ጥቂት ስለ ጀምስ አለን
━━━✦━━━
ምንም እንኳ አዝ ዘ ማን ቲንክዝ (As the man thinketh) የሚለው መጽሐፉ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ያነቃቃና በከፊልም ሰዎች ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ እንዲያሻሽሉ ያደረገ ቢሆንም በጀምስ አለን ሕይወት ዙሪያ የሚታወቀው በጣም ጥቂት ነው።
ጀምስ አለን በእንግሊዝ ሀገር በሌስተር ከተማ እ.ኤ.አ. በ1864 ዓ.ም. ተወለደ። እስከ 1902 ዓ.ም. ድረስም በአንድ የእንግሊዝ ትልቅ ኮርፖሬሽን ውስጥ ልዩ ጸሐፊ በመሆን አገልግሏል።
ጀምስ አለን በ38 ዓመቱ ከጸሐፊነት ሥራው ጡረታ በመውጣት መኖሪያውን ከባለቤቱ ጋር በእንግሊዝ ሀገር ኢልኮምብ ወደሚገኘው ትንሽ ቤት አዛወረ።
ጀምስ አለን በድንገት እስካለፈበት 48 ዓመት ዕድሜው ድረስ ከሃያ በላይ የሚሆኑ ሥራዎችን ጽፏል።
አዝ ዘ ማን ቲንክዝ (As the man thinketh) የተሰኘው የጀምስ አለን ሥራ በኖርማን ቪንሰንት ፒል፣ ኦርል ናይቲንጌል፣ ጄሰን ዊትሌን እና በሌሎች ብዙ የሆኑ የዘመናችን ጸሐፊዎች ላይ አሻራውን አሳርፏል።
ራሱ ጀምስ አለን 'ይህች ትንሽ መድብል' እያለ የሚጠራት አዝ ዘ ማን ቲንክዝ (As the man thinketh) የምትል መድብሉ በአምስት ታላላቅ ቋንቋዎች ተተርጉማ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አንባቢዎች የሰው ህልም በሃሳብ ኃይል ብቻ በቀላሉ እውን ሊሆን እንደሚችል እንዲያውቁ ረድታለች።
━━━━━
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery