"ክሱን የያዙ ጠበቆች ለሚድያዎች የክሱን ሒደት እንዳያስረዱ ዛቻና ማስፈራርያ እየደረሰባቸው ነው"- የቀድሞው የሀዋሳ ከንቲባ ቤተሰቦች
(መሠረት ሚድያ)- ጥቅምት 2016 ዓ/ም በብልሹ አመራር እና በአፈፃፀም ድክመት ምክንያት በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ቤተሰቦች 'በፖለቲካ ሴራና በጥቂት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጥላቻ' ስቃይ እየደረሰበት ነው በማለት ተናገሩ።
የቤተሰብ አባላቱ ለመሠረት ሚድያ በሰጡት ቃል "ያለፍትሕ ከታሰረ አንድ ዓመት ከአራት ወር ያህል ሆኖታል፣ አሁን ላይ የክልሉ መንግሥት በዳኞች ላይ በሚያደርሱት ፖለቲካዊ ጫና ዙርያ መረጃ ይፋ ማድረግ እንፈልጋለን" ብለዋል።
አክለውም "ምንም እንኳን በቀረበበት ክስ ላይ በተገቢዉ መልኩ የተከላከለ ቢሆንም የክልሉ መንግስት የፍትህ ስርአቱን ለማዛባት ከሚያደርጉት የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት በተጓዳኝ ክሱን የያዙ ጠበቆች ለሚድያዎች የክሱን ሒደት እንዳያስረዱ ዛቻና ማስፈራርያ በማድረስ ላይ ነው" ያሉት እነዚህ የቀድሞው የሀዋሳ ከንቲባ ቤተሰቦች የመከላከያ ምስክር ተደርገዉ የተቆጠሩ የመንግስት ስራ ሀላፊዎቾ ፍርድ ቤት ቀርበዉ ቃል እንዳይሰጡ ዛቻና ማስፈራራት፣ በሰበብ አስባብ ቀጠሮዎችን ማራዘምና በቂ የህክምና ክትትል እንዳያገኝ ከማድረግ አንስቶ ቤተሰቡን እና ልጆቹን ለችግር እንዲዳረጉ አስርገዋል ብለው ከሰዋል።
"ኢትዮጲያ ህዝብና መላዉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ድምጽ እንድትሆኑት ስንል በማክበር እንጠይቃለን" ብለዋል።
ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ በከንቲባነት ዘመናቸው ህዝብን የሚጎዳ ጥፋት እንዳልሰሩ እና እሳቸውን ማሳደዱ 'የስልጣን ፍላጎትና የእዉቅና ሽሚያ' በማለት ከዚህ በፊት በሚድያዎች በኩል ተናግረው ነበር።
የቀድሞ ባለስልጣኑ በህግ ሲፈለጉ ከቆዩ በኋላ ከውጭ ሀገር ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።
በዚህ ዙርያ ከሲዳማ ክልል አመረሮች ምላሽ ለማግኘት ያረግነው ሙከራ አልተሳካም።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia