#ከዜናዎቻችን| የኮሪደር ፕሮጀክት ለአምስት አመት እንደሚቆይ ተረጋገጠ
(መሠረት ሚድያ)- አነጋጋሪው እና ለበርካቶች ከቤት እና ከስራ መፈናቀል ምክንያት እየሆነ የሚነገርለት ፕሮጀክቱ በአዲስ አበባ በርካታ ስፍራዎች፣ አሁን በቅርቡ ደግሞ በክልል ከተሞች እና በገጠራማ ስፍራዎች ጭምር እየተተገበረ ስላለው ወይም ሊተገበር እቅድ እየተያዘለት እንደሆነ ይታወቃል።
መሠረት ሚድያ የደረሰው አዲስ መረጃ እንደሚጠቁመው የኮሪደር ፕሮጀክት ለአምስት አመት የሚቆይ እና በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያሉ አብዛኞቹን የጭቃ ቤቶች በማንሳት በአዳዲስ የፕሮጀክቶች ሳይቶች ለመተካት ያለመ መሆኑ ታውቋል።
የኮሪደር ልማት ሥራው ህዝብ በጉጉት ሲጠብቀው የነበረ እና ካረጁ እና ከተጎሳቆሉ ቤቶች ህብረተሰቡን አውጥቶ የተሻለ አኗኗርን የሚያስገኝ እንደሆነ በመንግስት ተደጋግሞ ይነገራል።
የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች መካሄድ ከጀመረ በኋላ መንገዶች አምረዋል፣ ህንፃዎች አሸብርቀዋል፣ አዳዲስ የመዝናኛ እና ማረፍያ ስፍራዎች ተገንብተዋል።
ወትሮውን ጽዳት የሚጎድላት ከተማ ተደርጋ ስትወሰድ የነበረችው የአፍሪካ መዲናዋ አዲስ አበባ እንደስሟ አዲስ የሚያስመስሏት ስራዎች ተሰርተዋል፣ ይህን ደግሞ ፕሮጀክቶቹን በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ የሚተቹ እና የሚነቅፉ ሁሉ የሚመሰክሩት ሀቅ ነው።
ይሁንና ከዚህ ባለ ብዙ ቢልዮን ብር ፕሮጀክት ጋር ተያይዞ እየተካሄዱ ያሉ በርካታ የመኖርያ ቤቶች፣ የህንፃዎች፣ የመንገዶች እና የመሰረተ ልማት አውታሮች ጭምር የጅምላ ፈረሳ የሀገራችንን ህዝብ በቅርብ አመታት ታይቶ በማይታወቅ ግርታ ውስጥ ከቶታል።
ነገ ተራው ደርሶኝ ፈራሹ ቤት የኔ ይሆን ወይ? ነገ የተከራየሁት ቤት ፈርሶ መንገድ ዳር እወድቅ ይሆን ወይ፣ የስራ ወይም የንግድ ቦታዬ ፈርሶ ቤተሰቤን ማስተዳደር ያቅተኝ ይሆን ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች የህዝብ የእለት ተእለት ጭንቀት፣ ሮሮ እና ሀሳብ ከሆኑ ሰነባብተዋል።
ይህ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሳብ አመንጪነት እንደተጀመረ ተደጋግሞ የሚነገርለት የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ከአዲስ አበባ ተሻግሮ እንደ ቢሾፍቱ፣ አዳማ፣ መቀሌ፣ ጅማ፣ ሀረር፣ ድሬዳዋ፣ ሀዋሳ ወዘተ ያሉ ከተሞች መስፋፋትም ጀምሯል።
(#ከዜናዎቻችን በሳምንቱ በቪድዮ ዩትዩብ ላይ ያቀረብናቸውን የተመረጡ መረጃዎች ቆየት ብለን በድጋሜ በፅሁፍ የምናቀርብበት አምድ ነው)
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia