውን በቁርኣኑ ተረከላቸው። መልክተኞቹ ደግሞ የሚከተለውን ማለታቸውን ነገራቸው፦

قَالَتْ لَهُمْ رُسُلُهُومْ إِن نَّحْنُ إِلّا بَشَرࣱ مِثْلُكُمْ وَلَٰكِنَّ ٱللَّه يَمُنُّ عَلَیٰ مَن يشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۖ۝١١

"መልዕክተኞቻቸው ለነርሱ አሉ፦እኛ ቢጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ አይደለንም፣ግን አላህ ከባሮቹ ውስጥ በሚሻው ሰው ላይ ፀጋውን ይለግሳል
" (ሱረቱል ኢብራሒም5:11)

ነቢያትና ሩሱሎች ሁሉም የሰው ልጆች ነበሩ። መልእክተኛ ከመላኢካ ከሆነ ሰው በመላኢካ መመራት ስለማይችል የመልእክትና የመልእክተኛነት አላማ ሊሳካ አይችልም።ጥርጣሬውም (ሹበሃው)እንደነበረ ይቆያል ማለትነው። አላህ እንድህ ይላል፦

وَلَوْ جَعَلْنَٰهُ مَلَكࣰا لَّجَعَلْنَٰهُ رَجولࣰ وَلَلَبَسْنَا عَلَيْهِمْ مَّا يَلْبِسُونَ۝٩

"(መልእክተኛውን)መልአክም ባደረግነው ኖሮ ወንድ (በሰው ምስል)ባደረግነው ነበር። በእነርሱም ላይ የሚያመሳስሉትን ነገር ባመሳሰልንባቸው ነበር።" (አል-አንኣም 6:9)

ሙሽሪኮች ኢብራሂም፣ኢስሚኢልና መሳ(ዐ.ሰ)መልእክተኞች መሆናቸውንና የሰው ልጅ መሆናቸውን ያውቁትና ይቀበሉትም ስለነበር በዚህ ማስመሰያቸውና ማጠራጠሪያቸው ሊገፉበት አልቻሉም።ሌላ ማስመሰያ አመጡ።"አላህ መልእክቱን የሚያደርስለት ከዚህ የቲምና ሚስኪን ሌላ ሰው ማግኘት አልቻለምን?አሉ። አላህ መልእክተኛ ቢልክ ኖሮ የቁረይሽንና የሰቂፍን ምርጦችና ታላላቅ ሰዎች ትቶ ይህንን የሙት ልጅ አይልክም ነበር" አሉ።

وَقَالُوا لَوْ لَانُزِّلَ هَذَا ٱلْقُرْءَانُ عَلَیٰ رَجُلࣲ مِّنَ ٱلْقَرْيَتَيْنِ عَظِمٍ۝٣١

"ይህ ቁርኣን ከሁለቱ ከተሞች በታላቅ ሰው ላይ አይወርድም ኖሯልን?አሉ።" ከመካና ከጧኢፍ ማለታቸው ነው።(አል-ዙኽሩፍ 43:31)
 
አላህ የሚከተለውን መልስ ሰጣቸው

أَهُمْ يَقْسِمُونَ رَحْمَتَ رَبِّكَۚ
እነርሱ የጌታህን ችሮታ ያከፋፍላሉን ? (አል-ዙኽሩፍ 4:32)

ይቀጥላላል
https://t.me/Menhaj_Asselefiya


✅ይህ ቻናል ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ባጠቃላይ
እጅግ ጠቃሚ ቻናል ነው
ወደ ቻናሉ ተቀላቀሉ ዛሬ ባይጠቅማችሁ
ነገ ይጠቅማችኋል⭐
👇
t.me/+SYGKSEYXv-kyNTQ0
t.me/+SYGKSEYXv-kyNTQ0




🔠🔠🔠🔠

  

    

      
   ረ 

ገባ ገባ በሉ


🖋ርዕስ    ✅ኹሹዕ ፊ ሰላህ ⚫️

🎙አቅራቢ ፦✅ ከማል አህመድ ✅

የሚተላለፍበት ሊንክ

⬇️
t.me/tdarna_islam?livestream
t.me/tdarna_islam?livestream


🛜ዛሬ እና ነገ የሚደረጉ የዳዕዋ ፕሮግራሞች

ዛሬ ምሽት በትዳር እና ኢስላም ቻናል

t.me/tdarna_islam/4730
t.me/tdarna_islam/4730

ዛሬ ምሽት በኢብኑ ተይሚያህ ቻናል
⚫️
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/13943
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/13943
⭐️
ነገ እለተ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ
በደሴ ከተማ
🌟
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy/19805
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy/19805

🛜ከላይ ባለው ልንክ እየገባችሁ ሙሉ ተጋባዥ እንግዶች እና ርዕስ አንብቡ✅


Abu_Oubeida~channel dan repost
✏️ መልካም ዜና

ከ"አል_ሁዳ"የሩቃ አገልግሎት መስጫ፦

የአላህ ፈቃድ ሁኖ ሸሪአውን በጠበቀ አሰራር፡የሩቃ አግልግሎት ጀምረናል።ከየትኛውም ቦታ ለሚመጡ አገልግሎት ፈላጊዎች፡ቤታችን ክፍት ነው።ከምንሰጣቻው አገልግሎቶች ውስጥ፦

☑ የሲሕር     
☑ የቡዳ
☑ የጅን
☑ የዛር=>እና ሌሎችም
ከህጻናት እስከ አዋቂ በህመሙ ለተጠቁ ሁሉ አገልግሎቱን እንሰጣለን።

📍አድራሻ ኬሚሴ ከዶ/ር ሰኢድ ክልኒክ ፊት ለፊት ባለው ኮብሊስቶን #300ሟ አካባቢ ገባ ብሎ።

#⃣0930827492
1⃣ላይ በቦት መረጃ ለመጠየቅ ከፈለጋችሁ፡@AbuOubeida90_bot

የቴሌግራም ቻነል፦
t.me/AbuOubeida


የስራ ማስታወቂያ የምንለቅበት
አዲሱ  ⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️ ነው  ✅
በሀገር ውስጥም ይሁን ካሀገር ውጪ ያላችሁ
የሱና ወንድም እና እህቶቻችን 
ይህ ቻናል ይጠቅማችኋል ተቀላቀሉ
👇
join request የሚለውን በመጫን✅️
t.me/+SYGKSEYXv-kyNTQ0
t.me/+SYGKSEYXv-kyNTQ0



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.