#የህዝብድምፅ ከህዝብ በጥቆማ መልክ ደርሰውን ትክክኝነታቸው የተረጋገጡ 5 መረጃዎች
1. በቅርቡ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የታሪፍ ማሻሻያ እንዲሁም የቫት (VAT) ክፍያ መጀመሩን ተከትሎ በተለይ ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ አስደንጋጭ ክፍያ እየተጠየቁ እንደሆነ አንዳንድ ዜጎች እየተናገሩ ይገኛሉ። ደምበኞች እንደሚሉት ለምሳሌ በቅድመ ክፍያ ካርድ የሚጠቀም አንድ ሰው 1,000 ብር ቢሞላ ቆጣሪዉ ላይ የሚታየዉ የተሞላዉ የብር መጠን 353.3 ብር ነው። የድርጅቱን ሰራተኞች ለማጋነር ጥረት ሲደረግ የቫት ክፍያ ነዉ እንደሚሉ፣ ቫቱ እንዴት እና በምን ስኬል እንደሚሰላ ግን ማስረዳት እንደማይችሉ ታውቋል። በሀገራችን የቫት አዋጅ መሰረት የቫት ስኬሉ የአገልግሎቱ 15% መሆኑ ይታወቃል፡፡
2. በአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ውሳኔ ምክንያት የኤችአይቪ ክትትል የሚያደርጉ ከ 500,000 በላይ ኢትዮጵያውያን አደጋ እንደተጋረጠባቸው ታውቋል። ውሳኔው ኤችአይቪን እንደማይመለከት ተገልፆ የነበረ ቢሆንም የጤና ሰራተኞች ግን መድሀኒት እና ቁሳቁስ ለማዘዋወር እንደተቸገሩ ተሰምቷል። ገና ከአሁኑ ለበሽታው የሚወሰደውን መድሀኒት በህገወጥ መልኩ ለመሸጥ ሙከራዎች እየታዩ እንደሆነ ታውቋል። የኢትዮጵያ የጤና እና የሰብአዊ እርዳታ ሴክተሮች ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ እርዳታ ባስተላለፉት ውሳኔ ክፉኛ መጎዳቱ እየታየ ነው።
3. የኢትዮጵያ ማሪታይም ትሬኒንግ ኢንስትትዩት ተማሪዎች ትምህርቱን ተከታትለው ከጨረሱ በኋላ 36,000 ዶላር እየጠየቀ እንደሆነ ታውቋል። መርከበኞችን አሰልጥኖ ማስቀጠር ከጀመረ ከአስር አመት በላይ የሆነው ተቋሙ በ Marine Engineering and Electrotechnical Officer አስተምሮ ወደ ስራ የሚያሰማራቸው ዜጎችን የሚጠየቀው የገንዘብ መጠን በጣም የተጋነነ እና ከሌሎች ሃገራት አንፃር ሲታይ በብዙ እጥፍ እንደሚበልጥ ታውቋል። ለምሳሌ በተመሳሳይ ትምህርት የተማሩ ሰዎች በህንድ 5,000 ዶላር እንዲሁም በፊሊፒንስ 10,000 ዶላር ብቻ ይጠየቃሉ።
4. በሸገር ከተማ አስተዳደር ለመንግስት ቢሮ ማሰርያ ብር አምጡ እየተባሉ እንደሆነ ዜጎች ለመሠረት ሚድያ ጠቁመዋል። "በተጨማሪም ቤት ለቤት እየዞሩ የቴሌቪዥን ግብር ክፈሉ ይላሉ፣ የቴሌቪዥን ግብርን በተመለከተ EBC ከመብራት አገልግሎት ጋር ደረስኩት ባለው ስምምነት ላለፋት 3 ዓመታት መብራት ስንሞላ የቴሌቪዥን እየተቆረጠብን ነው የኖርነው፣ አሁን ሸገር ከተማ ከነቅጣቱ ክፈሉኝ እያለ ነው" ብለው ነዋሪዎቹ ያስረዳሉ። አክለውም የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ከውሀና ፍሳሽ ጋር በመሆን ከነዋሪዎች የቆሻሻ ቢሰበስብም የወረዳ አስተዳደሩ የራሱን ማህበር አደራጅቶ በየወሩ ከነዋሪው በድጋሜ እንደሚያስከፍል ታውቋል።
5. በመጨረሻም፣ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ቤታቸው ፈርሶባቸው ወደሌላ ቦታ የተዛወሩ ሰዎችን በፈረሰው ቤት ስም የቤት ግብር እንዲከፍሉ የቴክስት መልዕክት እየላከላቸው እንደሆነ ታውቋል። "ቤቴ ካዛንችስ ነበር፣ ቤቴም ሰፈሩም ከፈረሰ 3 ወራት አለፉ። ለፈረሰው ቤቴ ነው ግብር ክፈል የተባልኩት" ያሉት አንድ ግለሰብ "መሬት እና የቤት መስሪያ ወደፊት እንሰጣችኋለን ስላሉን የምንጠብቀው እሱን ነበር። በአሁን ሰአት ከነቤተሰቤ ቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚንየም ተከራይተን እየኖርን ነው። ዛሬ ታድያ ላፈረሱት ቤቴ ግብር ክፈል ይሉኛል!" በማለት ለሚድያችን ተናግረዋል።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia