ከትናንት እንማር መሪዎቻችን እንዎቅ መሪዎቻችን እንጠብቅ እስከነፃነት እንዝለቅ ለአማራነት እንሰጥ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አማራ እንደ አማራ ብዙ መሪዎችን አጥቷል ሌላውን ትተነው በወያኔ መራሹ ኢህአዴግ እና በኦህዴድ መራሹ ብልፅግና የአገዛዝ ዘመን ብቻ እንደ ፕ/ሮ አስራት ወልደየስ፣ ሳሙኤል አወቀ፣ አሳምነው ፅጌ የመሳሰሉ መሪዎችን መጠበቅ አቅቶን ተነጥቀናል። አሁን በትናንት ታሪክ ለመወቃቀስ ሳይሆን ዛሬም መልሰን የማናገኛቸውን መሪዎች እንዳናጣ ያሰጋል።
መሪ ብዙ አይነት ቢሆንም ነገር ግን በትጥቅ ትግል ውስጥ ትግሉን አስተባብሮ የሚመራ ፖለቲካዊም ወታደራዊም እውቀት ያለው፣ ማስተባበር እና ማደራጀት የሚችል፣ ተደማጭ የሆነ፣ ለትግሉ ታማኝ የሆነ መሪ ከሌለ የፈለገ ጀግና ተዋጊ ቢኖር የፈለገ ብዙ ወጣት ትግሉን ቢቀላቀል የፈለገ ጥሩ የውጊያ ስልት ቢጠቀም አንድ ነፍጥ አንግቦ የተነሳ ተዋጊ ብቁ የሆነ መሪ ከሌለው አያሸንፍም።
ለዚህ ታሪክ ምስክር ነው ለምሳሌ ያህል የኮሚኒስት ቻይናዎች የትጥቅ ትግል በማኦ(Mao Zedong) የበሰለ አመራር ባይመራ በአሜሪካ የሚደገፈውን መንግስት እና የጃፓን ወራሪዎችን ማሸነፍ ከባድ ነበር፣ የኩባ ኮምኒስት የደፈጣ ተዋጊዎች በፊደል ካስትሮ ባይመሩ የወቅቱን የኩባ አንባ ገነን መንግስት ማሸነፍ ይችላሉ ብሎ እንኳን መናገር ቢቻል ግን በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ለማሸነፍ የፌደል ካስትሮ የአመራር ጥበብ አያጠያይቅም በተመሳሳይ እነ እነሆቺ ሚኒን(Ho Chi Minh)፣ እነ ቺኩቬራ(Che Guevera)፣ እነ Simon Bolivar በመሩት የትጥቅ ትግል ላይ ምን ያህል አበርክቶ እንዳበረከቱ ታሪክ መመስከር ይችላል።
በየትኛውም የትጥቅ ትግል ላይ የመሪ አስተዋፅኦ የታወቀ ነው በማንም ሊተካ አይችልም ሲጀመር መሪ የሌለው የትጥቅ ትግል ብዙ ጊዜ ሲከሽፍ ታይቷል ለዚህም ዛሬ ድረስ ሀገር አልባ ሆነው እየታገሉ ያሉት ኩርዶች በወቅቱ አንድ አድርጎ የሚመራቸው ሰው ባለማግኘታቸው ዛሬም ድረስ በየቦታው እየተቅበዘበዙ ይገኛሉ ሌሎችም ብዙ የትጥቅ ትግሎችም ሆኑ ሌሎች ፖለቲካዊ ትግሎች በታሪክ ሲከሽፉ የምናይበት አንዱ ምክንያት የመሪ እጦት ነው።
በትጥቅ ትግል ውስጥ መሪ ሲባል ተራ የጎበዝ አለቃ ሳይሆን ዘመኑን በደንብ የተረዳ፣ እታች ያለው ሰራዊት የሚያደምጠው እና የሚያከብረው፣ ማደራጀት እና ማስተባበር የሚችል፣ የአመራር ብቃት ያለው፣ ወታደራዊውንም ፖለቲካዊውንም ሁነት የሚያውቅ፣ ቆራጥ እና ፅኑ የሆነ በአጭር አገላለፅ ለትግሉ የተሰጠ ማለት ነው እናም በኛ የትጥቅ ትግል ውስጥም መሪ የግድ ነው መሪ ስል የብርጌድ ወይም የክፍለ ጦር አልያም የዕዝ መሪ ሳይሆን ሁሉንም አማራ አንድ አድርጎ የሚመራ መሪ ያስፈልገናል።
እንደዚህ አይነት መሪ ደግሞ ስለፈለግን ብቻ አይመጣም እንዲየውም በታሪክ እንደምናየው አንድን አብዮት ወይም ትግል በብቃት የሚመሩ መሪዎች የሚፈጠሩት ከስንት አንዴ ነው እንደነዚህ አይነት መሪዎች በክፍለ ዘመን አንዴ የምናገኛቸው አይነት ናቸው እንጂ ሁል ጊዜ አናገኝም የሀገራችንን ታሪክ ብናይ እንኳን ዘመነ መሳፍንት በሀገራችን ለ86 አመት የቆየው እንደ አፄ ቴዎድሮስ ይህንን ስርአት ለማስቆም ቆርጦ የተነሳ መሪ በቶሎ ባለመገኘቱ ነው፣ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ገና በማለዳ ወደ ሀገራችን ያልገባው እንደ አፄ ምኒልክ ያለ አስተዋይ እና አርቆ አሳቢ መሪ በጊዜ ባለመነሳቱ ነው በአጠቃላይ ብዙ እድሎችን ያባከንበት አንዱ ምክንያት መሪ ስላልነበረን እና ከስንት አንዴ ብቅ የሚሉ መሪዎቻችንም መጠበቅ ባለመቻላችን ነው።መልህቅ