ወንድምህ ማለት …
ካለህ ላይ ትሰጠዋለህ እሱም ይሰጥሀል ለችግርህ ጊዜ ከጎንህ ይቆማል፣ አንተ ከሱ ኪስ ትወስዳለህ እሱም ካንተ ኪስ ይወስዳል ፣ ሁሌ መስማማት ላይኖር ይችላል፣ አዎ በአንዳንድ ጉዳዮች ላትስማማ ትችላለህ በአንዳንድ ጉዳዮች ደግሞ ትስማማለህ አንተ ትወቅሰዋለህ እሱም ይወቅስሀል መጨረሻ ላይ ግን እርስ በርሳችሁ ትታረቃላችሁ ልባችሁ ላይ ቂምን አትቋጥሩም የቀኑ መጨረሻም ሌሊት ላይ አብራችሁ በሳቅ በጨዋታ ታሳልፋላችሁ።ይህ ነው ትክክለኛ ወንድማማችነት።አንተ ስትደሰት ይደሰታል፣ አንተ ተከፍተህ ማየት አይወድም አንተ ስትከፋ እሱም ይከፋዋል ፣ አንተ በሌለህበት ስትታማ ካንተ ይከላከልልሀል ፣ ነውርህን ይሸፍንልሃል ፣ ወደ መልካም ነገር እጅህን ስትዘረጋ እሱም ይዘረጋል፣ ክፍተትም ካለብህ ይሸፍንልሃል፣ እንጂ እንደሌላው ዳር ይዞ አንተን አያማም ፣ የሆነ ችግር ወይም አደጋ ቢደርስብህ ቀድሞ የሚደርስልህ ወንድምህ ነው!
የሆነን ነገር ከጠየቅከው ይሰጥሀል ፣ አኩርፈኸው ዝም ብትለው እሱ በሰላምታ ይጀምርሃል ያናግርሃል ፣ መልካም በሆኑ ነገራቶች ከራሱ አንተን ያስቀድማል ፣ ለችግርህ ቀድሞ ይደርሳል ፣ ከአይኑ ስትሰወር ይናፍቅሀል ይፈልግሀል፣ ስትዘነጋም ያነቃሃል።ጌታውን ሲለምን ዱዓዕ ሲያረግ አይረሳህም ፣ በዱዓው ያስታውስሃል።
ወንድም ማለት ራስ ላይ የሚደፋ አክሊል ፣ አንገት ላይ የሚደረግ ጌጥ ነው ፣ እርሱ ማለት ላንተ ውበት ነው። ወንድም በሆነ ችግር ወድቆ ብታገኘው ልታነሳው ይገባል ፣ ችግር ላይ ቢወድቅ እርዳው ደግፈው ፣ ቢደክም ቢልፈሰፈስ አንሳው አበርታው ።
ወንድም ማለት በችግር ጊዜ ደራሽ ነው ፣ አጋዥ ነው ፣ በችግር ጊዜ እንደ ጥላ ያገለግልሀል ፣ ልትወድቅ ስትል እንደ ምርኩዝ ያገለግልሃል።
👉 ስለ ወንድምነት ካደረገው የጁምዓ ኹጥባ የተወሰደ
https://t.me/sultan_54