የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክን 25ኛ አመት ምክንያት በማድረግ የ''እንኳን ደስ አላችሁ'' መርሐ-ግብር አከናወነ።
''25 ዓመታትን በታታሪነትና በአገልጋይነት'' በሚል መሪ ቃል የብር ኢዮቤልዩ በዓሉን ሲያከብር የቆየው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የምሥረታ በዓሉን ማጠቃለያ ዝግጅት መከናወኑ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሉዑክ ቡድን በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ከባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ የተላከውን ''የእንኳን ደስ አላችሁ'' መልዕክት እና ስጦታ አበርክቷል።
በዚህም የባንኩ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አልሰን አሰፋ ንግድ ባንክ ሐገር ላይ ጉልህ አሻራቸውን ማሳረፍ የቻሉና እንደ ንብ ያሉ ታላላቅ ተቋማት የምሥረታ በዓላቸውን ሲያከብሩ ''እንኳን ደስ አላችሁ'' መልካም ምኞት ማስተላለፍ መጀመሩን በመጠቆም ይህም በዘርፉ ያለውን አዎንታዊ ስሜት ለማሳደግ የሚረዳ መሆኑን ገልፀዋል።
ንብ ባንክም በተለያዩ አጋጣሚዎች ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያልተቆጠበ ድጋፍ ካደረጉና ሊመሰገኑ ከሚገባቸው ተቋማት መካከል አንዱ በመሆኑና ባሳለፋቸው 25 ዓመታት ለተቀዳጀው ስኬትም ቦታ ያለን መሆኑን ለማሳየት በማቀድ ነው ሁነቱ እንዲዘጋጅ ያደረግነው ብለዋል።
የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ በበኩላቸው ንግድ ባንክ የጀመረው ተግባር በአርአያነት የሚነሳና በዘርፉ ያልተለመደ እንዲሁም በንብ ባንክም የመጀመሪያው በመሆኑ የመልካምነት ስሜትን የሚያጎለብት ነው፤ ለዚህም እናመሰግናለን ብለዋል።
ሁለቱ ተቋማት ወደፊትም በተለያዩ የሥራ ምዕራፎች ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማድረግም መሰል እንቅስቃሴዎች ሚናቸው ላቅ ያለ መሆኑን ተናግረዋል።