👉♻️ሚስት በባልዋ ላይ ያላት ተጽእኖ!
🤌ሀሰን አል-በስሪ እንዲህ አሉ፡ "በመካ አንድ የጨርቅ ነጋዴ ጋር ቆሜ ልብስ ልገዛው ነበር። እሱም ሸቀጡን ለማራመድ እንዲሸጥለት ሲል ማሞገስና መማል ጀመረ። ስለዚህ እሱን ትቼ ከሌላ ገዛሁ። ከሁለት ዓመት በኋላ ተመልሼ ሳገኘው ሲያሞግስም ሲምልም አልሰማሁትም!
እኔም፡ "ከዓመታት በፊት እዚህ ቆሜ የማውቅህ ሰው አይደለህም እንዴ?" አልኩት።
እሱም፡ "አዎ" አለ።
እኔም፡ "ምን አገኘህና እንደዚህ ሆንክ? ስታሞግስና ስትምል አላይህም!" አልኩት።
እሱም፡ "ሚስት ነበረችኝ። ትንሽ ነገር ይዤ ብመጣ ትንቃለች [ይኸውም ታቃልለች]፣ ብዙ ነገር ይዤ ብመጣ ደግሞ ታሳንሳለች። አላህም ወደ እኔ ተመልክቶ አስወገዳት። ከዛም ሌላ ሴት አገባሁ፣ ወደ ገበያ ልሄድ ስል ልብሴን ትይዝና
"እገሌ ሆይ! አላህን ፍራ! ጥሩ ነገር እንጂ አታብላን። ትንሽ ይዘህ ብትመጣልን እናሳምረዋለን፣ ምንም ይዘህ ባትመጣልን ደግሞ ባለን ነገር እንብቃቃለን" ትለኛለች።
[አል-ሙጃላሳ ወጀዋሂር አል-ዒልም (ገጽ 141)]
ከዚህ ታሪክ የምንረዳው ሚስት በባሏ ላይ ያላትን ተጽእኖ ያሳያል። አንዲት ሚስት ባሏን በመደገፍና በማበረታታት ቀጥተኛና ታማኝ እንዲሆን ልትረዳው ትችላለች። በተቃራኒው ደግሞ ባሏን በማንቋሸሽና በማሳነስ አሉታዊ ተጽእኖ ልታሳድርበት ትችላለች። ስለዚህ ሚስቶች ባሎቻቸውን መደገፍና ማበረታታት፣ ባሎችም ሚስቶቻቸውን ማክበርና ማድነቅ አለባቸው።
🤝መልካም አዳር
👇👇👇👆👆👆
https://t.me/nurders/7608