• መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም. በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ደጋ ዳሞት ወረዳ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂዎች (በተለምዶ “ፋኖ”) መካከል ከተደረገ የተኩስ ልውውጥ በኋላ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች የደጋ ዳሞት ወረዳን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች (በተለምዶ “ፋኖ”) ወደ ወረዳው መቀመጫ ፈረስ ቤት ከተማ በመግባት በርካታ የወረዳ አመራሮችን፣ ሥራ ኃላፊዎችን እና “የመንግሥት የመረጃ ምንጭ ናቸው” ያሏቸውን ቢያንስ 80 ሰዎች አስረዋል። እንዲሁም የወረዳ አስተዳዳሪውን ጨምሮ 3 መኖሪያ ቤቶችን በእሳት እንዳቃጠሉ የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል። ከመስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በቁጥጥር ሥር ውለው ከነበሩት ሰዎች መካከል 38 ሰዎች ኅዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም. በግምት ከጠዋቱ 1፡00 እስከ 2፡00 ሰዓት አካባቢ ልዩ ቦታው ፈረስ ቤት ሚካኤል 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በታጣቂዎች (በተለምዶ “ፋኖ”) እንደተገደሉ ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች አስረድተዋል። ሁሉም ሟቾች ሲቪል ሰዎች (የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች እና ነዋሪዎች) ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል 22ቱ ሰዎች ኢሰመኮ በስም የለያቸው ናቸው።
• ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. በሰሜን ጎጃም ዞን፣ በደቡብ ሜጫ ወረዳ፣ ገርጨጭ (መሃል ገነት) ከተማ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች (በተለምዶ “ፋኖ”) መካከል የነበረውን ግጭት ተከትሎ የመንግሥት የጸጥታ አባላት አቶ ገብሬ ሙሉዬ እና አቶ መሀሪው መኩሪያ የተባሉ 2 ሰዎችን “ከፋኖ ጋር በመሆን ስትዋጉን ቆይታችሁ ነው ወደ ቤታችሁ የገባችሁት” በማለት ከቤታቸው አውጥተው እንደገደሏቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
• ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡20 አካባቢ በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ በደጋ ዳሞት ወረዳ፣ ፈረስ ቤት ከተማ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት አማን እንየው የተባለ 1 የ4 ዓመት ሕፃን ልጅ ሲገደል፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፈረስ ቤት ቅርንጫፍ የሚገኝበት ሕንጻ ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል። የድሮን ጥቃት በተፈጸመበት ወቅት ፈረስ ቤት በታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር እንደነበረ እንዲሁም በጥቃቱ በሌሎች ሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል።
• ኅዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም. በግምት ከምሽቱ 3፡20 ሰዓት በሰሜን ሸዋ ዞን፣ መንዝ ማማ ባሽ ንኡስ ወረዳ፣ “ጦስኝ አፋፍ” በተባለ አካባቢ በሚገኝ አንድ የመንገድ ተቋራጭ ድርጅት ሲጠቀምበት የነበረ ካምፕ ላይ በተፈጸመ የአየር (ድሮን) ጥቃት 2 ሕፃናትና 1 ሴት የተገደሉ ሲሆን በ5 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎችና የዐይን እማኞች ገልጸዋል። ተጎጂዎቹ ከ5 ዓመታት በፊት በመሬት መንሸራተት ምክንያት ባሽ ቀበሌ “ወራና ጨታ” ከተባለ ጎጥ ተፈናቅለው በዚሁ ካምፕ ተጠልለው ይኖሩ የነበሩ ናቸው። የድሮን ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት አካባቢው በታጣቂዎች (በተለምዶ “ፋኖ”) ሥር የሚገኝ እንደነበርና ጥቃቱ ከመድረሱ በፊት ታጣቂዎቹ የመጠጥ ውሃ ለመቅዳት፣ ለመታጠብ እና ምግብ ለማብሰል ወደ ካምፑ ይመጡ እንደነበር ጨምረው አስረድተዋል።
• ኅዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም. በሰሜን ወሎ ዞን በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከወልድያ ከተማ ወደ ቃሊም ከተማ በተከታታይ የተተኮሰ ወታደራዊ ዒላማን ያልለየ የጦር መሣሪያ በሰው ሕይወትና አካል እንዲሁም በመኖሪያ ቤቶች እና የቤት እንስሳት ላይ ጉዳት እንዳደረሰ ኢሰመኮ ያሰባሰባቸው መረጃዎች ያስረዳሉ። በወቅቱ ቃሊም ከተማ በታጣቂዎች (በተለምዶ “ፋኖ”) ቁጥጥር ሥር ብትሆንም የጦር መሣሪያ በሚተኮስበት ወቅት በአካባቢው ምንም ዐይነት የተኩስ ልውውጥ እንዳልነበረ ነዋሪዎች አስረድተዋል።
• ኅዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም. አቶ ተግባሩ ሽፌ አበበ የተባሉ የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪ የእህታቸውን ባል ተዝካር (የ“ፋኖ” አባል የነበረ) ታድመው ከደባይ ጥላትግን ወረዳ ሲመለሱ፣ በቁይ ከተማ አሰንዳቦ ፍተሻ ኬላ ላይ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል። ግድያው የተፈጸመባቸው ሲፈተሹ የሟችን ፎቶግራፍ ይዘው በመገኘታቸው “ለምን ፎቶውን ይዘህ ተገኘህ?” በሚል እንደሆነና እስከ ኅዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም. እኩለ ቀን ድረስ አስከሬናቸው እንዳይነሳ ከልክለው እንዳቆዩት የተጎጂ ቤተሰቦች አስረድተዋል።
• ኅዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም. በማእከላዊ ጎንደር ዞን፣ ጎንደር ዙሪያ ወረዳ፣ ለምባ አርባይቱ ቀበሌ፣ አርባ ተንሳይ ጎጥ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች (በተለምዶ “ፋኖ”) በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ላይ የደፈጣ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ቤት ለቤት በመግባት በአርሶ አደሩ እጅ የሚገኝ ሕጋዊ የጦር መሣሪያ ከሰበሰቡ በኋላ አቶ ነጋ ያለው (75 ዓመት)፣ አቶ አጉማሴ አዱኛ (45 ዓመት) እና አቶ ታእት ታከለ (34 ዓመት) የተባሉ 3 ሰዎችን ሕዝብ በተሰበሰበበት እንደገደሏቸው የተጎጂ ቤተሰቦች እና የዐይን እማኞች አስረድተዋል።
• ኅዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ሌሊት በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ብልባላ ከተማ በተፈጸመ የድሮን/የአየር ጥቃት እማሆይ ደስታ ካክራው የተባሉ የ83 ዓመት አረጋዊት በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ተገድለዋል። በዚሁ ግቢ ውስጥ ተከራይተው ይኖሩ የነበሩ 2 የብልባላ ጤና ጣቢያ ባለሙያዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ሕክምና እየተከታተሉ ይገኛሉ። ጥቃት ከመድረሱ በፊት እና ከደረሰ በኋላ በአካባቢው የድሮን ድምጽ ይሰማ እንደነበር ለማወቅ ችሏል።
• ኅዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም. በምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ እናርጅ እናውጋ ወረዳ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በአካባቢው በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) መካከል የተከሰተውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ ኅዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም. በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች የተተኮሰ ወታደራዊ ዒላማን ያልለየ የጦር መሣሪያ ቡሽት ኮኛ ቀበሌ፣ ግራርጌ ሰፈር በመጫወት ላይ ከነበሩ ሕፃናት መካከል ባንችግዜ አዲስ በተባለች የ5 ዓመት ሕፃን ላይ ሞት እና እባብሰው ጌቴ በተባለ የ6 ዓመት ሕፃን ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ማድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል። በተመሳሳይ ቀን በዚሁ ቀበሌ በሌላ መንደር በተፈጸመ ወታደራዊ ዒላማን ያልለየ የጦር መሣሪያ ጥቃት ወይዘሮ መደሰት ሞኜ የተባሉ የ42 ዓመት ሴት የሞቱ ሲሆን 1 ወጣት ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶ በሕክምና ክትትል ላይ የሚገኝ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።
• ኅዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በግምት ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን፣ ፋግታ ለኮማ ወረዳ፣ ፋግታ አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች (በተለምዶ “ፋኖ”) ቁጥጥር ሥር የነበሩ 12 የመንግሥት የጸጥታ አባላት እና ለጸጥታ አባላቱ ምግብ አቅራቢ የነበሩ 2 ሴቶች (ወይዘሮ ፈንታነሽ መላኩ እና ወይዘሮ ይመኙሽ አንዱዓለም) በድምሩ 14 ሰዎች ተገድለዋል። በተጨማሪም 9 በታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር ይገኙ የነበሩ የመንግሥት የጸጥታ አባላት፣ 1 ሕፃን (ከላይ በስም የተጠቀሱት የሟች ወይዘሮ ይመኙሽ አንዱዓለም የ2 ዓመት ሴት ልጅ) እና በትምህርት ቤቱ ውስጥ ሻይና ቡና በመሸጥ የምትተዳደር 1 ሴት በአጠቃላይ 11 ሰዎች በጥቃቱ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን የዐይን እማኞች አስረድተዋል።