👉♻️አስለቃሽ ታሪክ እዉነተኛ የእዉነተኛዉ ልጅ የሆነችዉ የአይሻ ቢንት አቡበከር ታሪክ
🤌የእናታችን አይሻ ቢንት አቡበከር ረዲየላሁ አንዐ ሙናፊቆች በዝሙት ስሟን ያጠፉበት ታሪክ በአጭሩ እንዲህ ዳሠነዋል ።
ነቢያችን ሙሀመድ ( ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም) ጉዞ ለመዉጣት ሲያስቡ በባለቤታቸዉ መሀከል እጣ ይጥሉ ነበር እጣ የወጣላትን ባለቤታቸዉ ይዘዉ ይሄዱ ነበር የዚያን ቀን ለእናታችን አይሻ እጣ ወጣላትና ከነቢዩ ሙሀመድ ( ሰለላሁ አለይሂ ወሠለም ) ጋር ጉዞ ወጣች ።
በዚያን ጊዜ ሴቶች ጉዞ ሲወጡ መንገዱ ከመርዘሙ ጋር ጸሐይ እንዳይጏዳቸዉና ከወንዶች እይታ ተሠዉረዉ ኒቃባቸዉን አዉልቀዉ እንዲጏዙ ከግመል በላይ ጎጆቤት የሚመስል አይነት ሀዉደጅ የተባለ መጠለያ ይሠራቸዉን ዉስጡ ገብተዉ ይጏዙ ነበር ። ሴቶች በአንድ ሠፍ ሆነዉ በመሪዎች እየተመሩ በመጏዝ ላይ ነበሩ ከአንድ አከባቢ ሲደርሱ የአሏህ መልዕክተኛ ጦሩ እንዲያርፍ አዘዙ ሴቶች የነበሩበትን ግመሎች ካንበረከኩላቸዉ በኃላ ከግመሎቹ ላይ የነበረዉን አዉደጅ አወረዱላቸዉ እናታችን አይሻ አሏህ ይዉደድላት ከጏደኞቿ ጋር ለመጸዳዳት ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደች ።
ሲመለሡ ነብያችን ሙሀመድ ( ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ) ጦሩ እንዲንቀሳቀስ ትዕዛዝ አስተላልፎ ስለ ነበር ጎጆዋቸዉ ከግመላቸዉ ላይ ተጭኖ ነበር እናታችን አይሻ የአነገቷን ሀብል ለመጸዳጃ በሄደችበት ቦታ ጥላዉ መጥታ ስለ ነበር አጣችዉ ሀብሏን ለማምጣት ለብቻዋ ተመለሠች ማንም አላስተዋላትም ነበር እናታችን አይሻ ሀብሏን አምጥታ ስትመለስ ጦሩ በሙሉ ሄዶዋል ።
ከአዋቂነቷ የተነሳ ሴት ልጅ ለብቻዋ እንደማትሄድ ስለምታቅ ባለችበት ቦታ ረጋች ሲያጡኝ መጥተዉ ይወስዱኛል ብላ በቦታዋ ላይ ቁጭ እንዳለች እንቅልፍ ይዟት ሄደ ነቢያችን ሙሀመድ ( ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ) ከጦሩ በረጂም ርቀት ከኃላ እየተከተለ የሚመጣ የወደቁ እቃዎች ካሉ እየሠበሠበ እንዲመጣ ሰፈዋን የሚባልን ሠሀቢይ መድበዉ ነበር ። ሰፍዋን አይሻ በተኛችበት ፊቱዋ ተገልጦ ስለ ነበር ይመለከታታል በጣም ደንግጦ ላሀዉለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን ሲል እናታችን አይሻ ትሠማዋለች ።
በአሏህ ይሁንብኝ ከነዚህ ቃላት ዉጪ ሌላ ቃላትን አልተናገረም ትላለች አይሻ ግመሉን አንበረከከልኝ ዉጪ እንኻን አላለኝም እራሴ ወጣሁኝ ያለምንም እረፍት ረጂም ሰዓት ተጎዞ ጦሩ ጋር ሲደርሱ ከሡ ግመል ወርዳ ወደ ግመሏ ስትሄድ የሙናፊቆች አለቃ አብዱሏህ ኢብኑ ሰሉል ተመለከታት ወላሂ እሱ ከእሷ አልጸዳም እሷም ከእርሡ አልጸዳችም ዝሙት ሠርተዋል ብሎ ወሬ ማናፈስ ጀመረ ።
ነብያችን ሙሀመድ ( ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ) መዲና በደረሡ ግዜ ሙሉ መዲና ከተማ ዉስጥ ሙናፊቆች የዉሸት ወሬዉን ማናፈስ ጀመሩ እናታችን አይሻ ከመንገድ ስለ ገባች ትንሽ አመማትና ተኛች እስካሁን ድረስ ምንም የደረሳት ወሬ የለም ። አንዴ ገላዋን ለመታጠብ ከኡሙ ሚስጣ ጋር ወጣች ኡሙ ሚስጣ እንቅፋት ሲያደናቅፋት ልጇን ሚስጣ ረገመችዉ አይሻ በሰማች ግዜ አሏህን ፍሪ የበድር ጦርነት ላይ የተሳተፈን ሰዉ ትረግሚያለሽ አለቻት ኡሙ ሚስጣም ለጄ ሚስጣ ምን እያለ እንዳወራብሽ አልሠማሽም አለቻት ምን አለ አለቻት እየተወራ ያለዉን ነገር ሁሉ ነገረቻት ።
ይህ ወሬ ነብያችን ሙሀመድ ( ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ) ጋር ደረሠ አለቻት አዎ ደርሶዋል አለቻት ወደ ቤት ተመልሳ ነቢያችን ሙሀመድ ( ሠለላሁ አለይሂ ወሠለምን ) አስፈቅዳ ወደ ወላጆቿ ቤት ሄደች ኡሚ ሠዎች እንዲህ እያወሩብኝ ለምን አልነገርሽኝም አለች ። ልጄ ተረጋጊ ብላ ልታረጋጋት ሞከረች ተንሠቅስቃ እያለቀሠች ወደ አባቷ አቡበከር ሲዲቅ (ረዲየሏሁ አንሁ ) ሄደች ።
አባቴ ሰዎች የሚያወሩብኝን ነገር ለምን አልነገርከኝም አለችዉ እንደ እናቷ ሊያረጋጋት ሞከሩ ተንሠቅስቃ ማልቀስ ጀመረች ቤተሠቦቿ በለቅሶ ብዛት ትሞታለች ብለዉ እስኪፈሩ ድረስ ቀንና ማታ ማልቀስ ጀመረች የአሏህ መልዕክተኛ አኮረፏት ሌላ ቀን ከሳቸዉ የምታገኘዉን ፍቅር አጣች በሀዘን ላይ ሀዘን በረታበታ ። አንድ ወር ሙሉ ጅብሪል ለነቢያችን ሙሀመድ ( ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ) ዋህይ ይዞ ይወርዳል ስለ ሷ ግን ምንም አይነት ዋህይ አልወረደም አልነገራቸዉም ።
ነብያችን ሙሀመድ (ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም) ከሙናፊቆች በሚደርሳቸዉ አዛ በጅጉ ልባቸዉ ይሠበር ያዝኑ ነበር ። ኻዲማቸዉን አነስ ኢብኑ ማሊክ ጠርተዉት ያአነስ አንድ ቀን እንኳ ከአይሻ የሚያጠረጥርህን ነገር አይታሀል አሉት ያረሡሉሏህ ከቤተሠቦችህ ኸይርን እንጂ አይቼ አላቅም አላቸዉ ።
ኡሳማን ጠየቁት እሱም የአነስ አይነት ምላሽ ከመለሠላቸዉ በኃላ የአይሻን ኳዳሚ በሪራን ይጠይቋት እሷ እዉነቷን ትነግሮታለች አለች በሪራን ጠየቋት ያበሪራ ከአይሻ ጋር ስትኖሪ የሚያጠራጥርሽን ነገር አይተሽባት ታዉቂያለሽ አሏት ያረሡለሏህ ከእሷ መልካምን እንጂ አላየሁባትም አለች ።
