#ልዩመረጃ በትናንትናው እለት 'ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ጠፈር ሊጓዙ ነው' በሚል ርዕስ ለከፋይ አባሎቻችን (paid subscribers) ያስነበብነውን መረጃ በርካቶቻችሁ ሙሉውን ማንበብ እንደምትፈልጉ ባቀረባችሁት ጥያቄ መሰረት አቅርበነዋል።
(መሠረት ሚድያ)- በአለም ታሪክ ወደ ጠፈር (space) የተጓዙ ሰዎች ቁጥር 721 እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ፣ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ የጠፈር ተመራማሪዎች ሲሆኑ ከቅርብ አመታት ግን ጥቂት ሰዎች ከፍተኛ ገንዘብ በመክፈል የዝቅተኛው ንፍቀ ክበብ የጠፈር ጉብኝት አድርገዋል።
መሠረት ሚድያ ከሀገር ውስጥ እንዲሁም በዋናነት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከሚገኙ ምንጮቹ ለበርካታ ቀናት ሲያሰባስበው የነበረው መረጃ እንደሚጠቁመው በአለም ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ የአንድ የሀገር መሪ ወደ ጠፈር ሊጓዝ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፣ መንገደኛውም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ናቸው።
በኤምሬቶች የሚገኙ ምንጮቻችን እንዳረጋገጡልን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጠፈር የመጓዛቸው አላማ በርካታ ግቦችን አካቷል፣ ከእነዚህም መሀል የሰላም እና የአንድነት መልዕክት ለአለም ብሎም ለኢትዮጵያውያን ማስተላለፍ እንዲሁም ወጣቶች ወደ ቴክኖሎጂው ዘርፍ እንዲሳቡ እና እንዲነሳሱ ለማድሩግ ታስቧል።
"ውይይቱ በኢትዮጵያ መንግስት እንዲሁም በተባበሩት ኤምሬቶች በኩል በስፋት ንግግር እየተደረገበት ነው" ያሉት አንዱ በዱባይ የሚገኝ የመረጃ ምንጭ በተለይ ከጠፈር ላይ ሆኖ ለአለም ህዝብ መልዕክት ማስተላለፍ የእቅዱ ዋና ግብ ነው ብለዋል።
'Project X' የሚል ስም ተሰጥቶት እየተሰራበት እንደሆነ የሚነገርለት ይህ የጠፈር ጉዞ ወጪው በተባበሩት ኤምሬቶች የሚሸፈን መሆኑን አንድ ሌላ እዛው ዱባይ የሚገኝ ምንጭ ለሚድያችን ተናግሯል።
ለመዳሰስ የሞከርናቸው ፅሁፎች እንደሚጠቁሙት ወደ ጠፈር የሚደረግ ጉዞ ለአንድ ሰው ከትንሹ 250 ሺህ ዶላር እስከ ከፍተኛው 55 ሚልዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ይጠቁማሉ።
ለምሳሌ 'Blue Origin' እና 'Virgin Galactic' የተባሉት መንኩራኩሮች ከንፍቀ ክበብ በታች ለሚደረግ እና ርካሽ የተባለ ጉዞ ከ200 ሺህ ዶላር እስከ 400 ሺህ ዶላር ያስከፍላሉ፣ ራቅ ያሉ እና ከንፍቀ ክበብ ውጪ የሚደረጉ የጠፈር በረራዎችን የሚያከናውኑት እንደ 'Space X' ያሉ ሮኬቶች ደግሞ በአንድ ሰው እስከ 55 ሚልዮን ዶላር (7.3 ቢልዮን ብር) እንደሚያስከፍሉ ታውቋል።
ጠ/ሚር አብይ ሊጓዙ እቅድ የያዙት ከንፍቀ ክበብ ውጪ ወደ አለም አቀፉ የጠፈር ማዕከል (International Space Station) እንደሆነ ታውቋል፣ ወጪውም ከላይ እንደተጠቀሰው በአንድ ሰው እስከ 55 ሚልዮን ዶላር እንደሚደርስ እና በኤምሬቶች እንደሚሸፈን ታውቋል።
አንድ ሌላ የስፔስ ባለሙያ ግን የጉብኝቱ አይነት 'lunar' የሚባለው እንደሆነ ሲገለፅ እንደሰሙ ጠቅሰው ይህም ጨረቃ ላይ ሳይታረፍ፣ ዙርያውን በመሄድ የሚደረግ ጉዞ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬት የዛሬ ስድስት አመት ገደማ ሀዛ አል-ማንሱሪ የተባለ ዜጋዋን ወደ ጠፈር ልካ ነበር። ከዛ ወዲህም ከአሜሪካው የጠፈር ድርጅት ናሳ ጋር በመተባበር በመጪው የፈረንጆቹ አመት 2026 ላይ ሰው ወደ ጨረቃ ለመላክ እየተዘጋጀች መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ከጉዞው ጋር በተገናኘ ሂደቱን ተከታትለው እንዲያስፈፅሙ ቢያንስ አምስት የሚሆኑ የመንግስት ሀላፊዎች የቤት ስራ እንደተሰጣቸው የሀገር ቤት ምንጮች አረጋግጠዋል። ይህ የቤት ስራ እስከ ሀምሌ 2017 ዓ/ም ድረስ ንግግሮችን በመጨረስ ከመስከረም በሗላ ጉዞው እንዲከናወን ማድረግ ነው ተብሏል።
ነገር ግን ጠ/ሚሩ ወደ ጠፈር ከመጓዛቸው በፊት ለበርካታ ወራት ልምምድ እና የጤና ሁኔታ ክትትል ማድረግ እንደሚጠብቃቸው አስረድተዋል።
አንድ ስማቸውን የማንጠቅሳቸው የመንግስት ሀላፊን በጉዳዩ ዙርያ መረጃ ጠይቀን "በመጪው አመታት ከተያዙ እቅዶች ውስጥ አንዱ ነው። ለኢትዮጵያ እና ለአለም ሕዝብ የእርቅ እና ሰላም ጥሪ ይደረጋል" ብለው አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።
መረጃን ከመሠረት!
***የምናወጣቸውን መረጃዎች በእለቱ ለማግኘት ከፋይ አባል (paid subscriber) ይሁኑ ⤵️
https://substack.com/@meseretmedia