♻️✍ሙዓዊያ እና ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁም በተጋጩ ግዜ የሮሙ ንጉስ እንዲህ ሲል ደብዳቤ ፃፈ።
🍂 "ከሮም ንጉሰ ነገስት ለ ሙስሊሞች መሪ ሙዐዊያ አቡ ሱፍያን!!
ባንተ እና በዐሊይ መካከል የተከሰተውን ግጭት ሰምተናል።ስለዚህም ለሙስሊሞች መሪ አንተ መሆን እንዳለብህም ስለምናምን አንተ ፍቃድህ ከሆነ የዐሊይን ጭንቅላት ቀንጥሶ የሚያመጣልህን ወታደር ልላክልህ።"
👉 ይህ ደብዳቤ ሙዐዊያ ጋር እንደደረሰም ሙዓዊያም
➖ "ከሙዓዊያ ለሮም መሪ!!! ሁለት ወንድማማቾች ስለተጣሉ አንተ ምን አገባህ? አፍህን የማትዘጋ ከሆነ ጅማሬው እኔ ጋ የሆነ እና ፍፃሜው አንተ ጋ የሆነ ሰራዊት ልኬ አንገትህን በማስቀንጠስ ለዐሊይ በስጦታ መልኩ አበረክትለታለሁ።"
#ይህ_ትክክለኛ_ሙስሊሞች_ሳለን_ነው
___
🍁 ካሊድ ኢብን ወሊድ ለፐርሺያው ንጉሰ ነገስት እንዲህ ሲል ደብዳቤ ፃፈለት
"ስለም ትድናለህ። እንቢ ያልክ እንደሆን ግን፤ እናንተ ህይወትን የምትወዱትን ያህል ሞትን የሚወዱ ሰራዊቶችን ይዤልህ እመጣለሁ።"
ንጉሱ ይህን ደብዳቤ ካነበበ በኋላ የቻይናውን ንጉስ የጦር እርዳታ ሊለምነው ደብዳቤ ፃፈለት።
➖ የቻይናውም ንጉስ እንዲህ ሲል ደብዳቤ መልሶ ላከለት።
"ንጉስ ሆይ! ተራራን እንኳን ለመናድ ካሰቡ ምንም ከማያግዳቸው ወታደሮች ጋር ለመጋፈጥ አቅሙ ስለሌለኝ ጥያቄህን መፈፀም አልችልም።"
#ምን_ያህል_ሀያላን_እንደነበርን_ተመልከቱ
___
🍃 በደውለቱል ዑስማኒያ የአገዛዝ ዘመን የሙስሊም ወታደሮች የጦር መርከቦቻቸውን ይዘው በአውሮፓ ደሴቶች ሲያልፉ በአከባቢው ያሉ አብያተ ክርስትያናት በሙሉ ሙስሊሞች መጥተው ፈትህ እንዳያደርጉ በመፍራት ከበሮ ከመምታት እና ምንም አይነት ድምፅ ከማሰማት ይቆጠቡ ነበር።
#ያኔ_ጀግና_ሳለን
___
🍁 በደውለቱል ኡስማኒያ የአገዛዝ ዘመን በያንዳንዴ ቤት ደጅ ላይ ሁለት የበር ማንኳኩያዎች ይኖራሉ። አንዱ ትልቅ ሲሆን አንዱ ትንሽ ነው። በትልቀኛው ከተንኳኳ አንኳኪው ወንድ ነው'ና በሩን ሊከፍት ሚመጣው ወንድ ይሆናል። ነገር ግን በትንሸኛዋ ከተንኳኳ አንኳኪዋ ሴት መሆኗ ስለሚታወቅ ሴት ትከፍትላታለች።
➖ በዚያ ምርጥ ዘመን አንድ ቤት ውስጥ ሰው ከታመመ ደጅ ላይ ቀይ አበባ ይንጠለጠል ነበር። ያን አበባ የተመለከቱ ሰዎች ሁሉ እዝያ ቤት በሽተኛ መኖሩን ስለሚያውቁ በበሩ ሲያልፉ ድምፃቸውን ዝቅ ያደርጉ ነበር።
#ሹፍ_ምን_እንመስል_እንደነበር!!!
____
🍁 ግዜው ሰላሁዲን አል አዩቢ በይተል መቅዲስን ባስመለሰበት ግዜ ነበር። እና ጦርነቱ ነገውን ሊጀመር ማታ ላይ የጦር መሪው ሰላሁዲን የወታደሮቹን ድንኳን እየዞረ ሲያዳምጥ፤ ግማሹ ለይል ይሰግዳል፣ ሌላው ቁርአን ይቀራል፣ የተቀሩት ደግሞ ይዘክራሉ።
➖ ግን ድንገት በሆነ ድንኳን አጠገብ ሲያልፍ በድንኳኑ ውስጥ ያሉት ሁሉም ተኝተው ነበር። ይህን ግዜ፦"በዚህች ድንኳን አዳሪዎች ምክንያት ልንሸነፍ እንችላለን" ብሎ አለፈ።
___
🍂 ቀደምት ዑለማኦች በሶስት ነገራት አደራ ይባባሉ ነበር።
1፦ሰውዬው በሱ እና በአላህ መካከል ያለውን ግንኙነት ካሳመረ፤ በሱ እና በሌሎች መካከል ያለው ግንኙነት ያምርለታል።
2፦ሰውዬው ሚስጥራዊ ተግባሩን ካሳመረ አላህ ይፋዊ ተግባሩን ያሳምርለታል።
3፦ሰውዬው የአኪራው ጉዳይ ካስጨነቀው አላህ የዱንያውንም የአኪራውንም ጉዳይ ያግራራለታል።
____
#ትልቁ_ኪሳራ_ማለት_ይህ_ነው
ጀነት ስፋቷ የምድርን እና የሰማያትን ያህል ሁና ላንተ በሷ ቦታ ሳይኖርህ ሲቀር...ትልቅ ኪሳራ ነው።
በእለታዊ ፕሮግራምህ ውስጥ ቁርአንን መቅራት ካልተካተተ ወላሂ ትልቅ ኪሳራ ነው።
°
ይህ ታሪክ እንዲሁ አልተፃፈም። ጀግና ትውልድ ለመፍጠር የጀግኖችን ታሪክ ማወቅ ያስፈልጋል። ይልቅንስ በድናችን ጀግና ሆነን ጀግና ትዉልድ እንፍጠር::
🎖ይህን አስደናቂ ፅሁፍ አንብበው ሼር ማድረግ አይዘንጉ!!! منقول
🤝መልካም አዳር
👇👇👇👇👇
https://t.me/nurders/7494