👉🥀የትዳር ገዳይ ወረርሽኞች🌹
👉 ስንፍና ትዳርን ይገድላል ።
👉 አጉል ጥርጣሬ ትዳርን ይገድላል።
👉 አለመከባበር ትዳርን ይገድላል።
👉 አላስፈላጊ ክርክርና ጭቅጭቅ ትዳርን
ይገድላል።
👉 ሚስጥር መደባበቅ ትዳርን ይገድላል።
👉በገንዘብ፣ በስሜት፣ በስነ-ልቦና፣ በቁሳቁስ የሚደረግ ጭቆና ትዳርን ይገድላል።
👉ደካማ የሆነ ተግባቦት ትዳርን ይገድላል።
👉 ከትዳር አጋር ይልቅ ከቤተሰብ ከጓደኛና ከዘመድ አዝማድ ጋር ጊዜን ማሳለፍ ትዳርን ይገድላል።
👉 የትዳር አጋርን ማንጓጠጥ፣ ማዋረድና መዝለፍ ትዳርን ይገድላል።
👉 ወሬ ማብዛትና ጥንቃቄ የጎደለው ንግግር ትዳርን ይገድላል።
👉 ለትዳር አጋርና ለትዳሩም ጭምር በቂ ጊዜ አለመስጠት ትዳርን ይገድላል።
👉ወጪ ማብዛት፣ ድግስ ቸበርቻቻ፣ ከአቅም በላይ ወጪ የሚያስወጡ መኀበራዊ ግንኙነቶች ትዳርን ይገድላሉ።
👉 ለቤተሰብና ለዘመድ የትዳር አጋርን ድክመት መናገር ትዳርን ይገድላል።
👉 ፈጣሪን አለመፍራት፣ ከሃይማኖትም ከዕምነትም ህግጋት ውጭ መሆን ትዳርን ይገድላል።
👉 ከስህተት አለመማርና ጥፋትን ለማረም አለመሞከር ትዳርን ይገድላል።
👉 ጋባዥ ያልሆነ፣ ደባሪ ሙድና ፈገግታ የተለየው ፊትን ለትዳር አጋር አዘውትሮ ማሳዬት ትዳርን ይገድላል።
👉በትዳር ውስጥ ያለንን ኃላፊነትና ድርሻ አለመወጣት ትዳርን ይገድላል።
👉ቁጣንና ብስጭትን መቆጣጠር አለመቻል ትዳርን ይገድላል።........
🌺..እነዚህን ምክሮች ትዳራችንን በመልካም ለመምራት ይረዳናልና አላህ ለሁላችንም ሁሌም ያማረ የተዋበ መልካም ትዳር ያድርግልን🤲
👇👇👇👆👆👆
https://t.me/nurders/7614