በሀረሪ ክልል "ከደረጃ በታች የሆኑ" ስድስት የግል ኮሌጆች መዘጋታቸውን የክልሉ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ገለፀ።
ኮሌጆቹ አገልግሎታቸውን እንዲያሻሽሉ ኤጀንሲው ድጋፍና ክትትል በማድረግ ስልጠናዎችን ሲሰጣቸው ቢቆይም በተደረገ ክትትል የሚሰጡትን አገልግሎት ማሻሻል ሳይችሉ በመቅረታቸው እርምጃው መወሰዱን የኤጀንሲው ኃላፊ ነቢላ ማህዲ ገልፀዋል።
አፍራንቀሎ ኮሌጅ፣ ሪፍት ቫሊ ኮሌጅ፣ አዋሽ ቫሊ ኮሌጅ፣ ወሊፍ ኮሌጅ፣ ሉሲ ኮሌጅ እና ሙርቲ ጉቱ ኮሌጅ እንዲየዘጉ የተደረጉት ኮሌጆች መሆናቸውም ተገልጿል።
ኮሌጆቹ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ስትራቴጂ ከተቀመጠው 1 ለ 25 አሰራር በመውጣት አንድ መምህር ከ 50 እስከ 70 ተማሪዎችን እንዲያስተምር ሲያደርጉ መቆየታቸውንም አክለዋል።
ኮሌጆቹ በአግባቡ ያልተደራጁ፣ ምቹ የትምህርት አካባቢ የሌላቸው፣ በተበታተኑ ማዕከላት ሲያስተምሩ የነበሩ እና የትምህርት ጥራት ችግር የተስተዋለባቸው መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
ኮሌጆቹ የማስተማሪያ ዕውቅናቸውን ሳያድሱ ግዜው ባለፈበት ፈቃድ ሲጠቀሙ የነበሩ ከመሆናቸው ባለፈ በርካታ የመመሪያ ጥሰት መፈፀማቸው ተመልክቷል።
ኮሌጆቹ ሲያተምሯቸው የቆዩ ተማሪዎች በተደጋጋሚ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና እንዲወስዱ ቢደረግም ማሳለፍ ያልቻሉ መሆናቸውን ኃላፊዋ አረጋግጠዋል።
ኤጀንሲው ተማሪዎችን ደረጃቸውን ወዳሟሉ ኮሌጆች ለማዛወር እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ከክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘ መረጃ ያሳያል።
@minster_of_education