👉♻️አንድ ቀን ኢማሙ ሻፊዒይ እና ኡስታዛቸው ኢማም ማሊክ ክርክር ገጠሙ።
ኢማም ማሊክ፦
«የሰው ልጅ በተወኩል ብቻ ያለ ሰበብ ሪዝቁ ይመጣለታል። ለዚህም "ወፍ በአላህ ላይ እንደምትመካው ሰዎችም ብትመኩ ወፍን እንደሚረዝቅ ሁላ እናንተንም ይረዝቅ ነበር።ወፍ ጠዋት በረሀብ ማልዳ ማታ በጥጋብ ትመለሳለች" የሚለው ነብያዊ ሀዲስ ማስረጃ ነው» ብለው ሞገቱ።
ኢማም ሻፊዒይም፦
«አይ ነገሩ እንዲህ አይደለም። ወፍ ጠዋት ማልዳ ባትወጣ አትረዘቅም። ለመረዘቅ አይደለም ሰው ወፍም መሯሯጥ አለባት።» ሲሉ ሞገቱ። የቃላት ክርክሩ መተማመንን አላመጣ ሲል ኢማሙ ሻፊዒይ ሌላ ማሳመኛ መንገድ ፍለጋ ሊያመጡ እያሰላሰሉ ከቦታው ሄዱ።
በመንገድ ላይ ሳሉ አንድ አዛውንት ኩንታል ሙሉ ተምር ተሸክመው ሲንገላቱ ኢማሙ ሻፊዒይ ተመለከቷቸው።
ከአዛውንቱ ኩንታሉን ተቀብለውም ቤቱ አደረሱለት። አዛውንቱም ለመልካም ትብብርህ ማካካሻ ብለው የተወሰኑ ተምሮችን ለሻፊዒይ ሰጧቸው።
ሻፊዒይ ልባቸው በሀሴት ተሞላ፦ «አሁን ሙግቴ ፀናልኝ፤ ይህን ኩንታል ባልሸከም እነኚህን ተምሮች አላገኝም ነበር።»
ብለው ወደ ኡስታዛቸው ኢማም ማሊክ ገሰገሱ።
ልክ ሲደርሱም በእጃቸው የያዟቸውን ተምሮች ለኢማም ማሊክ በስጦታ መልኩ ጀባ አሉ'ና መንገድ ላይ የገጠማቸውን ነግረው፦ «ሰው ያለ ሰበብ አይረዘቅም። እኔም ተሸክሜ ነው ይህንን የተረዘቅኩት» አሏቸው።
ኡስታዙ ኢማም ማሊክ ፈገግ ብለው የደረሳቸውን(ተማሪያቸው) ፊት እየተመለከቱ ከፊታቸው የተቀመጠላቸውን ተምር ጉርስ አደረጉ'ና፦ «ይኸው አንተ ደግሞ የኔን ሪዝቅ እኔ ምንም ሳልደክም ይዘኽልኝ መጣህ» አሉት።
🫵ተመልከቱ የነበራቸው በመሀከላቸው መከባበርና አደብ ኢልም አጂብ ነው ለኛም ኢብራ ትምህርት እንዲሆን ከማለት ለማጋራት ወደድኩ
👇👇👇👇👇
https://t.me/nurders/7497