ነቢያችን ሙሀመድ ( ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ) የሙናፊቆች አዛ መቆሚያና መቀመጫ ሲያሳጣቸዉ ሚንበር ላይ ወጡና እናንተ ሰዎች ሆይ የዚን ሙናፊቅ ሸር የሚይዝልኝ ማነዉ አሉ ዘዉትር አዛ ያደርገኛል አሁን ደሞ በኔና በባልተቤቴ ሂወት ገባ ሲሉ የአዉስ መሪ የሆነዉ ሳዐድ ቢን ሙዐዝ ተነሳና ያረሡለሏህ ይህ ሠዉ አብዱሏህ ኢብኑ ሰሉል ከኔ ጎሳዎች ከሆነ በአሏህ ይሁንብኝ አሁኑኑ አንገቱን ቀነጥስልሀለዉ ነገር ግን ከወንድሞቻችን ኸዝረጅ ከሆነ ያንተን ትዕዛዝ እሻለሁኝ ከፈለክ አንገቱን እቆርጥልሀለዉ አላቸዉ ። የኸዝረጅ ጎሳ መሪ የሆነዉ ሠዐድ ኢብኑ ኡባዳ ትክክለኛ ሙስሊም ቢሆንም የሆነ ወኔ ያዘዉና ለሰዐድ እኔ ቁጭ ብዬ ከጉሳዬ ሰዉ ትገላለህ በአሏህ ይሁንብኝ አትገለዉም አለ ኡሠይድ የተባለዉ ሰሀቢ ተነሳ አንተ ሙናፊቅ ለሙናፊቅ ትከራከራለህ አለዉ ።
መስጂድ ዉስጥ ቃላት ይለዋወጡ ጀመር ነቢያች ሙሀመድ (ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም) አረጋጏቸዉና ከሚንበራቸዉ ላይ ወርደዉ ከወር በኃላ ለመጀመሪያ ግዜ ወደ እናታችን አይሻ ቤት ሄዱ ከተኛችበት ፍራሽ ጎን ቁጭ አሉ አይሻ ወንጀልን ሰርተሽ ከሆን ተዉበት አድርጊና ወደ አሏህ ተመለሺ አሏህ ይምርሻል ንጹህ ከሆንሽ አሏህ ንጽህናሽን ይመሠክርልሻል አሏት ወደ አባቷ ዞረች አባቴ የአሏህ መልዕክተኛን ስለኔ መልስ ስጣቸዉ አለቻቸዉ ምን ብዬ እንደ ምመልስ አላዉቅም አሏት ወደ እናቷ ዞረች እናቴ ለአሏህ መልዕክተኛ ስለኔ መልስ ስጪ እናቷም ለአሏህ መልክተኛ ምን እንደምመልስ አላዉቅም አለች አይሻም ወላሂ ወንጀል ሰርቼያለሁኝ ብላችሁ ታምኑኛላችሁ ግን አልሠራሁም አልሠራሁም ንጹህ ነኝ ብላችሁ አታምኑኝም አሏህ ምስክሬ ነዉ እኔ ንጹህ ነኝ ዩሱፍ አባት እንዳለዉ ፈሰብሩን ጀሚል ከማለት ዉጪ ሌላ ምንም አልልም አለችና ተከናንባ ተኛችና ።
መንሠቅሠቅ ጀመረች ነቢያችን ሙሀመድ ( ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ) ከቦታቸዉ ሳይነሡ ንጹህነቷን የሚያረጋግጥ የቁርኣን አያ ጅብሪል ይዞ ወረደላቸዉ አብሽሪ የአይሻ ከሠባት ሠማይ በላይ የሆነዉ አሏህ ንጽህናሽን መስክሮልሻል አሏት አባትና እናቷ ተነሺ የአሏህን መልዕክተኛ አመስግኝ አሏት ወላሂ ከአሏህ ዉጪ ማንንም አላመሠግንም ንጹህ እንደሆንኩ ነብያችን ሙሀመድ ( ሰ,ዐ,ወ) ህልም ያያሉ ብዬ እንጂ አንድም ቀን በኔ ሠበብ ቁርዐን ይወርዳል ብዬ ጠብቄ አላዉቅም ነበር ትላለች ሡረቱ ኑር ዉስጥ ስለ ንጽህናዋ አሏህ ተባረከ ወተዐላ 9 አንቀጾችን በማዉረድ መሠከረላት ።