ኤርትራ በአዲስ አበባ ያለውን ኤምባሲዋን እየዘጋች መሆኑ ታወቀ
(መሠረት ሚድያ)- ካለፉት ሁለት አመታት ወዲህ ግንኙነታቸው እየሻከረ የመጣው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግስታት የቃላት ጦርነት መጀመራቸውን ተከትሎ ኤርትራ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ኤምባሲዋን እየዘጋች መሆኑ ታውቋል።
የዛሬ ሰባት አመት ገደማ ግንኙነታቸውን ያደሱት ሁለቱ ሀገራት በትግራይ የተካሄደው ደም አፋሳሽ ጦርነት ላይ በጋራ ቆመው ቢዋጉም የፕሪቶሪያው ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ ግንኙነቱ መሻከር መጀመሩ ይታወሳል።
"ኤምባሲው ከዚህ በኋላ የአፍሪካ ህብረት ተወካዩን ይዞ ይቀጥላል፣ በኢትዮጵያ ያለውን የኤምባሲ ስታፍ ግን እያሰናበተ ነው" ያሉን አንድ የኤምባሲው ምንጫችን ሂደቱ በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
ከቀናት በፊት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የኤርትራ መንግስት የአፍሪካ ቀንድን የማተራመስ አላማ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ነው፣ በአስቸኳይ እንዲቆም መደረግ አለበት በማለት አልጀዚራ ላይ በቀረበ ፅሁፋቸው አስነብበው ነበር።
የኤርትራው የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ለዚህ ምላሽ የሰጡ ሲሆን የፕሬዝደንቱን አስተያየት አጣጥለው የኢትዮጵያን መንግስት የቀጠናውን ሀገራት በመተንኮስ ከሰዋል።
የኤርትራ ኤምባሲ መዘጋት መጀመርን ተከትሎ በአስመራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እጣ ፈንታ እስካሁን አልታወቀም። ላለፉት ጥቂት አመታት ኤምባሲው ክፍት ቢሆንም አምባሳደር ሳይመደብበት መቆየቱም ይታወሳል።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia