TGStat
TGStat
Qidiruv uchun matnni kiriting
Ilg‘or kanal qidiruvi
  • flag Uzbek
    Sayt tili
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Saytga kirish
  • Katalog
    Kanal va guruhlar katalogi Kanallar qidiruvi
    Kanal/guruh qo‘shish
  • Reytinglar
    Kanallar reytingi Guruhlar reytingi Postlar reytingi
    Brendlar va shaxslar reytingi
  • Analitika
  • Postlarda qidiruv
  • Telegram'ni kuzatish
мυѕтєfα иσтєѕ📝

18 Sep, 21:26

Telegram'da ochish Ulashish Shikoyat qilish

ከሰሃቦች ጋር እንተዋወቅ ክፍል 5

▪️መጀመሪያ ከሰለሙት ውስጥ ነው 3ተኛ ነበር የሚሉ ዘገባዎች አሉ።

▪️በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው።

▪️በጣም ለጋሽና ቸር የሆነ ሰሃቢይ ነበር።

▪️እድሜው ከ60 በላይ ከሆነ በኋላ መርዋን ኢብኑል ሀከም የሚባል ሰው በቀስት ገደለው።

➡️ትክክለኛ ስሙ

ጠልሃህ ኢብኑ ዑበይዲላህ ኢብኑ ዑስማን ይባላል። ብዙ ስያሜዎች አሉት ከነዛ ውስጥ

 ๏ በህይወት ያለው ሸሂድ ይባላል። ምክኒያቱ ደግሞ እንደሚከተለው ይሆናል
⇨ኡሁድ ዘመቻ ላይ ሙስሊሞች ሲሸነፉ ከረሱል ﷺ ጋር 11 ሰው እንጂ አልቀሩም ነበር። ከነዚህም መካከል አንዱ ጠልሃህ ነበር። የዛን ረሱል ﷺ እነዚህን 11ዱን ወደ ተራራ ይዟቸው እየወጡ ነበር የተወሰኑ ሙሽሪኮችም ለመግደል እየተከተሏቸው ነበር።

ከዛም ረሱል ﷺ "ማነው እነዚህን የሚመልስልን ከኔም ጋር በጀነት ውስጥ ጓደኛዬ የሚሆን" ብለው ጠየቁ:
ጠልሁ ከሁሉም በፊት እኔ አለ፣ የዚህን ጊዜ ረሱል ﷺ አይ ቆይ አንተ ቦታህን አሉት፣ ከአንሳሮች አንዱ እኔ ያ ረሱለላህ አለ፣ እሺ ብለው ፈቀዱለት።

ያሰው እስኪገደል ድረስ ተፋለማቸው አሁን ወደ ተራራው እየወጡ ሙሽሪኮች መከተላቸውን አላቆሙም" አንድ ሰው ለነዚህ" አሉም፣ ረሱል ﷺ አሁንም ጠልሃህ ከሁሉም በፊት እኔ አለ፣ አይ ቆይ አንተ ቦታህን አሉት ከአንሳሮች አንዱ እኔ ያ ረሱለላህ አለ፣ ተፈቀደለት፣ ከዛ እስኪገደል ድረስ ተፋለማቸው እያሉ እያሉ ከረሱል ﷺ ጋር ጠልሃህ ብቻ ቀረ።

ከዛም እንዲጋደል ፈቀዱለት፣ ለጠልሃህ እየተፋለማቸው ከረሱል ﷺ እየተከላከለ ወደ ተራራውም ይዟቸው እየወጣ ሙሽሪኮችን እስኪመልሳቸው ድረስ ተፋለማቸው‥


▪️አቡበክር አሲዲቅ እንዲህ ይላሉ እኔና ዑበይደህ የዛን ቀን ከረሱል ﷺ ርቀን ነበርና መጥተን ልንወስዳቸው ስንል እኔን ተውኝና ሂዱ ለጠልሃህ አሉን።
ጠልሃህ ጋር ስንሄድ ደሙ እየፈሰሰ ነው ከ70 በላይ የሰይፍ ወይም የጦር ወይ ደግሞ የቀስት ምት ነበረበት። ነዳፉም ተቆርጦ እራሱን ስቶ ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ ነበር ‥

ከዛ አንዲት አንቀፅ ወረደች ረሱልም ሰሃቦቹ ፊት ቀሯት "ከአማኞቹ በእርሱ ላይ ለአላህ ቃል ኪዳን የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አልሉ ከነርሱም ስለቱን የፈጸመ (ለሃይማኖቱ የተገደለ) አለ። ከነርሱም ገና የሚጠባበቅ አለ (የገቡበትን ቃል) መለወጥንም አልለወጡም። "[አህዛብ 23]


▪️ከቀሯትም በኋላም ረሱል ﷺ ጣታቸውን ወደ ጠልሃህ በማመላከት እንዲህም አሉ "ሸሂድ ሆኖ ምድር ላይ የሚሄድን ሰው ማየት የፈለገ ጠልሃህን ይመልከት"


๏ ጠልሀተል ኸይርና ጠልሀተል ጁድም ይባል ነበር። ምክኒያቱ ደግሞ በጣም ሀብታም ነጋዴ ነበር።

▪️አንድ ጊዜ በጣም ብዙ ብር አገኘ 700 ሺህ ዲርሃም ነበር የዛን ቀን ለሊት በጣም አዝኖ ነበር ባለቤቱ ኡሙ ኩልሱም አቡበክር ገባችበትና አባ ሙሀምድ ሆይ ምን ሆነህ ነው? አለችው።

▪️አንድ ሰው በጌታው ምን አስቦ ነው ይህ ብር ቤቱ እያለ የሚተኛው? አላት ከሱ ምን ይጨንቅሃል ስታነጋ አከፋፍለው አለችው።

አላህ ይዘንልሽ የተወፈቅሽና የተወፈቀ ልጅ ነሽ አላት። ከዛ ሲነጋ ለአንሳሮች እና ለሙሃጂሮች አከፋፈለው። ጠልሀተል ኸይር እና ጁድም ተባለ።


⇨የእናቱ ስም

ሰዕበህ ቢንት ሀድረሚይ ኢብኑ ዐብደህ ትባላለች

ክፍል 6 ይቀጥላል....
ቻናሉ➥https://t.me/mustefa_Notes

┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒
  ይቀጥላል  ከ50 ላይክ ቡሀላ
┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚

654 0 1 22
Katalog
Kanal va guruhlar katalogi Kanallar to‘plamlari Kanallar qidiruvi Kanal/guruh qo‘shish
Reytinglar
Telegram-kanallar reytingi Telegram-guruhlar reytingi Postlar reytingi Brendlar va shaxslar reytingi
API
Statistika API'si Postlar qidiruvi API'si API Callback
Kanallarimiz
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
O‘qish
Академия TGStat Telegram tadqiqoti 2019 Telegram tadqiqoti 2021 Telegram tadqiqoti 2023
Kontaktlar
Справочный центр Qo‘llab-quvvatlash Email Vakansiyalar
Har xil narsalar
Foydalanuvchi shartnomasi Maxfiylik siyosati Ommaviy oferta
Botlarimiz
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot