мυѕтєfα иσтєѕ📝


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


وَدَاعِيًا إِلَى اللَّهِ بِإِذْنِهِ وَسِرَاجًا مُّنِيرًا
ወደ አላህም በፈቃዱ ጠሪ፣ አብሪ ብርሃንም (አድርገን ላክንህ)፡፡[33:45]
ዋናው ቻናሌ ነው ጎራ በሉ➾https://t.me/mustefa_Apologetics

Bog‘liq kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


𝑚𝑢𝑠𝑡𝑒𝑓𝑎 A𝑝𝑜𝑙𝑜𝖌𝑒𝑡𝑖𝑐𝑠 🥷 dan repost
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ሰላም ናችሁ ውድ ቤተሰቦቼ

አላህ ዱንያ የሰጣችሁ እና በከባድ ሀጃ ውስጥ ያለን ሰው ማውጣት የምችሉ ውድ የተውሒድ እህት ወድሞቼ ካላችሁ በዚህ ➥@mustefa_1_2 አናግሩኝ


💔 ችግሩ የሚጀምረው
በጥፊ ማለት የነበረብህን ሰው
ሰላም ስትለው ነው ።

        ❣️


ትላንትና ሞተው የቀበርናቸው ሰዎች ሁሉም ትላንት እንደሚምቱ አያውቁም ነበር
እኔና አናንተም ልክ እንደዚሁ አናውቅም‼


ሰዎች ያሰቡልኝን አይነት አወዳደቅ
ያልወደኩት አላህን ስለተደገፍኩ
ነው❤️‍🩹


ችግርህን በሚዲያ አትልቀቅ ላይክ ያረጉብሃል አላለም 😁


ገራሚ እና አክቲብ የሆነ ኢስላሚክ ቻናል መግዛት የምፈልጉ በዚ ➥ @comment1_0 አናግሩኝ


.
ለፈገግታ

አንድ ወንድ ሁለቱን ባለቤቶቹን #ሳራንና_ሰሚራን አገባ፤ በሁለቱም መካከል በነገሮች ሁሉ ፍጹም ዕኩል አድራጊ ነበር።
አላህ ቀድሮት... ሁለቱ ሚስቶቹ በአንድ ቀን ሞቱ።

የባለቤቱ ፍትሐዊነት ታላቅነትም፦ « በአንድ ጊዜ እንዲታጠቡ» ጠየቀ።
በዚያው ሰዓትም ሁለት አጣቢ ሴቶችን አስመጣ።
ለቀብር ሊያወጧቸው በፈለገ ጊዜ ግን፦ መውጫው ያለው አንድ በር ብቻ ነበር!
በአንድ ጊዜ ሊያወጧቸው ስለፈለገ ሌላ በር እንዲሠራ (እንዲገነባ) አዘዘ።

▢ አናፂውም መጥቶ ሥራውን አጠናቀቀ፤ በዚሁም መሠረት በአንድ ጊዜ ተቀበሩ፤ ጉዳዩም ተጠናቀቀ፤ አላህም ይህንን ፍትሕ እንዲያደርግ ስለገጠመው አመሰገነው።

በአንደኛዋ ሌሊትም፦ ባለቤቱን ሰሚራን በሕልሙ ያያታል፤ እሷም እንዲህ አለችው፦
«እኔ በአንተ  ቅር ብሎኛል (አዝኜብሃለሁ)፤ ፈጽሞም ይቅር አልልህም»💔

እሱም፦ «ለምን በእኔ አዘንሽ ሰሚራ?» አላት።

እሷም፦ «አንተ በደለኛ! ሳራን በአዲሱ በር አስወጣሃት፣ እኔን ግን ከቀድሞው (ከአሮጌው) በር! መቼም ይቅር አልልህም» አለችው ይባላል።😭


ቀላል ሆነው ግን በጣም የምያሰለቹ ስራዎች

የእንጀራ ላስቲክ ማጠብ
ሽሮ ፣በርበሬ መቀነስ
ተበልቶ ሲያበቃ እቃ ማነሳሳት
የጫማ ክር ማስገባት
ልብስ ማጠፍ
🤮


ሰዎች:-ይላሉ እስኪ ወደ ወንጀሎችህ ተመልከት 😣
አላህም ይልሀል እስኪ እዝነቴን ተመልከት🫶🏼🥰


መፅሐፉ ብቻ የሚለቀቅበት ቻናል ብቻ ለማግኘት ሊኩ ይጫኑ እና በቀላሉ ያግኙ

https://t.me/+DhKpTohs-VRiY2Vk


የፖስቴ ላይክ ማነስ ከነዳጁ ጋር ይያያዛል እንዴ ? የኔን ላይክ ቆፍራቹ ነው እንዴ የምታወጡት😒😁


ፈገግታ post😁

እስልምና አራት ፈቅዶልህ አንዷም የለለችህ አንተ😁

ምደረ ላጤ 😁😁


ትምህርት በጣም ከመናፈቄ የተነሳ ዩኒፎርሜን ለብሼ መተኛት ጀምሪያለው ይለኛል እንዴ በ28 አመቱ 7ተኛ ክፍል እየተማረ

                 #ይሄ_ሹገር_Student 😂


አዎ ቆንጆ ነች ነገር ግን ከዛ
ፈገግታዋ ጀርባ ያለውን ሀዘን
አላህ ብቻ ነው ሚያውቀው


ፈገግታ።🙂

አንዱ ስለ ጀነት ኒዕማ ስለ ሑረልዐይን ይነገረዋል አሉ

“ውበታቸው የጉድ ነው አንዷ ስትስምህ 70 አመት ፌንት ታረጋለህ” 🫠ይለዋል

“አሁንም ብትስመኝስ?”🥹 ይለዋል

“አሁንም 70 አመት ፌንት” 🫠

“እዛው ብትደግመኝስ” 😍

“እዛው 70 አመት ትወድቃለህ” 🫠

“210 አመት ፌንት😟? ታድያ ምኑን ጀነት ገባሁ😕?”

አለ አሉ 🤲😁


ይህ ሶዬ ግን😭😂


ክፍል 6 ልለቅላቹ ነበረ ግን የተባላቹት ½ እራሱ ሞምላት አቃታችሁ እያነበባችሁ እየተጠቀማችሁ ቢሆን ኖሮ ትሞሉት ነበረ ስለዚ እያነበባችሁ አረለም ማለት ነው።


ከሰሃቦች ጋር እንተዋወቅ ክፍል 5

▪️መጀመሪያ ከሰለሙት ውስጥ ነው 3ተኛ ነበር የሚሉ ዘገባዎች አሉ።

▪️በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው።

▪️በጣም ለጋሽና ቸር የሆነ ሰሃቢይ ነበር።

▪️እድሜው ከ60 በላይ ከሆነ በኋላ መርዋን ኢብኑል ሀከም የሚባል ሰው በቀስት ገደለው።

➡️ትክክለኛ ስሙ

ጠልሃህ ኢብኑ ዑበይዲላህ ኢብኑ ዑስማን ይባላል። ብዙ ስያሜዎች አሉት ከነዛ ውስጥ

 ๏ በህይወት ያለው ሸሂድ ይባላል። ምክኒያቱ ደግሞ እንደሚከተለው ይሆናል
⇨ኡሁድ ዘመቻ ላይ ሙስሊሞች ሲሸነፉ ከረሱል ﷺ ጋር 11 ሰው እንጂ አልቀሩም ነበር። ከነዚህም መካከል አንዱ ጠልሃህ ነበር። የዛን ረሱል ﷺ እነዚህን 11ዱን ወደ ተራራ ይዟቸው እየወጡ ነበር የተወሰኑ ሙሽሪኮችም ለመግደል እየተከተሏቸው ነበር።

ከዛም ረሱል ﷺ "ማነው እነዚህን የሚመልስልን ከኔም ጋር በጀነት ውስጥ ጓደኛዬ የሚሆን" ብለው ጠየቁ:
ጠልሁ ከሁሉም በፊት እኔ አለ፣ የዚህን ጊዜ ረሱል ﷺ አይ ቆይ አንተ ቦታህን አሉት፣ ከአንሳሮች አንዱ እኔ ያ ረሱለላህ አለ፣ እሺ ብለው ፈቀዱለት።

ያሰው እስኪገደል ድረስ ተፋለማቸው አሁን ወደ ተራራው እየወጡ ሙሽሪኮች መከተላቸውን አላቆሙም" አንድ ሰው ለነዚህ" አሉም፣ ረሱል ﷺ አሁንም ጠልሃህ ከሁሉም በፊት እኔ አለ፣ አይ ቆይ አንተ ቦታህን አሉት ከአንሳሮች አንዱ እኔ ያ ረሱለላህ አለ፣ ተፈቀደለት፣ ከዛ እስኪገደል ድረስ ተፋለማቸው እያሉ እያሉ ከረሱል ﷺ ጋር ጠልሃህ ብቻ ቀረ።

ከዛም እንዲጋደል ፈቀዱለት፣ ለጠልሃህ እየተፋለማቸው ከረሱል ﷺ እየተከላከለ ወደ ተራራውም ይዟቸው እየወጣ ሙሽሪኮችን እስኪመልሳቸው ድረስ ተፋለማቸው‥


▪️አቡበክር አሲዲቅ እንዲህ ይላሉ እኔና ዑበይደህ የዛን ቀን ከረሱል ﷺ ርቀን ነበርና መጥተን ልንወስዳቸው ስንል እኔን ተውኝና ሂዱ ለጠልሃህ አሉን።
ጠልሃህ ጋር ስንሄድ ደሙ እየፈሰሰ ነው ከ70 በላይ የሰይፍ ወይም የጦር ወይ ደግሞ የቀስት ምት ነበረበት። ነዳፉም ተቆርጦ እራሱን ስቶ ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ ነበር ‥

ከዛ አንዲት አንቀፅ ወረደች ረሱልም ሰሃቦቹ ፊት ቀሯት "ከአማኞቹ በእርሱ ላይ ለአላህ ቃል ኪዳን የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አልሉ ከነርሱም ስለቱን የፈጸመ (ለሃይማኖቱ የተገደለ) አለ። ከነርሱም ገና የሚጠባበቅ አለ (የገቡበትን ቃል) መለወጥንም አልለወጡም። "[አህዛብ 23]


▪️ከቀሯትም በኋላም ረሱል ﷺ ጣታቸውን ወደ ጠልሃህ በማመላከት እንዲህም አሉ "ሸሂድ ሆኖ ምድር ላይ የሚሄድን ሰው ማየት የፈለገ ጠልሃህን ይመልከት"


๏ ጠልሀተል ኸይርና ጠልሀተል ጁድም ይባል ነበር። ምክኒያቱ ደግሞ በጣም ሀብታም ነጋዴ ነበር።

▪️አንድ ጊዜ በጣም ብዙ ብር አገኘ 700 ሺህ ዲርሃም ነበር የዛን ቀን ለሊት በጣም አዝኖ ነበር ባለቤቱ ኡሙ ኩልሱም አቡበክር ገባችበትና አባ ሙሀምድ ሆይ ምን ሆነህ ነው? አለችው።

▪️አንድ ሰው በጌታው ምን አስቦ ነው ይህ ብር ቤቱ እያለ የሚተኛው? አላት ከሱ ምን ይጨንቅሃል ስታነጋ አከፋፍለው አለችው።

አላህ ይዘንልሽ የተወፈቅሽና የተወፈቀ ልጅ ነሽ አላት። ከዛ ሲነጋ ለአንሳሮች እና ለሙሃጂሮች አከፋፈለው። ጠልሀተል ኸይር እና ጁድም ተባለ።


⇨የእናቱ ስም

ሰዕበህ ቢንት ሀድረሚይ ኢብኑ ዐብደህ ትባላለች

ክፍል 6 ይቀጥላል....
ቻናሉ➥https://t.me/mustefa_Notes

┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒
  ይቀጥላል  ከ50 ላይክ ቡሀላ
┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚


ከሰሃቦች ጋር እንተዋወቅ ክፍል 4

▪️ከልጆች መጀመሪያ በረሱል ﷺ ያመነና የተቀበለው ነው። 10 አመት ነበር እድሜው ሲሰልም።

▪️የረሱል ﷺ አጎት ልጅና አማችም ነው።

▪️ከዑስማን (ረ.ዐ) በኋላ 4ተኛው ኸሊፋ ነው።

▪️በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው።

▪️በኢስላም የመጀመሪያው ፊዳእ (መስዋእት) ነው።

▪️ወህይን ወይም ቁርአንን ከሚፅፉ ሰሃቦች (ከነቢዩ ፃሃፊዎች) አንዱ ነበር።

▪️የረሱል ﷺ አምባሳደርም ነበር።

▪️ልክ ዑስማን (ረ.ዐ) እንደተገደለ ኺላፋውን ተረክቦ 6 አመት ከ3 ወራት ከመራ በኋላ ፈጅር ሰላት እያሰገደ አብዱረህማን ኢብኑ ሙልጂም በሚባል የኸዋሪጆች ራስ የሆነው ከኋላው መጣና በተመረዘ ሰይፍ ራሱ ላይ መታው፤
ልክ ከተመታ በኋላ ወደ ቤቱ ተወሰደ፣ የመታኝን ከምግቤ አብሉት አጠጡትም ከሞትኩም፣
እንደገደለኝ ግደሉት ከተርፍኩ ደግሞ ውሳኔዬ እወስድበታለሁ አለ። ከዛ ብዙ ሀኪሞች መጡ ሊያተርፉት አልቻሉም ከ3 ቀን በኋላ ሞተ



➡️ትክክለኛ ስሙ

ዐሊይ ኢብኑ አቡጣሊብ ኢብኑ አብዱልሙጠሊብ ነው። ብዙ ስያሜዎች አሉት ከነዛ ውስጥ

🔹አቡ ቱራብ ይባላል፣ የተባለበት ምክኒያት ከእለታት አንድ ቀን መሬት ካይ ተኝቶ ረሱል ﷺ መጡበትና እንዲህም አሉት “ከስሞችህ የሚገቡህ አቡ ቱራብ ነው አንተ አቡ ቱራብ ነህ” አሉት።

🔹ሀይደረህም ይባላል፣ ምክኒያቱ ደግሞ ሲወለድ እናትየው ሀይደራህ ብላ መሰየም ፈልጋ ነበር። ነገር ግን አባትየው እንቢ ብሎ ዐሊይ አለው ሀይደረህ ማለት ከአንበሳ ስሞች አንዱ ነው።

🔹አልከራር ተብሎም ይታወቅ ነበር። ስያሜውን ረሱል ﷺ ነበር የሰየሙት እዛው ኸይበር ዘመቻ ላይ ሙስሊሞች በተደጋጋሚ መክፈት ያቃታቸውን ምሽግ ረሱል (ﷺ) ዐሊይ (ረ.ዐ) እንዲከፍተው ባንዲራውን ሰጠው ሲሰጠውም እንዲህ ብሎ ነበር የሰጠው:

“ባንዲራውን አላህንና መልእክተኛውን ለሚወድ፣ አላህና መልእክተኛውም ለሚወዱት ሰው እሰጣለሁ፣ ወደፊት የሚሄድ እንጂ የሚሸሽ አይደለም " ከራር ማለት ወደ ኋላ የማይል የማይሸሽ ማለት ነው ...


▪️የእናቱ ስም ፋጢማህ ቢንቱ አሰድ አልሃሺሚየህ ትባላለች....

ክፍል 5 ይቀጥላል....
ቻናሉ➥https://t.me/mustefa_Notes

┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒
  ይቀጥላል  ከ50 ላይክ ቡሀላ
┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚


ከሰሃቦች ጋር እንተዋወቅ ክፍል 3

▪️መጀመሪያ ከሰለሙት ውስጥ ነው።

▪️ከአቡበክርና ከዑመር (ረ.ዐ) ቀጥሎ 3ተኛው ኸሊፋ ነው።

▪️መላኢኮች የሚያፍሩት ነው።

▪️በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው።

▪️መጀመሪያ ወደ ሀበሻ የተሰደደው እሱ ነበር።

▪️በኺላፋው ዘመን ቁርአንን በሙስሀፍ የሰበሰበው እሱ ነው።

▪️አርማኒያ፣ ኹራሳን፣ ኩርማን፣ አፍሪካንና የተለያዩ ሀገራትን ከፈቶ ኢስላማዊ መንግስትን አስፋፍቷል።

▪️መስጂደል ሀረምንና መስጂደ ነበዊን አስፋፍቷል።

▪️ለመጀመሪያ ጊዜ ኢስላመዊ የባህር ሀይልን አቋቋመዋል።

▪️በሁለተኛው አጋማሽ ኺላፋው ወደ 12 አመት ከቆየ በኋላ ፊትና ብቅ አለች፣ በዛ ምክኒያት በሙናፊቆች ቁርአን እየቀራ ሸሂድ ሆነ፣ ተወግቶ ደሙ በአንዲት አንቀፅ ላይ ፈሰሰ «እነሱንም አላህ ይበቃሃል፣ እርሱም ሰሚው አዋቂው ነው።» [በቀራህ 137]

➡️ትክክለኛ ስሙ

ዑስማን ኢብኑ ዐፋን አል ኡመዊ ይባላል። ዚን ኑረይን ተብሎም ይታወቃል።

👉ዚን ኑረይን የተባለበት ምክኒያት ደግሞ

๏ የረሱል (ﷺ) 2 ሴት ልጆችን ስላገባ ነው። ሩቀያን አግብቶ ከሞተች በኋላ ዳግም ረሱል ኡሙ ኩልሱምን ዳሩት፣ እሷም ስትሞት ረሱል (ﷺ) 3ተኛ ልጅ ቢትኖረኝ ዑስማንን እድረው ነበር ብለው ነበር።

▪️ይህን በማስመልከት ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንዲህ ይላሉ: አጎቴ እንዲህ አሉኝ “ ዑስማን ለምን ዚን ኑረይን እንደተባለ ታውቃለህን?

አላውቅም አልኩኝ:  ከአደም ፍጥረት ጀምሮ እስከ እለተ ቂያም ድረስ ዑስማን እንጂ የአንድ ነቢይ 2 ሴት ልጅ አግብቶ ማንም አያውቅም። ለዛም ነው ዚን ኑረይን የተባለው ” አለኝ።

▪️እናቱ አርዋ ቢንት ኩረይዝ ኢብኑ ረቢዐህ ትባላለች።

ክፍል 4 ይቀጥላል....
ቻናሉ➥https://t.me/mustefa_Notes

┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒
  ይቀጥላል  ከ50 ላይክ ቡሀላ
┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.