#የህዝብአስተያየት የንግዱ ማህበረሰብ ገደብ በሌለው ግብር መከራውን እየበላ ነው
ከሸዋንግዛው ኬ. ለመሠረት ሚድያ የተላከ
የምተዳደረው በንግድ ስራ ነው፡፡ በእኔ እና በማውቃቸው ሌሎች ነጋዴዎች የሚደረስው ጫና ቤተሰባችንን የሚበትን አደጋ ሆኖብናል፡፡
የግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት የሚልካቸው ሰራተኞች ደሞዝ ከፍለው የሚያሰሩን ሰራተኞቻቸው ነው የምንመስላቸው፡፡ ማመናጨቃቸውን ችላ ብንለውም የሚያደርሱብን የግብር ጫና ግን ያለንን ጥሪት ሽጠን የምንወጣው አይደለም፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጀመሩት አሰራር መዘዙ እጅግ አስፈርቶናል፡፡ በሁለት አቅጣጫ ነው ዱላቸውን የሰነዘሩብን፡፡
በአንድ በኩል ቫት እንድንመዘገብ ያስገደዱናል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የቀን ገቢ ግምት ቆልለዋል፡፡ ለአንድ ቡቲክ 10 ሺህ መድበውበት ከሆነ፣ 1,500 ብር በየወሩ ቫት ይከፍላል፡፡ችግር አጋጥሞት 2 ወር ባይሰራ፣ የተመደበበትን 1,500 በየወሩ ይከፍላል፡፡ የ600 ሺህ ብር ሽያጭ ግብር ተቆልሎ ይጠብቀዋል፡፡
እንዲህ እያለ በአመቱ መጨረሻ የግብር ሒሳቡ፡- 1,500*12=18,000.00
ከ3 ሚሊየኑ 600 ሺህ የሚታሰብ የገቢ ግብር ይጠበቅበታል፡፡
ይሄ ነጋዴ የሱቅ ኪራይ፣ የንግድ እቃዎችን መግዛት እና ሌሎች ወጪዎችን ችሎ ስራውን ማስኬድ ይጠበቅበታል፡፡ከዕለት የሚያገኛትን አተራርፎ ደግሞ ቤተሰቡን ያስተዳድራል፡፡
በአዎንታዊ አስተሳሰብ ተሞልቶ ቫቱን፣ የሱቅ ኪራዩን፣ ቤተሰቡን እያስተዳደረ ይክረም እንጂ መንገድ ላይ ክልትው ማለቱ አይቀሬ ነው፡፡ እንግዲህ ከተረፈ ነው በአመቱ መጨረሻ ለግብር መሰብሰቢያ ሰዓት የሚደርሰው፡፡
ምን ያህሉ እንደሚደርስ መገመት ይከብዳል፡፡ ቋሚ ንብረት ካገኙ፣ በአድራሻ አሳደው ይወርሳሉ፡፡ ምንም የሌለው ግን ቤተሰቡን ይዞ ይሰደዳል፡፡
በታሪክ ስንሰማ የጭሰኛ እና የመሬት ከበርቴው ግንኙነት እንዲህ ነበር። ከበርቴው ጨካኝ አሽከሮችን ወደ ጭሰኞች ቤት ይልካል፡፡ እንደ አሁኖቹ የግብር ከፋይ ሰራተኞች ከአርሶ አደሩ ጉሮሮ ነጥቀው የከበርቴውን ጎተራ ይሞላሉ። የከበርቴው ቤት በየቀኑ ድል ያለ ድግስ ያደርጋል፡፡
ከ100 አመት በፊት እንደነበረው ጊዜ ዛሬም ጎምበስ ቀና ብሎ የሚሰራ ነፃ ሰው የላቡን ተነጥቆ ቤተሰቦቹን የመበተን አደጋ ተጋርጦበታል፡፡
---------------------------
ለመሠረት ሚድያ አስተያየት ወይም ጥቆማ ያላችሁ በእነዚህ የኢሜይል አድራሻዎች መላክ ትችላላችሁ:
info@meseretmedia.org
contact@meseretmedia.org