☑️ጤነኛው እብድና ጥያቄዎቹ❓
♻️ጠራራ ፀሀይ ላይ ከመቃብሮች መሀል ቡህሉል የተባለ የከተማው ዕውቅ እብድ ቁጭ ብሏል። (160 አመተ ሂጅራ)
በግዜው የሙስሊሙን አለም ሲያስተዳድር የነበረው ሀሩነ-ረሺድ ድንገት ከመቃብር መሀል የተቀመጠውን እብድ ይመለከተዋል።
👉ንጉስ ሀሩን የማፌዝ ገፅታ እየተነበበበት፦ «አንተ ቡህሉል! እንተ ቆይ መች ነው ሰው ምትሆነው?» ብሎ ጠራው።
👌ከመቃብሮች መሀል ብድግ አለ። ዙርያውን በአይኑ ቃኘ'ና ከአጠገቡ ከምትገኝ ዛፍ ላይ በርጋታ ወጥቶ፦ «አንተ ሀሩን! አንተ ቀውስ! ቆይ ግን መች ይሁን ሰው ምትሆነው?» ብሎ ጮኸበት።
👉ንጉስ ሀሩን የተቀመጠባትን ፈረስ በዝግታ እየጋለበ መጥቶ ቡህሉል ከወጣባት ዛፍ ስር ቆመ።
እዝያው ፈረሱ ጀርባ ላይ ተንደላቅቆ፦ «እንዴ! እኔ ነኝ እብድ ወይስ በዚ ጠራራ ፀሀይ መቃብሮች ላይ ምትቀመጠው አንተ ነህ እብድ?»
👌«እኔማ ጤነኛ ነኝ» አለ ቡህሉል፤ ሙሉ መተማመን ፊቱ ላይ እየተስተዋለበት።
«እንዴት ሆኖ?» ሀሩን የማሾፍ ስሜት የተቀላቀለበት ጥያቄ ጠየቀ።
👌ቡህሉልም ወደ ንጉሱ ቤተ-መንግስት እያመላከተ፦ «ያኛው ጠፊ እንደሆነ አውቃለሁ። ይኸኛው ደግሞ (መቃብር) ዘውታሪ እንደሆነም አውቃለሁ።
👌ስለዚህ እኔ ይኸኛውን ከዝያኛው አስበልጬ ገንብቸዋለሁ። አንተ ደግሞ እንደሚታወቀው ያኛውን ብቻ ገንብተህ ይኸኛውን አፍርሰኸዋል።
👌ምንም እንኳን ከገነባኸው ህንፃ ተነቅለህ ወዳፈረስከው መቃብርህ ወራጅ እንደሆንክ ብታምንም ግን መሄድን አትሻም» ብሎ በአውላላ የትካዜ ሜዳ ላይ ንጉሱን አደናገረው።
👌ቡህሉል ንግግሩን ቀጥሏል፦ «ታድያ ከኔ እና ካንተ ማናችን ነን እብድ መባል ያለብን!»
👉ካማረው ፈረስ ላይ በክብር ቁጭ ያለው ንጉስ ከጉንጮቹ እንደ ጅረት የሚፈሰው እንባው ፂሙን አረጠበ።
✍ንጉስ የሀፍረት ስሜት ውስጥ ሆኖ፦ «ቡህሉል ሆይ! ወላሂ አንተ ትክክል ነህ። እባክህ ትንሽ ምክር ጨምርልኝ» አለው።
👌«ቁርአን ይበቃኻል፤ ምክሮቹን ጠበቅ አድርገህ ያዝ» አለው ቡህሉል።
👉«እሺ ምትፈልገውን ንገረኝ'ና ልፈፅምልህ» አለው ንጉስ ከግዛቱ ሊያስጠቅመው።
✍«አዎን! 3 ምፈልገው ነገር አለ። ከፈፀምክልኝ አመሰግንሃለሁ» አለው ቡህሉል ከዛፉ ላይ ቁጭ ብሎ ቁልቁል እየተመለከተ።
👉ንጉስም፦«ጠይቀኝ» አለ፤ ሙሉ መተማመን ፊቱ ላይ እየተነበበ።
👌ቡህሉል፦«እድሜዬን ጨምርልኝ»
ንጉስ፦ «ይኸንን እንኳን አልችልም»
✍ቡህሉል፦ «ከመለከል መውት ጠብቀኝ»
ንጉስ፦ «ኧረ አልችልም»
👌ቡህሉል፦ «እሺ ከእሳት ታድገኸኝ ጀነት አስገባኝ»ንጉስ፦ «በምን አቅሜ...!»
👌ቡህሉል፦ «አየህ አንተ ባርያ እንጂ ገዢ አይደለህም፤ እኔም ባንተ የሚፈፀምልኝ ምንም ጉዳይ የለኝም»
👉ምንጭ፦የተወሰደ
ﻛﺘﺎﺏ ﻋُﻘﻼﺀ ﺍﻟﻤﺠﺎﻧﻴﻦ
👇👇👇👇👇👇👇
🔗https://t.me/mesjidalsunnah/17023